>

ዘረኝነት ፀረ እግዚአብሔርና ፀረ ሰበእ መቅሰፍት ነው!!! (በመምህር ፋንታሁን ዋቄ)

ዘረኝነት ፀረ እግዚአብሔርና ፀረ ሰበእ መቅሰፍት ነው!!!

በመምህር ፋንታሁን ዋቄ

ሰው ሆኖ በመቆምና ከአራዊታዊ የቡድን እሳቤ (groupthink) እሥረኝነት ነፃ በመውጣት ሰውነትን እንታደግ!!!
በእጃችን ላይ የሚገኘው አገራዊ ፈተና የአእምሮ በስሕተት ትምህርት መታጠብ ውጤትነው! መፍትሔውም ወደ ሰውነት መመለስ ብቻ ነው!!!
የቡድን እሳቤ (Groupthink)፣ የአእምሮ አጠባ  ፖለቲካና በሃይማኖት ላይ የሚያመጣው ጣጣ!!
 እያናንዳንዱ ሰው ከተሠራለት ሣጥን ውጭ  በማሰብ የሚያተርፈው እንጂ የሚከሥረው ነገር የለም!!
በቡድን ሣጥን መታሠር በሁሉ ቦታ፣ በሁሉ ውሥጥ ሆኖ ሁሉን የያዘውን  እግዚአብሔርን እንኳ ማየትን ይከለክላል!!!
አንባቢ ሆይ ምናልባት ለአንተ ወይንም ለአንቺ ሳይታወቅሽ  አእምሮህ/ሽ በሚገባ ታጥቦ በአንድ ሣጥን ውስጥ ተቆልፎብህ/ሽ ሊሆን ይችላል፡፡
ለምሳሌ አንድ ጃጃ የሚባለ ሀሳባዊ የጎሣ ነጻ አውጭ አለ እንበል፡፡
ጃጃ የግል ፍላጎትህን የሚደግፍ ፕሮፓጋንዳ ይግትሀል፤ ጃጃ በድንገት ከመንገድ ላይ ጠልፎህ በአንድ ምሽግ ውስጥ አስቀመጠህ፤  ዘወትር ይሰብክሀል፣ ሲያምህ በእንክብካቤ ያክምሀል፣ እራትና ምሳህን ከለመድከው በተሻለ አዘጋጅቶ ያበላሀል፤ ከሳምንታት በኃላ  እያመንካውና እየወደድው፣ የልህን በልቡናህ እያሳደርህ፣ አስቀድሞ የምታስባቸውን በአዲሱ ስብከት እየተካህ ትመጣለህ፡፡
ጃጃ እንዳመንኸውና የራስህን የኖረ አስተሳሰብ እንደተውክ፣ አንተ እንደ ማኅደር እርሱ እንደ ኀዳሪ ሆኖ  ግኑኝነታችሁ እንደተለወጠ ካረጋገጡዠጠ በኃላ  አንድ ምክረ ሀሳብ ቀርቦልሀል፡፡ እርሱም።፦
— ኦርቶዶከሳዊ እምነት  የእገሌ በሔር እምነት ነው፤ ያንተ ሌላ ነው፣  ወደ አዲስ አባባ እና ሌሎች ከተሞች ገብተን አቢያተክርስቲያናትን እናቃጥል፣
ክርስቲኖችን እናባርር፣
መንግሥት ሥራችንን እንዳያስቆመን በቡድን ጫና እናድርግበት ወዘተ ብለው ቢነግሩህ አሳባቸውን ለመቃወም ወይንም ሌላ አሳብ ለማቅረብ አቅምንስሃል፡፡
 ስህተታቸውን መምርመር አትችልም፤ እስከ ሞት ከጃጃ ጋር ተባብረህ ትዋጋለህ፡፡ ይህ አእምሮህ መታጠቡን ፍንጭ ይሰጥሀል፡፡
ትምህርት ቤቶች እንደ አእምሮ ማጠቢያ ካምፖች፡-
