ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
እንደምታዩት የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫው ፈጽሞ የውሸት ምርጫ መሆኑን ተረድቶ የምርጫ ካርድ ከማውጣት ተቆጥቧል!!!
የተቃዋሚ ፓርቲ ተብየዎች ደግሞ እንደምታዩዋቸው ምርጫ በሚካሔድባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ከ80% በላይ ዕጩ ማስመዝገብና የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ፈጽሞ ባልቻሉበት ሁኔታ እንዴት ብለው “እናሸንፋለን!” ብለው እንዳሰቡ እግዚአብሔር ይወቅላቸው እስከአሁንም እራሳቸውን ከምርጫ ሳያገሉ በዚህ የውሸት ምርጫ እንደሚሳተፉ እየገለጹ ነው የሚገኙት!!!
በመሆኑም እንደምታዩት የሕዝቡና የተቃዋሚ ፓርቲ ተብየዎች ሐሳብ አቋምና አመለካከት ፈጽሞ አልተገናኝቶም ሆኗል!!! ይሄም እጅግ የሚገርምና የሚያሳዝን ነው!!!
ምርጫው የውሸት መሆኑ ቁልጭ ብሎ እየታየ ሌላው ቀርቶ ተመራጭ ማስመዝገብና ቅስቀሳ ማድረግ እንኳ ያልቻሉበት ሁኔታ እንደሆነ ያለው እያዩ አሁንም በውሸቱ ምርጫ ለመሳተፍ መፈለጋቸው የሚያሳየው ነገር ተቃዋሚዎች የቁም ቅዠት ውስጥ ያሉ የሥልጣን ጥመኞች መሆናቸውን ነው እንጅ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ የሚታገሉ የዲሞክራሲ ታጋዮች መሆናቸውን አይደለም!!!
የሚገርመኝ ነገር ሕዝብ የምርጫ ካርድ አለማውጣቱን እያዩ ማን ይመርጠናል ብለው ነው ለመሆኑ ተቃዋሚ ተብየዎች እንዲህ ያሰፈሰፉት??? ተመራጮቻቸው መቸ ተመዘገቡና ነው የሚመረጡት??? በጣም እኮ የሚገርም ነገር እኮነው ወገኖቸ!!! ሰው ይሄንን ያህል በቀን ቅዠት ውስጥ ይሰምጣል???
አገዛዙ ደግሞ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች እየሰማቹህት እንዳለው ካርድ መውሰድ የፈለጉ ጥቂት ሰዎች ቢኖሩም እንኳ ካርድ ለማውጣት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ሲሔዱ የምርጫ ካርድ ላለመስጠት የምርጫ ጣቢያዎችን ዘግቶ በመጥፋት፣ “ካርድ አልቋል!” በማለትና የተለያየ ሐሰተኛ ምክንያት እየሰጠ ካርድ ሳይሰጥ እየመለሳቸው ይገኛል!!!
የምርጫ ቦርድ ተብየው በመላ ሀገሪቱ ከከፈታቸው ሐምሳ ሽህ የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ሃያ አራት ሽህ አራት መቶ ያህሉ ወይም ግማሽ በግማሽ እስከአሁንም ድረስ ማለትም ካርድ የመውሰጃ ጊዜው ሊጠናቀቅ አንድ ሳምንት ብቻ እስከቀረው ጊዜ ድረስ ካርድ መስጠት ያልጀመሩ ወይም ጨርሶ ያልተከፈቱ ናቸው፡፡ ይሄ ምንን ያሳያል??? የአንድ ምርጫን በጣም ዝቅተኛ ደረጃን እንኳ ያላሟላ እጅግ አስቂኝ የቀልድ ምርጫ ሒደትና ክዋኔ ነው የተፈጸመው!!!
አገዛዙ በእንደዚህ ያሉ መሰናክሎች የሕዝቡን የመምረጥ ፍላጎት ስሜት የሚገልበት ምክንያት ሕዝቡ ካርድ ሳያወጣ ቢቀር ሕዝቡ ካርድ ለመውሰድና ለመምረጥ አለመፈለጉ አገዛዙን ተጠቃሚ የሚያደርግ የተሳሳተ ትርጉም ስለሚሰጠው ነው!!! ይሄ የተሳሳተ ትርጉም ምንድን ነው???
