>

አስደንጋጭ ምስጢራዊ መረጃ:- በህግ ማስከበር ስም አማራ ላይ የታቀደ መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ኦፕሬሽን...!!!! (አህመድ ሱሌይማን)

አስደንጋጭ ምስጢራዊ መረጃ:-

በህግ ማስከበር ስም አማራ ላይ የታቀደ መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ኦፕሬሽን…!!!!
አህመድ ሱሌይማን

አብይ አህመድ በአመራርነት እየተሳተፈበት ያለው ቡድን በአማራ ሠራዊት ሕይወቱ የተረፈውን መከላከያን እና የኦሮሞ ልዩ ሀይልን ይዞ በብአዴን ይሁንታ ሰጪነት በአማራ ክልል ላይ ትግራይ ክልል ከተወሰደው በላይ የሆነ መጠነ ሰፊ የ “ሕግ ማስከበር” ሥራ ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ነው። 
የብአዴን ብልፅግና አመራሮች (ተመስገን ጥሩነህ፣ ደመቀ መኮንን፣ አገኘው ተሻገር፣ ገዱ አንዳርጋቸውና አጠቃላይ በፌዴራል ያሉ የብአዴን ባለስልጣናት) ከኦሮሚያ ብልፅግና አመራሮች በደረሳቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ መሠረት እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ በሰሜን ሸዋ ስለተፈፀመና እየተፈፀመ ስላለው ወረራና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አንዲትም ቃል አለመተንፈሳቸው ለመጪው የአብይ፣ የመከላከያና የኦሮሚያ ጥምር ጦር በአማራ ለሚያውጀው ጦርነት ይሁንታን ለመስጠታቸው ማሳይ ነው።
በዚህ ዘመቻ ከመከላከያ እና ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሌላ በጫካ ከኢትዮጲያ በተመዘበረ ገንዘብ በአብይ አህመድ በሁሉም ዘርፍ እንዲታጠቅ የሆነው ኦነግም (የጃል መሮ ኦነግ ሳይሆን የአብይ/ለማ ኦነግ ሸኔ) “በሕግ ማስከበሩ” ተሳታፊ እንዲሆንና እንዲያግዝ ስምምነት ተደርሷል።
አማራ የሆኑ የመከላከያ መሪዎችና ጄኔራሎች ከወዲሁ በሚዲያም ጭምር እንዳይወጡና በመዋቅሩ በየበረሃው ከመዋጋትና ከማዋጋት በዘለለ ምንም ተሳትፎ እንዳይኖራቸው ሆነው የተገለሉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በመጪው በአማራ ክልል በሚደረገው “የሕግ ማስከበር” ዘመቻ ‘ለምን’ ብለው የሚጠይቁና ‘እምቢ’ ሊሉ የሚችሉ ከወዲሁ ተለይተው እንዲመቱና እንዲገደሉ ይሆናሉ ተብሏል። የተቀሩትን በትግራይ ባለው “የሕግ ማስከበር” ሥራ ግዳጅና ሀላፊነትን በመስጠት በአማራ ክልል በሚደረገው ዘመቻ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ታቅዷል።
በምትካቸው እንደ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላና ጄኔራል ባጫ ደበሌ ያሉ የኦሮሞ ጄኔራሎች፣ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል መኮንኖች፣ የጫካ “ጄኔራሎች” እና non Amhara የሆኑ ወታደራዊ አመራሮች የሚሳተፉበት ለማድረግ ታስቧል።