ትምህርት ቤቶች ከላይ ሲመለከቷቸው እውቀት አውዶች ናቸው፡፡  በተግባር ግን የሚሰጡት እውቀት በርእዮተ ዓለም ወይንም በአንድ አቅም ያላቸው አካላት በወሰኑት የአስተሳሰብ አቅጣጫ ተውልድ ለመፍጠር በሚጥሩ ቡድኖች ሰውን ወደ ማሽን መቀየሪያ ቦታዎች የይሆናሉ፡፡
ትምህርት ቤት መሥርተው የሚመሩ ሰዎች የሚገቡትን ሰዎች በአንድ አስቀድሞ በተወሰነ መንገድ እንዲያስቡ ግብ አስቀምጠው ይሠራሉ፡፡
አገር በቀሎች  አስተሳሰቦች ትክክል አይደሉም፣ ሌሎችና በትምህርት ቤቱ የሚመሰከርላቸው ትክክል ናቸው፤ አንዳንድ ድርጊቶች  መልካም፣ ሌሎች ክፉ ብሎ የሚበየነውም በትምህርት ይዘቱ ነው በሚል ዶግማ ይመራል፡፡
ለምሳሌ ሃይማኖት ጎሣና ዘር የለውም ማለት ስህተት ነው፤ የእገሌ እምነት የእነዛ እንጂ የአንተ አይደለም፤ የአንተ እንትን የተባለ እምነት ነው!!!  ከዚህ ውጭ የሆነ መሰደድ፣ መገደል አለበት!! ወዘተ የሚል ትምህርት ሊሰጥ ይችላል፡፡
በዚህ ዶግማዊ ሣጥን ይፈበረካል፣ ብዙ እሥረኞች ወደዚህ ይጋዛሉ፡፡ ወደ እሥሩ የገቡ ሁሉ ብዙ መረጃዎችና ትንታኔ በየበኩላቸው መሥጠት ይችላሉ:: ያን የተረኩትን፣ የተነተኑትን፣ ያመኑትን ያልሙታል፡፡ ላለሙት ሕልም ጠበቃ ይሆናሉ፣ ያራምዳሉ፣ ይገሉለተል ይሞቱለታል፤ ይሰደዱለታልም ያሳድዱለታል፡፡
በቢዝነስ ትምህርት ቤት ለምሳሌ ተማሪዎች ትርፍና ኪሣራ የማስላት ትምህርት ይማራሉ፤ ከዚህ የተነሳ ብዙ ተማሪዎች የዓለም ማያቸውን በትርፍና ኪሳራ ስሌት ብቻ የመመልከት ሣጥን ውስጥ ይቆልፉበታል፡፡  ወላጆች ልጅ ለመውለድ ሲያስቡ ስለ ትርፍና ኪሳራ ማላት ይጀምራሉ፤ ፖለቲከኞች ስለ ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ሲነጋገሩ በትርፍና ኪሣራ ያሰላሉ፡፡
በንፅፅር፣  ፍልስፍና ትምህርት ሲሰጥ የተለያዩ አቀራረቦች አሉት፡- ልምን እንኖራለን? ሰው እንዴት መኖር ይኖርበታል  እንዴት ቢተዳደር መልካም ነው?  መልካም ራሱ በምን ይመዘናል?  ፍቅር ደስታ፣ ሩካቤ ሥጋ፣ ድልና ስኬት  ወዘተ በመተንተን ተማሪዎች የሚያስቡበትን፣ የሚናገሩበትንና ለድርጊት የሚወስኑበትን ማያ ይቀረፃል፡፡
በዚህ መንገድ ስንመዝነው ትምህርት ቤቶች ዋንኛ አእምሮ ማጠቢያ ማዕከላት ናቸው፡፡
ፖለቲካዊ አእምሮ አጠባ !
