>

በመረጃ የተደገፈ ሙግት ! (ተወልደ በየነ  ((ተቦርነ)

በመረጃ የተደገፈ ሙግት !

ተወልደ በየነ  (ተቦርነ)

መጋቢት 30,2013 አ.ም ለኪነ- ጥበብ ባለሙያዎች የተሰጠው ሽልማት ተሸላሚዎችን ከለየበት መስፈርቶች አንዱ አንጋፋነት መሆኑ በአዘጋጆቹ ተነግሯል።በዚህ መሰረት ተሸላሚዎቹ  የስድሳ እና ከዛ በላይ እድሜ ባለቤት  መሆን እንደሚኖርባቸውም ተገልጿል።አዘጋጆቹ በገለፁት መለኪያ መሰረት ሽልማቱ ሲገመገም ከዚህ በታች የምዘረዝራቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎች እድሜ ወይም ሽልማቱ የተጭበረበረ አይመስላችሁም?
ከድምፃውያን
-አያሌው መስፍን
-ጠለላ ከበደ
-ፀሀይ እንዳለ
-ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
-ተሾመ ወልዴ
-ተሾመ አሰግድ
-በዛ ወርቅ አስፋው
-ጌታቸው አስፋው
-ጥላዬ ጨዋቃ
-ፀጋዬ ደንደና
-ስዩም ጥላሁን
-የመቶ አለቃ ግርማ ሞገስ
-አበበ ሀይለሚካኤል
-ወሮታው ውበት
-ውሽንፍር አርጋው
-የመቶአለቃ ውብሻው ስለሺ
-መንበረ በየነ
ከትያትር ባለሙያዎች
-ጌታቸው አብዲ
-አልአዛር ሳሙኤል
-አዳነች ወ/ገብርኤል
-ገለታ ተ/ፃዲቅ
-ጀማነሽ ሰለሞን
የዜማና ግጥም ደራሲዎች
-አምሀ ተወዳጅ
-ሻለቃ ክፍሌ አቦቸር
-ያየህይራድ አላምረው
-የኔው አካሉ
-ዘላለም መኩርያ
-ሶስና ታደሰ
ሙዚቀኞች
-ጥላዬ ገብሬ
-ሞገስ ሀብቴ
-ሀይሉ መርጊያ
-ዮሀንስ ተኮላ
-ስምኦን ሊበን
-ኤልያስ ወንድሙ
-ብሩክ ክፍሌ
-ይስሀቅ ባንጃው
-ጉልቱ ተፈራ
-ዳዊት ሰንበቶ
-ሰላም ስዩም
-ፈቃደ አምደመስቀል
-አለምሰገድ ከበደ
-ኤልያስ በቀለ
-ሽመልስ በየነ
-ታምሬ ወልደየስ
-ፈለቀ ሀይሉ
-ብሩክ ከበደ
-ቸርነት ለማ
-ሰለሞን አባተ
-ዳንኤል በቀለ
-አባተ በሪሁን
ከደራሲያን
-አለማየሁ ገላጋይ
-ዉድነህ ክፍሌ
-ዘነበ ወላ
በነገራችን ላይ በሽልማቱ ሰነስርአት ካልተካተቱ የኪነጥበብ ዘርፎች ውስጥ የውዝዋዜ  እና የመድረክ አስተዋዋቂነት ሙያዎች ይገኙበታል ።አዘጋጆች ሆይ በእነዚህ ሙያዎች ውስጥ ያለፉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን እንደ ኡጋንዳዊ ወይስ ታንዛንያዊ ቆጥራችሗቸዉ ይሆን ወይ? እኛ እልፍ ኢትዮጵያዉያን ግን የተሸለሙትንም ሆነ ያልተሸለሙትን ጥበበኞቻችንን የሙያ በረከቶቻቸዉን ከፍ ባለደረጃ ሁሌም ስንዘክር እንኖራለን!
በነገራችን ላይ የዘረዘርኳቸዉ የኪነጥበብ ሰዎች የእድሜ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሸልማቱን መስፈርቶች እንደሚያሟሉ የማምንባቸዉ ናቸዉ።
 ወንድሜን ታማኝ በየነን  እንደሽልማት ኮሚቴዉ ዘንግቼዉ አይደለም።በዚህ አጋጣሚ እንኳን ከሸላሚዎቹ  የሻሞ የሜዳልያ ሽልማት አተረፈህ ልለዉ እወዳለዉ!
Filed in: Amharic