ይህን ወረራና ጭፍጨፋ የትግራይ ዋና ኦፕሬሽንን ለማጠናቀቅ የወሰደውን የጊዜ ገደብ ታሳቢ አድርጎ ለመጨረስ የታሰበው ከምርጫ በፊት በሁለትና በሦስት ወር ገደማ ሲሆን ከሰሞኑ በሰሜን ሸዋ ምናልባትም በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀንን የገደለውና ከተሞችን ያወደመው የአብይ አህመድ ወረራና ጭፍጨፋ ለመጪው ዘመቻ እንደ መንደርደሪያ የሆነ የዚሁ ኦፕሬሽን አካል መሆኑ ታውቋል።
የዚህ እኩይ ዘመቻ የመጀመሪያ ኢላማ ለማድረግ የታቀደው አጠቃላይ ወሎን ሲሆን፣ ኮምቦልቻና ደሴን ደብድቦና ነዋሪውን ገድሎ በማለፍ በወልዲያ ተመሳሳይ ተግባር በመፈፀም እስከ ራያ ቆቦ ትግራይ ድንበር ድረስ ጦርነት ከፍቶ በወረራ ለመያዝ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
በመተከል በኩል ባለው የኮማንድ ፖስት ኦሮሞ ጄኔራሎች መሪነት በዛ ያለው መከላከያ በወለጋ አድርጎ የሚገባለትንና ላለፉት ሦስት አመታት ንፁሀንን በገጀራና ስለት ሲዘለዝል የቆየው የአብይ ኦነግ ሸኔን ጦር ይዞ ወደ ጎጃም በመዝመት በሁለንተናዊ መልኩ አገርን በማጥፋትና ህዝብን በመግደል ላይ ታሳቢ ያደረገን ወረራ ጎጃም ላይ ለመፈፀም አቅዷል።
በጎንደር በኩል ጎንደርን ለመምታት የጠነሰሱት ፕላን ውሀ በልቶባቸዋል። ዕቅዳቸው በዛ በኩል አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ለዚህም ምክኒያቱ ከዚህ በፊት አብይ አህመድ ከኤርትራ ጦር ጋር በትብብር ከትግራይ ጦርነት ምላሽ በጎንደር አማራ ላይ ጦርነት ለመክፈት አስቦ የነበረ ቢሆንም፣ በትግራይ ክልል በኤርትራ ጣልቃ ገብነት ምክኒያት ያልጠበቀው ውግዘት ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የደረሰበት በመሆኑ፣ የኤርትራን ወታደሮች በኢትዮጲያ ግዛት ለዳግም ወረራ በአማራ ላይ ለመጠቀም የሚችልበትን አቅም አሳጥቶታል። በመሆኑም የጎንደር ጉዳይ የኤርትራ ጦር የማይሳተፍበት የሚሆን ስለሆነ ተወሳስቧል። ይህ ማለት ግን ሱዳን ድንበር ጥሳ ወደ ውስጥ እንድትገፋና ተጨማሪ የጎንደር መሬቶችን እንድትቆጣጠር አያስደርግም ማለት አይደለም። ይሄንን ከማድረግ ወደኋላ አይልም። በዛም ጎንደርን ማስጨነቅና ለሌላው ድምፅ እንዳትሆን አድርጎ መወጠር የቀረው ብቸኛ ስትራቴጂው በመሆኑ በጎንደር ያንን ለማድረግ አስቧል። ከዛ ባለፈ እንደ አዲስ ህወሀትንም በሱዳን በኩል ወደ ጎንደር ዘልቃ እንድትገባ በማድረግ ጎንደርን ለመበጥበጥ ሀሳብ አለ።
ትግሬውን እንደሰባበርነው ሁሉ አማራውንም በተመሳሳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በ’ሕግ ማስከበር’ ግዛቶቹን ይዘን የገደልነውን ገድለን የተቀረውን ደግሞ እንዲበተንና እንዲሰደድ አድርገን ኢትዮጲያን በአማራ መቃብር ላይ እንደ አዲስ በብልፅግና በአባ ገዳና በኦሮሙማ ቅርፅ እንገነባለን በሚለው መስመር እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ናቸው። በሰሜን ሸዋ ከተሞችና ሕዝብ ላይ የተጠቀሙት ከተማን ሙሉ በሙሉ በእሳት በማያያዝ ነዋሪዎችን ሳይለዩ መግደልና ከቦታው ማፈናቀልን ለመጪው በሰፊው የአማራ ግዛት ለሚያደርጉት ኦፕሬሽን እንደ ግብአት ለመጠቀም ወጥነዋል።