የየቀድሞው ጆርጅ ቡሽ አስተዳደር የፕሬስ ሰክሬታሪ የነበረው ስኮት ሚክልላን (Scott McLellan)  አስተዳደሩን ከለቀቀ በኃላ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ እንዲ ይላል፡-  ሥራዬን ለቅቄ ማሰብ እስክጀምር ድረስ ፖለቲካው አእምሮዬን ስላጠበው ስናገር የነሮኩትን ሁሉ ለምን እንደምናገር ተጠራጥሬው አላውቅም፤ ለብዙ ዓመታት የተነገረኝን ሁሉ ያለ ጥያቄ እከተል ነበር፤
 ከልቤ አምኜ ነበር፣ አሁን ግን ሳስበው ሌሎ በእን ውስጥ ሆነው ሲገለገሉብኝ እንደሆነ ተረዳሁ ፡፡
 ይህ ዛሬ በኢትዮጵችን የጎሣ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ራሳቸውም መንጋ ሆነው ሕዝቡን አእምሮ ተቆጣጥረው እንደሚመሩት ማለት ነው፡፡ ራሳቸው ማደሪያ ሆነው በሌሎች ዜጎች ላይ በሁለተኛ ደረጃነት  ያድሩባቸዋል፡፡
ሁላችንም ሁሉ ጊዜ አእምሮአችንን ማጠብ በቻሉ አካላት አዳሪነት ማደሪያ ሆነን እንንከላወሳለን፡፡
 ስንገድልም ስንሞትም በሰዎች ማደሪያነት ነው፡፡
እስቲ ራሳችንን አሁን ከምንገኝበት የአገራችን ሁኔታ አንጻር እንፈትሽ (ክርስቲኖች እንኳ ሳንቀር)፡-
#አንዳንዶቻችን አንድ ጎሣ ፓርቲ አባላት ወይንም ደጋፊዎች ነን፣ ይህ ከኦርቶዶክሳዊነታችን እንዳይበልጥብን ሚዛኑን እናውቅ ይሆን?
#አንዳንዶቻችን የአውሮጳ የኳስ ክለብ ቲፎዞዎች ወይንም የአንዱ የኢትዮጵ ክፍል ሰፖርት ክለብ አባል ነን ፤ ይህ ክርስቲያናዊ ተልእኮአችን በምድር ምን እንደሆነ ያዘነጋን ይሆን?
#አንዳንዶቻችን ዳንሰኞችና ተወዛዋዦች የመዝናኛ ክለብ ሠራተኞ ነን፤ ይህ ሕሊናንና እግዚአብሔርን እንድንዘነጋ ያደርገን ይሆን?
#አንዳንዶቻችን የቢዘነስ አማካሪዎችና ዘወትር ስለ ትርፋማነት የምንጨነቅ ነን፤ ይህ ንጽሕናችንን ይፈታተነን ይሆን?
#አንዳንዶቻችን በግብርና ሚኒስቴር የአግሪካልቾራል ትራንስፎረሜሽን ኤጀንሲ ሠራቶኞች ሆነን ረሀብን ለማጥፋትና ኢትዮጵያን በምግብ ራሷን ለማስቻል ከልባችን የምንተጋ ነን፤ ይህ እንጀራችንን የባዕዳን ጥገኛ በሚያደርግ መንገድ እየሠራን አለመሆናችንን ተጨንቀን እንመረምር ይሆን?
በሁሉም በተሠማራንበት አገልግሎት ክልክልና የተፈቀደ አለ፣ ስታንዳርድ አለ፣ የጥራትና የወጤታማነት መሥፍርት አለ? ግብና ዓላማ ተቀምጦልን፣ እኛም ለራሳችን አስቀምጠን ነው የምንሠራው?
እንዚህ ሁሉ በእውነት ከእኛ ውስጥ ማለትም ከምናምነው እውነተኛ ሃይማኖት፣ ከተፈጠርንበት ዓላማ ጋር ተገናዝበው የተቀበልናቸው ናቸው?
