በይፋ መጥተዋል!
ጌታቸው ሽፈራው
የኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ላይ በዓል ማክበር አብዝቷል። ለየት ለማድረግ “በኦሮሚያ ደረጃ ተከበረ” ይሉናል። አሁን አዲስ አበባ ላይ በኦሮሚያ ደረጃ እያሉ በበዓል ስም ከማለማመድ አልፈው በግልፅ መጥተዋል። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተቋም ሲገነባ ሪቫን ቆራጩ ሽመልስ አብዲሳ ሆኗል፣ ከአዳነች አቤቤ ጋር።
ልክ አማራ ክልል ከተሞች ላይ ተቋማት ሲገነቡ፣ ፋብሪካዎች ሲሰሩ አገኘሁ፣ ሶማሊ ክልል ከተሞች ላይ ደግሞ ሙስጦፋ ከከተማ ከንቲባዎቹ ጋር እንደሚገኙት መሆኑ ነው። አዲስ አበባን የኦሮሚያ ክልል ከተማ አድርገዋት ሽመልስ ከንቲባዋ ጋር ፊት አውራሪ ሆኖ ይገኛል። ኦ ቢ ኤን የሽመልስና የአዳነችን ሲዘግብ፣ ሌሎቹ አብይና አዳነች ተገኝተው የመረቁትን ያሳያሉ። በቀጣይ ቀስ እያሉ ሁሉም ሽመልስ የሚገኝበትን ይዘግቡታል።
ፎቶው አዲስ አበባ ላይ በሚመረቅ ፋብሪካ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት በቀይ ምንጣፍ ተሻግሮ ወደሪቫኑ ሲሄድ ነው። አራዳ ነኝ ብለህ “ምን ችግር አለው ታዲያ?” በለኝ! ይህን ተጠቅሞ ነው የሚጫወትብህ!
ይህ አጀንዳ የሚገባህ፣ ፖለቲካውንም ፕሮቶኮሉንም የምታውቀው ከሆነ ብቻ ነው፣ “ምን ችግር አለው” የሚል “አራዳነት” ከለመደብህ የማንም የቁማሩ ካርድ ሆነህ ሲያነሳ ሲጥልህ/ሲጫወትብህ/ የምትውል ሆነህ ትቀራለህ!