>

የአማራን ዘር ማጥፋት ከማውገዝም በላይ ለሕዝባዊ እምቢተኝነት አየተዘጋጀ ነው...!!! (አሥራት ቲቪ)

የአማራን ዘር ማጥፋት ከማውገዝም በላይ ለሕዝባዊ እምቢተኝነት አየተዘጋጀ ነው…!!!

አሥራት ቲቪ

ሚያዚያ 12/ 2013 ዓ/ም
ወግድ
ቪላ እየገነባህ- ጎጆዬን አታንድድ❗️
ዞር በል
ልጅህን እየሳምክ- ልጆቼን አትግደል❗️
እንቢ
አገር አፍራሽ እንጂ- አይደለህም ገንቢ❗️
ክላልኝ
ሕፃናት እንደ እትብት- አፈር ማልበስ በቃኝ፡፡
 የጣናዋ ፈርጥ➖ ባሕር ዳር
ደብረማርቆስ፣ ወልድያ፣ ደሴ፣ ባሕርዳር፣ ኃይቅ፣ ኮምቦልቻ ሕዝብ በነቂስ በመውጣት ተቃውሟል!
ግፍ ጭቆና በደል ግድያና የዘር ፍጅት  የተደራረበበትና  የታወጀበት የአማራ ህዝብ ከእለት ወደ እለት ይቆማል  ሲባል እየከረረና ይባስ ብሎም መንግስታዊ ሽፋን እየተሰጠው በመምጣቱ ነው ህዝባዊ ቁጣው የበረታው፡፡
በዛሬው እለት በወኔ በእልህና በቁጭት በተለያዩ የአማራ ከተሞች የ ሞት ይብቃን እንዲሁም የዘር ፈጅት የንፁህ አማራ ጅምላ ጭፍጨፋና ማፈናቀል  ይቁም  የሚሉ ህዝባዊ ጥያቄዎች እየተነሱ ሲሆን፣ አሥራት ቁጣው እየተኪያሄደ ባለባቸው ከተሞች ከሚገኙ አስተባባሪዎች ጋር አጭያጭር የስልክ ቆይታዎችን አድርጓል፡፡
ደብረማርቆስ ከ 2 ቀናት በፊት ጀምሮ የሚደረገውን የደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች  የምግብ አድማና የዘር ጭፍጨፋ ተቃውሞ ለማስቆም የዞኑና የከተማው ገዥ መንግስት ተኩስ ለመክፈት በመሞከሩ ቁጣው የበለጠ ተቀጣጥሎ የማርቆስ ከተማን ህዝብ በነቂስ ወደ አደባባይ ለተቃውሞ እያዘመተ ይገኛል፡፡
በሰ/ወሎ ዞን  ወልድያና በክልሉ ዋና ከተማ  ባህርዳርም ተመሳሳይ ህዝባዊ ቁጣና ተቃውሞዎች ከማለዳ ጀምሮ የተነሱ ሲሆን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወደ አደባባይ በመውጣት ድምፁን እያሰማ እንደሚገኝ ከ አሥራት ጋር ቆይታ ያደረጉ ወጣቶች ተናግረዋል፡፡
ትላንት  የዳሰስነው የደሴው ህዝባዊ ተቃውሞ በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን ዛሬም ለ 2ኛ ቀን ቀጥሏል፡፡
አሥራት የክልሉ መንግስት በኮሚኒኬሽኑ በኩል ችግሮችን ለመፍታት እየሠራን ነው የሚል የተላዘበ መረጃ እያወጣ መሆኑን ተገንዝቦ ከህዝባዊ ቁጣው  ወቅታዊ ጉዳይ ጋር በማያያዝ ለማቅረብ ወደ  አማራ ክልል መንግስት ተደጋጋሚ የቃለ መጠይቅ ሙከራ እያደረገ ነው፡፡
Filed in: Amharic