ግልፅ የሆነ መንፈሳዊና፣ አገራዊና ታሪካዊ፣ ፍልስፍናዊና ባህላዊ ሚዛን አይቷቸው ያውቃል?
 የለም፡፡ ሁላችን በገባንበት መስክ እንደ ሮቦት የምንነዳ አእምሮአችን መታጠቡን ሳናውቅ የምንኖር ማኅደሮች ነን፡፡
እሰቲ እያንዳንዳችን ስለምንሠራበት መሥራያ ቤት ወይንም ስለሥራችን እናስብ፡፡  ምናልባት ከባልደረባዎቻችን ጋር የምንጋራው እሴት መሥረተን ይናል፤ ግን እነዚያ እሴቶች የአእምሮ አጠባ ውጤቶች ይሆናሉ፡፡ ጥያቄ አንስተን ሞግተናቸው ላናውቅ እንችላለን፡፡   ሁሉም ሰው እንደ ፍጹምና ትክክለኛ እሴቶች ተቀብሎአቸው አብሮ ይኖራል፡፡ የሚጠራጠሩ ከተገኙ እንደአጥፊና አፈንጋጭ ጥግ እንዲይዙ ይደረጋሉ፡፡
በክርስትና ውስጥ የሁሉ ሚዛንና መስፈረት፣ ልኬት፣ መነሻና መድረሻ ሰው የሆነው አምላክ እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በሌሎች ያ የማይደራደሩበት እምነታቸው ነው፡፡ ዛሬ ግን ሁሉ ነገር ዝግመተ ለውጣዊ በመሆኑ ቋሚና ዘለቄታዊ እሴትና ልኬት የለም፡፡ ስለዚህ የሚነዱን ሁሉ ወደሚነዱን እንድንሄድላቸው በየጊዜው የራሳቸውን አዳዲስ ዶግማዎች ፈጥረው በአእምሮ አጠባ ስልት ይጭኑብናል፡፡
ዛሬ ኦርቶዶክሳዊት (ከቀዳሚ እግዚአበሔር አስቀድማ አንድ ጊዜ ለቅዱሳን የተሰጠች ፍጹም፣ መለዋወጥ የሌላባት፣ ዶግማ ያላት እምነት) እምነትን እንኳ በጎሣና በፖለቲካ፣ በቋንቋና በሀሰት ትርክት በሚመሠረት እሴት መገዳደር እየተለመደ ነው፡፡
በዚህ አእምሮ አጠባ ምክኒያት ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ካህናት ሳይቀሩ በጎሣና በቋንቋ ግራ ሲጋቡ መመልከትና፣ ግጭትና ግድያ፣ ማፈናቀልና ነጠቃ ቀጥሏል፡፡
ትናንት ምዕራባዊያን  መፈክራቸው ለውጥ! አስቀድሞ   “አመለካከትና እይታ”! ኃላቀርና ዘመናዊ!  እያለ ነባሩን እሴት ሁሉ ወጋቢስ እያሰኘና  እያስረጀከ፣ አዲሱን እያስደነቀ እና ከፍጰእያደረገ በከንቱ ይንሳፈፈፋል፡፡ ተ
ጨባጭ ሕይወት የሚነግረን ግን ጥንት የተሠሩ መኪኖች ሁሉ ይሽከረከራሉ፣ ለዚህም የተጠረገ ጎዳና የግድ ነው፡፡ መንግድ የማያስፈልገው መኪና የለም፡፡ እንዲኖር ከተፈለገ ወይበራሪ ወይ እንደሰው የሚራመድና የሚዘል መፈብረክ የግድ ይላል፡፡  ሰውም በእግዚአብሔር የተፈጠረና በፈጣሪው አምሳልና አርያ እና ከፈጣሪውግና አንድነት ሰው ውጭ መኖር ከሞከረ ሰውነቱ መቅረት አለበት፡፡