ይህ ሁሉ ሲጠናቀቅ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሰፈረውን የኦሮሚያ ልዩ ሀይልን በመጠቀም አዲስ አበባ ደብረብርሃንና ዙሪያውን መምታትና ማንበርከክ የዘመቻው ማጠናቀቂያ ግብ ሆኖ ተወስዷል።
ከዚም በኋላ ወደ ተቀሩት የኢትዮጲያ ግዛቶች (ደቡብ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ) በመዘዋወርና ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ጅማ፣ ናዝሬት፣ ጋምቤላ እና ጠቅላላ ደቡብ እንደ አስፈላጊነቱ መጠነኛ ኦፕሬሽን በማድረግ በኦሮሙማ/አባገዳ ስርዓት መሬት ነጠቃና ሕዝብ ፍንቀላ በስፋት ታስቧል።
በብዛት አማራ በሚኖርበት መተከልና አካባቢው እንደተደረገው በሰሜን ሸዋ አማራ ግዛቶችም በኮማንድ ፖስት ስም ኦሮሞ ጄኔራሎችን በመሾም ወረራና ግድያውን ያስቆሙ መስለው የአብይ አህመድ ኦነግ ሸኔን ዳግም በማሰባሰብና በማስታጠቅ ከእስካሁኑ በባሰ መልኩ ፍጅታቸውን ወደ ኮምቦልቻና ደሴ ለማስፋትም አቅደዋል።
በእስካሁኑ የአማራ ፍጅትና ስደት ሁሉ ውስጥ ከአብይ አህመድ ኦነግ ሸኔ ጋር በዋናነት እየተሳተፈ ያለው የላይኛው የብአዴን አመራር አባላት ሲሆኑ፣ በመጪው ዘመቻም ሕዝብንና አገርን ለማስፈጀት ከኦሮሙማ ጋር ተማምሎ በመስራት ላይ ይገኛል።
ይህን በሕዝብና አገራችን እየመጣ ያለውን የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ ታሳቢ በማድረግ ከምንግዜውም በላይ በአደጋው መጠን ልክ መዘጋጀት ያስፈልጋል። አካባቢን በራስ ተነሳሽነት በመደራጀት ከማንኛውም አደጋ መጠበቅ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።
የአብይ አህመድ ሠራዊት ላለፉት ሦስት አመታት ባላባራ መልኩ ሕዝብን ሲጨፈጭፍና የዘር ፍጅት ሲፈፅም መቆየቱን ለአፍታ መዘንጋት ከባድ ዋጋ ያስከፍላል።
ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ መውጫ መንገድ አለ። ይህም ሠላማዊና ቀጣይነት ያለው ሕዝባዊ ትግል ማድረግ ነው። እምቢ ማለት በቃኝ ማለት ነው። የአብይ አህመድ ታጣቂ ሠራዊት ከሳምንት ጀምሮ በትንሹም አማራው ለህልውናው እና ሕይወቱን ለማዳን በውጭም በውስጥም እያሳየ የመጣው መተባበርና እምቢተኝነት ከወዲሁ አገር የማፍረስ ውጥኑን እያጋለጠና እያበላሸበት ይገኛል። ቢሆንም ግን ጭፍጨፋና ግድያውን ወረራና እልቂቱን እጅግ በከፋ መልኩ ንፁሀን ላይ አበርትቶ ቀጥሏል። በመሆኑም በዛው ልክ አማራው አገር ወዳድ ኢትዮጲያዊያን እና አጠቃላይ ሕዝብ የአደጋውን መጠን ተረድቶ ሠላማዊ ትግላቸውንና እምቢተኝነታቸውን ማበርታት አለባቸው።
በመጨረሻም፣ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ይሄ እንደሚሆን በትክክል assess አድርጎና አንብቦ “ዛሬ ያለንበት ይህ ወቅት ከዛሬ 500 አመት በፊት (በ16ኛው ክ ዘመን የኦሮሞ ወረራ) ከነበርንበት በላይ በጠላት የተከበብንበት ወቅት ነው” ያለው መጪው ጊዜ ምና ያህል ለሕዝባችን የከፋ መሆኑን ተረድቶ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም እላለሁ።
ሕዝብ ሁሌም ያሸንፋል!
Filed in: Amharic