>
5:18 pm - Tuesday June 14, 4433

"የ መጣንላቹ"   መድረስ! (ዮሀንስ አራጌ)

“የ መጣንላቹ”   መድረስ!

ዮሀንስ አራጌ

*…  ከአምስት ሲኖትራክ በላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በአፋር በኩል አድርጎ ወደ ከሚሴ ከተማ  ለመግባት እየመጣ መሆኑን የአይን መረጃዎች አድርሰውኛል። ከአጣዬና ካራ ቆሪ ጭፍጨፋና ቃጠሎ ቀጥሎ በይደር የተቀመጡት ማጄቴ፣ጂጉንቢ መስኖና መኮይ አካባቢ ሁሉም ስፍራዎች የሞት ጥላ አንዣቦባቸዋል!!!
 
“እየመጣን ነው”! 
 ታየ ደንደዓ    የኦሮሚያ ብልፅግና በይፋ ያሰለጠነውን፤ በሀገር ሀብት መከላከያ እንኳ ያልታጠቀውን ልዩ መሳሪያ ያስታጠቀውን ጦር ለወረራ አጣየ መድረሱን ሲነግረን “እየመጣን ነው”!የሚል መልዕክቱን ትናንት አጋርቶናል
 እውነት ነው ቃሉን ጠብቆ ትናንት ምሽት ጀምሮ የአጣየ ህዝብ ሲጨፈጭፉ አደሩ ዛሬ ከአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና የአካባቢው ሚሊሻ ጋ ሲታኮሱ ውለዋል። መድረሳቸውን ብቻ ሳይሆን ጦር መስበቃቸውን ያበሰሩን ኦቦ ታየ የአማራ ክልል መንግስት መዋቅርን  እንደ ትንኝም ሳይቆጥሩ ለሌላ እልቂት አታዘጋጁን ብለው ያንገራገሩበት ቃላቸው ተጠብቆ ያኔ 300 በላይ ንፁሀንን ገድለው ዛቻም ከጨመሩ በኋላ ተመልሰው ጦር ሰብቀው ዛሬ ከዚሁ ቁጥር ያላነሰ በመጨፍጨፍ አጣየን ተቆጣጥረዋል።
ንፁሀኑን መግደል ብቻ አይደለም ሀብት ንብረትና ቤታቸውን እያቃጠሉ ወረራውን ቀጥለዋል።
ዛሬም “ከበሮ በሰው እጅ ያምር ሲይዙት ያደናግር በማለት የጦራቸውን ሀይል ብሎም ጁንታው ህወሀትን የተበቀልን የጌታቸው አሰፋን ቤተሰብ ያጠፋን መንግስት ነን አሁንም የፈለገንን ምድር ለመጨበጥ የሚያቆመን የለም” በማለት እብሪታቸውን አፏሽከውብናል።
የአማራን ሀይል ሲሰብሩ መዋቅሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያዋቅሩ ድርጅታቸው ደንብ ላይ በመደንገግ ጠንካራ የህዝብ ልጆችን አስወግደዋል። ዮሀንስ ቧያለው ሲሾም እኮ ምክርቤቱ አያገባህም ተብሏል።
 ነፍጠኛውን አከርካሪውን ሰብረነዋል ሲሉ እኮ ብልፅግና ኦነጎች እነ ጀነራል አሳምነው ፅጌን እነ ዶ/ር አምባቸው መኮነንን እና ሌሎች ጀግኖችን በአደባባይ ገድለው እነ ገዱን አንዳርጋቸውን ከአመራር ሚናቸው አስወጥተው ፋኖን በመከላከያ ደብድበው ሌሎችን ጀግኖችንም አባረውና ከሚና አስወጥተው ከጨረሱ በኋላ ነበር።
ወለጋ መተከል አጣየ ከሚሴ ጉራፈርዳ ሻሸመኔ ነቀምት ወዘተ እኮ የተገደሉትን መቁጠር ያቅታል።
የአማራው ህልውና አደጋ ውስጥ የገባው ብልጽግና ሲደራጅ ነው። ያኔም ተናግረናል።
 
ዛሬ “መጣንላቹ! ዝም ካላላቹ ሌላ እልቂት ይከተላችኋል! ሰባብረናችኋል”ወዘተ እየተባልን የምንገራገረው፤ ጯሂ አጥተን የምንታረደው፤ በሞታችሁ አገር እናቆማለን የምንባለው ኢትዮጵያን የተቀማነው በፀራራ ፀሀይ እንጂ በአፍ ወለምታ ወይም በስውር አይደለም።
 
ዛሬን ሳይሆን ነገን የበለጠ እፈራዋለሁ። በእንቶ ፈንቶ ወሬ የስርዓቱ ፍቅር ውስጥ የተዘፈቁ አማራዎች ምስኪኑን ግን ራሱን የማይጥለውን አርሶ አደር ከበው እያዋከቡ እየደለሉ ገና ያሳርዱታል።ገና ቤተሰብ አልባ አገር አልባ ያደርጉታል።
 
እነ ዮሀንስ ቧያለው የብልጽግና ከፍተኛ አመራርነት ላይ ተቀምጠው አቅማቸውን እንደተነጠቁ እንደታፈኑ ህዝቡን ማዳን እንዳልቻሉና ህዝቡ በቻለው ሁሉ ተደራጅቶ ራሱን እንዲከላከል ተናግረዋል። ከዚህ በላይ ለእያንዳንዳችን በመመሪያ ካልወረደልን የሚል የሞኝ አስተሳሰብ ” ከብልጽግና ጋር ነገ ብርሀን ይሆናል” እያሉ ገና በማላዘን ውስጥ ያሉ የሞኝ ቀልድ እንዲሉ “አብይ ምን ያድርግ”ይሉሀል። አብይ የሚያደርገውንማ ሌላ ሰው ሳይነግርህ በአይንህ እያየህ ነው።
የአጣየ እልቂት ምናገባውና ዛሬ እሱ ስለመፅሀፍ ማስታወቂያ ይሰራል ቡድኖቹ በአማራው ላይ ጦር ያዘንቡልሀል።
Filed in: Amharic