ዛሬ በአእምሮ አጠባ ሰውነታቸውን ያጡ የፖለቲካና የዘረኝነት ደዌ ያንገላታቸው አገርና ዓለምን መከራ ውስጥ አስገብተዋታል፡፡ ሰውነታቸውን ስላጡት ለሰው የሚሆነውንና የሚበጀውን አላወቁም፡፡
ለምንገኝት ውድቀት መፍትሔው መሪዎች ራሳቸውም አእምሮአቸው የታጠበውን ያህል እኛን ለማጠብ መሞከራቸውን ማቆም፤ እኛም ከመታጠብ ለመመለስ ፍጹምና እውነት የሆነውን  ለመፈለግ ከቡድን እሳቤ ነጻነታችንን ማወጅ ይኖርብናል፡፡
  በአክቲቪስቲና በታዋቂ ሰዎች ተሰጥቶት መመራት መቆም ይኖርበታል፡፡
እያንዳንዱ ፍጡር ፈጣሪውንና ራሱን አክብሮ ይቁም፣
 ቀጥሎም የእግዚአብሔርን ቃል ከጤናማ መምህራን ይስማ፤
ታሪክንና አተራረኩን ከበሽተኞች ሳሆነ ፈሪሓ እግዚአብሔር፣ ፍቅረ-ሰብ እና የእውነት ጠበቃ ጀሆኑት ብቻ ያዳምጥ፤ የራሱን ሕሊና ያክብር፣ ሞትና ማጣትን አይፍራ
 —- ያን ጊዜ ነጻነት ስለሚኖረው ማመዛዘን ይችላል፤ ከመንጋነትና ሮቦትነት ይላቀቃል፡፡
የተቆለፈብን ሣጥን የሚሠበረው ለአፍታምቷ ቢሆንቷ ከጫጫታ ወጣ ብልን በራሳችን ማሰብ ስንጀምር ነው፡፡ ለነገሩ በዘር ፖለቲካ የናወዝን፣ በእስታዲየም ጫጫታ፣ በባለቀለም ትሌቪዥን ላመቀርቡ ደራማዎችና ፊልሞች የደነዘዝን፣ በብልሹ የአገር አስተዳደር ተስፋችንን የተነጠቅን፣ በወንጌል አገልግሎት መሳሳት ሴኩላሪዝም ነግሦ  ሆድና ምድርን እንጂ ሰማይና እግዚአበሔርን የዘነጋን እኛ የአእምሮ አጠባ ሰለባዎች ነን፡፡
እኛም መሪዎቻችንም፡፡ መሪዎቻችን በእርዳታ ሰጭዎቻቸውን ድግሪ በአደሏቸው ፕሮፌሰሮቻቸው አእምሮአቸው ታጥቧል፤ እኛ ተከታዮቻቸው በእነረሱ ፕሮፓጋንዳ አእምሮአችን ታጥቧል፡፡
#ታዲያ እኛም እነረሱም  መሪዎቻችኘ ከተቆለፈብን ሣጥን ነፃነትን እንዴት እናገኛለን?
 የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራችንን በመጠየቅ እንጀምር፡-
#አባል የሆንበት የፖለቲካ ፓረቲ ወይንም የምንደግፈው የፖለቲካ መሥመር ፍልስፍናው ምንጩ ነው?
የምንኖርበት ማኅበረሰብና ከልባችን ተቀብለን የምናራምደው አስተሳሰብ ምንጩ ምንድነው?
#ስኬት ነው ብለን የምንጓጓለት ሕይወትን ለመምረጥ የተጠቀምንበት መሥፍረት ምንጩ ምንድነው?
#እየሰጠን ያለው አገልግሎት፣ ወይንም እየሠራን ምንገኘው ሥራ ዓላማና ውጤትን የተቀበልንብነት ምክኒያት ምንድነው?
