>

አዲስ አበባን በውሃ የማንበርከክ የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ እስትራቴጂ!!! (ኢትዮ 360)

አዲስ አበባን በውሃ የማንበርከክ የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ እስትራቴጂ!!!

ኢትዮ 360

 

*… ልዩ የውሀ ክፍያ  ለኦሮሚያ በ60 ቀናት ውስጥ  ካልከፈለ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ያለውን የውሃ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የማቋረጥ ሥልጣን አለው…!!!
 
 በቅርቡ አቢይ አህመድ የሚመራው  የሚኒስትሮች ምክር ቤት  የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ የማስከበር አጀንዳውን ለማስፈፀም እና አዲስ  አቤቤን በጉልበት ለማንበርከክ በውሃ ሀብት አጠቃቀም ላይ አስደንጋጭ ረቂቅ አዋጅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። በአዋጁ ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው
1.  የአዲስ አበባን የዉሀ ባለስልጣን ሙሉ በሙሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያስተዳድራል።
2.  የአዲስ አበባ ህዝብ በየወሩ ከሚከፈለው የውሃ ክፍያ በተጨማሪ ልዩ የውሃ ግብር ለኦሮሚያ ይከፍላል።
3.  ከኦሮሚያ ክልል ተመርተው ከሚመጡ  የታሸጉ የውሃ መጠጦች ላይ ከተለመደው የቫት ክፍያ ውጪልዩ የዉሀ ታክስ ለኦሮሚያ ክልል እንዲከፈል ያስገድዳል።
4.  ይህ ልዩ ክፍያ የመጠጥ ውሃን ብቻ ሳይሆን ለመዝናኛ /የመዋኛ ስፍራ፣ አርቴፍሻል ፏፏቴ…/፣ለመስኖ ልማት እና  ለኢንደስትሪ የሚውል የውሃ ፍጆታንም ያካትታል።
5.  በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ሀይቆች የሚመረቱ የዓሳ ምርቶችም ሥዋጋቸው በኪሎግራም ተመዝኖ የዉሃ ታሪፍ ይወጣለታል ምክንያቱም ዓሣው ጠጥቶ ያደገው የኦሮሚያን ውሃ ስለሆነ።
6.  የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከላይ ለተዘረዘሩት ተግባራት ለተጠቀመዉ ውሃ ከመደበኛው የዉሃ ታሪፍ ውጪ የኦሮሚያ ክልል ተምኖ ያስቀመጠውን ልዩ የውሀ ክፍያ  ለኦሮሚያ በ60 ቀናት ውስጥ  ካልከፈለ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ያለውን የውሃ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የማቋረጥ ሥልጣን አለው።
7. አዋጁ ሐረርና ድሬዳዋንም ያካትታል
 ጥያቄ
•  አዲስ አበባ ውስጥ አብይ አህመድ የተከላቸው ችግኞች ለሚጠጡት  ውሃ የሚከፍለው ማን ነው?
•  በግብጽና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው ?
Filed in: Amharic