በዱር በገደሉ እየተፈለገ የሚገኘው “ሕወሓት የጁንታ ቡድን” ከፍተኛ አመራር የሆነችው ፋና ሀጎስ ከተደበቀችበት በስንት ድካም ተገኝታ እነሆ በዛሬ ዕለት የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ሆና በብል[ጽ]ግና ተሹማለች። ፋና ሀጎስ ዛሬ በብል[ጽ]ግና ከመሾሟ በፊት “በጁንታው የሕወሓት ቡድን” የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሆና ተሹማ ሕወሓት ከመቀሌ እስኪባረር ድረስ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ነበረች። በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተብዮው ሕገ ወጥ የተባለውን “ምርጫ” ጁንታው ካካሄደ በኋላም ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካዔል የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ሆኖ “ሲሾም” ደብረ ጺዮንን ቃለ መሀላ ያስፈጸመችው ዛሬ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሆና በብል[ጽ]ግና የተሾመችው ፋና ሀጎስ ናት። ሕገ ወጥ በተባለው ምርጫ ደብረ ጽዮን ፕሬዝደንት እንዲሆን ቃለ መሀላ ያስፈጽመችውንና በሰሜን ዕዝ ላይ የተወሰደው “መብረቃዊ ጥቃት” እንዲፈጸም አብራ የወሰነችውን የሕወሓት ከፍተኛ ሹም ሕወሓትን ታገለግል ከነበረበት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትነት ብል[ጽ]ግናን ወደምታገለግልበት ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንትነት እያዛወሩ የወንጀል ባልደረቦቿን እነ ጌታቸው ረዳንና ደ/ጺዮን ገ/ሚካሄልን ለምን ይፈልጓቸዋል?