>

ከነገው ብልጽግና የዛሬ ሰላም የበለጠ ያሳስባል...!!! (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ከነገው ብልጽግና የዛሬ ሰላም የበለጠ ያሳስባል…!!!

ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
.
.
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም የለም፡፡ ሰላም የለም ማለት የመኖር ዋስትና የለም ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዛሬን እንዳላየና እንዳልሰማ ችላ ብሎ፣ የበለጸገ ነገን በተሰፋ ማሰብ ለዛሬ ሽንፈት እጅ መስጠት ነው፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ላለው እልቂት መንግስት ትኩረት አልሰጠም፤ ችግሩን አልተጋፈጠም፡፡ እየሸሸው ነው፡፡ የዛሬን ችግር ሸሽቶ ነገ ሰላምና ብልጽግና አይገኝም፡፡
ከነገው ብልጽግና የዛሬ ሰላም የበለጠ ያሳስባል፡፡ ‹‹ሀገራችን ጦርነት ውስጥ ናት፤ እንደ ሀገር ህልውናችን አደጋ ላይ ነው›› የሚባለው ስንት ሰው ሲሞት፣ ስንት ሰው ሲሰደድ፣ ስንት ቤት፣ ስንት መንደር፣ ስንት ከተማ ሲቃጠል ነው?
ለመልማት፣ ለመበልጸግ ሰላም ያስፈልጋል! ከነገ ልማትና ብልጽግና በላይ የዛሬ ሰላም ያሳስባል! ያለብልጽግና፣ ያለልማት በድህነት ኖረናል፡፡ ያለሰላም በድህነትም አሸልቦ መንቃት አይቻልም፡፡ ያልነበረን ብልጽግና ላይ ለመድረስ፣ አስቀድሞ የነበረን ሰላም ሊመለስ ይገባል!
Filed in: Amharic