>
5:13 pm - Tuesday April 18, 3550

ይዋል ይደር እንጂ ፍጅቱ እንደማይቀርለት ያወቀው አማራ ከዘመናት እንቅልፉ ነቅቷል...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ይዋል ይደር እንጂ ፍጅቱ እንደማይቀርለት ያወቀው አማራ ከዘመናት እንቅልፉ ነቅቷል…!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

*…. ወልድያ  በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እያወገዘች ትገኛለች~ከመልዕክቶች መካከል~
 
-አማራ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እንጂ ስጋት ሆኖ አያውቅም!
 
-መርጠን ሳንወለድ ተመርጠን የሞትንው ካልታረመ አረም ጋር አብረን ተገኝተን ነው!
 
-በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት በአስቸኳይ ይቁም!
 
-አብይ አሕመድ በዘር ማጥፋት ወንጀል በአለምአቀፍ ህግ ይጠይቁልን!
 
-የኦሮሞ ልዩ ዞን በአስቸኳይ ይፍረስ!
-አብይ አሕመድ መጨረሻህን እንደ ጋዳፊ እናደርገዋለን
 
-የታገልነው ህውሓትን አስወግደን ኦነግን ለመተካት አይደለም!
 
-ጀኔራል አሳምነው ፅጌ፣ ዶ/ር አምባቸው፣ አቶ ምግባሩ ከበደ፣ የተገደሉት አማራ ተቆርቋሪ እንዲያጣና መሪ እንዳይኖረው በኦነጉ አብይ አሕመድ ነው!
 
-አማራ አልተሰበረም፤ አይሰበርም !
 
-ግፍና መከራ የተሸከምንበት ትክሻችን ዝሏል በቃን!
 
-በአማራ ደም ኢትዮጵያ አትቆምም!
 
… በዘመነ ህወሓት በቃና ዘገሊላ ዕለት ህጻን አዋቂ ሳትል ወያኔ አግአዚ ጦሯን ልካ በስናይፐር አናት አናታቸውን በርቅሳ ዐማሮችን በታቦተ ሚካኤል ደፋች። ታቦተ ሕጉን ባከበሩ ካህናት ላይም አስለቃስ ጭስ ተኩሳ ለተዋሕዶም፣ ለዐማራም ያላትን ንቀት አሳየች። ያ ሁሉ ሲሆን መቀሌም፣ አዲግራትና ዓድዋ የነበሩ ትግሬዎች ልክ አይደለም ብለው ህወሓትን አልተቃወሙም ነበር። ዐማራ ሲያለቅስ ህወሓት ከማስለቀስ አልፋ ትጨፍር ነበር። ዛሬ ግን ሁሉም ለቀስተኛ ሆነ።
… በመላ ኢትዮጵያ ዐማራ በአፍቃሬ ኦነጉ፣ በዐቢይ አሕመድ ሲታረድ፣ ሲዘረፍ፣ ሲሰቃይ፣ ሃብት ንብረቱ ሲወድም መላው የኦሮሞ ህዝብ ከዳር ቆሞ ያያል። ይታዘባል። ልጆቹ በዐማራ ላይ በሚፈጽሙት ግፍ የተስማማም መስሏል። በሴቶች ማኅጸን እንጨት ሲገባ፣ ልጆቹ የደረሰች የዐማራ እርጉዝ በካራ ሸልቅቀው ጽንስ አውጥተው ሲገድሉ እያዩ እየሰሙ ዝም ጭጭ ብለዋል። አቃፊ የሚባለው፣ የዲሞክራሲ ምሳሌ ነው እየተባለ በሌለ ግብሩ የሚለፈፍለት አባ ገዳ የሚባለው የኦሮሞ ሽማግሌ ስብስብም ዐማራን ከምድረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት ለተነሣው ኃይላቸው ሽፋን በመስጠት ግፉበት አይነት ዝምታን መርጠዋል።
… የመንግሥት ሚዲያ የዐማራን ሞት አይዘግብም። አጣዬ እንደ ሶሪያ ወድማ እነሱ የአራጅ አቢይን መቀመጫ እየተከተሉ ሌላ ነው የሚዘግቡት። ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሩብ ሚልየን ዐማራ በመሃል ሃገር ከተማው ወድሞ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታርደው፣ ትንፍሽ አይሉም። ዐማራ ሞተ ብሎ ማውራት ሃገር ያፈርሳል ይላሉ። አናታችሁ ይፍረስ አቦ።
… የሆነው ሆኖ አሁን ዐማራው የነቃ ይመስላል። ሞቱ እንደማይቀርለት ያወቀው ዐማራ የባነነ ይመስላል። ገዳዩን ለይቶ አውቋል። ዐብይ ከነ ካቢኔው በዐማራ መደመስስ፣ መጨፍጨፍ እንደወሰነ ተረድቷል። ፓርላማው ዐማራን እንደዜጋ እንደማይቆጥርም ተመልክቷል። እናም ዐማራው ወያኔን በታገለበት መንገድ ይሄንንም አራጅ ቡድን ለመታገል የቆረጠ መስሏል።
… ከትናንት ወዲያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የለኮሱት የትግል ችቦ ትናንት ደሴ፣ ወልድያ፣ ደብረ ማርቆስ ያቀጣጠሉት ሲሆን። ዛሬ ደግሞ ወልድያ እና ባህርዳር ተቀብለው አደባባይ ወጥተዋል። ገዳዩ ዐቢይ አሕመድም የጊዜ ጉዳይ እንጂ የንፁሐን ደም የእጁን ይሰጠዋል።
Filed in: Amharic