በአጭበርባሪው፣ በአባዩ፣ በነውረኛው፣ በውሸታሙ፣ በወፈፌው የወያኔ ኩሊ በአቶ ዐቢይ አሕመድ ስንት ተብሎለት የነበረውና በእንከን በመሞላቱ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት የውሸት ምርጫዎች የባሰ የሆነው ይሄ ምርጫ ፈጽሞ ነጻ፣ ፍትሐዊና ተአማኒ ሊሆን የማይችል መሆኑ ከሒደቱና በእጅጉ ከተበለሻሸው አሳዛኝ ክዋኔው አስቀድሞ በሚገባ ቢታወቅም ተቃዋሚ ፓርቲ ተብየዎች ይሄ ሁሉ ጉድ ምንም ሳይመስላቸው አሁንም በምርጫው እንደሚሳተፉ አረጋግጠው ባለበት ሁኔታ ሕዝቡ ግን ካርድ ለመውሰድና ለመምረጥ አለመፈለጉ በተለይም ለምዕራባውያኑ የሚሰጠው ትርጉም ሕዝቡ ለውጥ እንዳልፈለገና ያለው እንዲቀጥል እንደፈለገ የሚያስመስል የተሳሳተ ትርጉም ነው የሚሰጠው!!!
አገዛዙ በምርጫው ላይ የተለያየ መሰናክል እየፈጠረ ሕዝቡን ተስፋ አስቆርጦ የመምረጥ ፍላጎት ስሜቱን የሚገድልበትና ካርድ ለማውጣት የሚሔዱ ሰዎችንም የተለያየ ምክንያት እየፈጠረ በመመለስ ካርድ እንዳይወስዱ የሚያደርግበት ምክንያትም ሕዝቡ ካርድ አለማውጣቱ ይሄ ከላይ የገለጽኩላቹህ የተሳሳተ ትርጉም እንደሚሰጥለት ስለሚያውቅና ተጠቃሚ እንደሚያደርገውም ስለሚያውቅ ነው!!!
ተቃዋሚ ተብየዎች ብልጥ ከሆኑ ይሄንን የአገዛዙን ቁማር ማክሸፍ ወይም ማፍረስ የሚችሉት ከዚህ እነሱን በአጃቢነት ወይም በአሯሯጭነት ብቻ አሳትፎ የአገዛዙን አሸናፊነት ከሚያውጀው በእንከኖች የተሞላ አስቂኝ የውሸት ምርጫ ከወዲሁ እራሳቸውን ያገለሉ እንደሆነ ብቻ ነው!!!
በመሆኑም ተቃዋሚ ተብየዎች ሁሉም የአገዛዙ ቅጥረኞች ካልሆኑና ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ የሚታገሉ እውነተኛ ተቃዋሚዎች ካሉ አገዛዙ በምርጫው የፈጠራቸውን መሰናክሎችና ለማለፍ የማይቻሉ ጋሬጣዎችን በመግለጥ የይስሙላ ምርጫ ብሎ ለመጥራት እንኳ በማይበቃው አስቂኝ የቀልድ ምርጫ ለመሳተፍ አለመፍቀዳቸውንና ከዚህ በእንከኖች ከተሞላው ከውሸቱ ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን ከወዲሁ እየገለጡ ይውጡ!!!
ምርጫው የውሸት ምርጫ በሆነበት ሁኔታ ይሄንን ማድረግ የማይፈልግ ተቃዋሚ ፓርቲ ተብየ ካለ አትጠራጠሩ ይሄ ፓርቲ አገዛዙ ለአሯሯጭነት የፈጠረው ቅጥረኛ የአገዛዙ ፓርቲ ነው!!!
ከመጀመሪያው ጀምሮ አገዛዙ ለሯሯጭነት የፈጠራቸው ፓርቲዎች እንዳሉትና ተጠቃሚ ሲያደርጉት እንደቆዩ ታውቃላቹህ፡፡ አሁን በዚህ ዘመን እውነተኛ ለሕዝብ የሚታገል ፓርቲ ካለ በወያኔ/ኢሕአዴግ ወይም በብልጽግና አገዛዝ ዘመን ነጻ፣ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ ተደርጎ አገዛዙ ሥልጣን ያስረክባል ብሎ ማሰብ ዘበት መሆኑን ተረድቶ በአገዛዙ የይስሙላ ምርጫዎች እየተሳተፈ የኢትዮጵያ ሕዝብ የማይሆን ተስፋ እንዲጨብጥና ጊዜው በከንቱ እንዲባክን በዚህም የነጻነት ቀኑ እንዲርቅበት አያደርግም የአገዛዙ መጠቀሚያም አይሆንም!!!