#ባርነትና ነጻነት፣ ደስታና ሀዘን፣ ትልቅነትና ትንሽነት፣ ውርደትና ክብር፣ ፍቅርና ጥላቻ የምንላቸውን ፅንሰ አሳቦች የምንረዳበትን ማያ (ሥርዓተ አስተሳሰብና እምንት) ከወዴት አገኘነው?
እነዚህን አምስት ጥያቄዎች መልስ በጥንቃቄ እንጻፋቸው፤ ቀጥለን መልሶቻችንን ከክርስቲያናዊ ወይንም አምነታችን ከሚያስተምረን፣ የእምነታችን ምሳሌዎች  ከኖሩበት መንገድ ጋር እናገናዝብ፤ በመጨረሻ ልዩነቱን ለማረም ውሳኔ እናድረግ፡፡
ማሰብ እንጀምር!!  የጃጃ ፓርቲ፣ የጃጃ ጎሳ፣ የጃጃ ንዑስ ብሔር፣ የጃጃ ታሪክ አተራረክ፣ የጃጃ ሥርዓተ ትምህርት፣ የጃጃ ጆርናሊዝምና ሚዲያ፣ የጃጃ ኪነ ጥበብ፣ የጃጃ ፖሊሲዎችና ሕጎች ሃይማኖታችንን ተክተው አእምሮእችንን ሊያጥቡና በአንድ የቡድን አሳብሣጥን ውስጥ እንዳይቆልፉብን።
የምናደርገው አዲስ ውሳኔ የተቆለፈብንን ሣጥን ለመስበር የመጀመሪያው የማሰብ መጀመሪያና መዶሻ ነው!!
ከእግዚአብሔር ተለይተው የተፈጠሩ ቡድኖች እሥረኛ ከመሆን የነፃነት ተጋድሎ የምንጀምርበት መንገድ ነው!!!
እኛ ጎሣችን ክርስቶስ አገራችን ኢትዮጵያ፣  ታሪካችን ከሰው-እግዚአብሔር ግኑኝነት እና ይህን ግኑኝነት ለመበጠስ ጠላት ዲያብሎስ ካደረባቸው አስተሳሰቦችና ተግባራት ጋር ያደረግነው ተጋድሎ ወገባ ነው።
የዘር ታሪክ ጽፈንም አስተምረንም አናውቅም። ይህን ቀሳፊ ፀረ ኦርቶዶክስ ጉዞ አንድ ሆነን በፍቅራችንና ርኲሰትን በመፀየፍ እናስቆመዋለን። እኛ የክርስቶስ መንጋ እንጂ የሰዎችና የሰውሠራሽ እሳቤ መሪ ተቋማት የቡድን ሣጥን እስረኞች አይደለንም።
አንድ ነገር በእርግጠኝነት እንወቅ፦
የዘረኝነት መነሻው ሐሰተኝነት ነው
የሐሰት አባቷ ዲያብሎስ ነው
ዲያብሎስ ለእውነት ጠላቷ ነው
እውነት ክርስቶስ ነው
ክርስቶስ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ነው
ዘረኝነት ፀረ ክርስቶስነት ነው
ፀረ ክርስቶስ የሆነ ፀረ ሰው ነው
—- ስለዚህም ዘረኝነት ፀረ ሰውነት፤ ፀረ እግዚአብሔርነትና ዲያብሎሳዊነት ነው።
—- ስለዚህ የኢትዮጵያ የብሔር ፖለቲካ የዲያብሎስ ነው። ዲያብሎስ ፀረ ክርስቲያን ነው
—- ስለዚህም ክርስቲያንን ያርዳል ያሳርዳል።
—- በመላው ኦሮሚያ የነገሰውና ደም የሚያፈሰው ይኼው ዲያብሎስ በማደሪያዎቹ ሐሰተኞቹና ዘረኞቹ መሣሪያነት ነው።
ጸልዩ!!! ሰው እንሁንና ከሰውነት ለወጡት ምሳሌ እንሁን።
Filed in: Amharic