>

ሴራውን ገለጥለጥ ለማድረግ ያህል...!!! (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

ሴራውን ገለጥለጥ ለማድረግ ያህል…!!!

ብርሀኑ ተክለያሬድ

እነ ታዬ ደንደአ ቤተክርስቲያን “አብይ አህመድና ግራኝ አህመድ አንድ ናቸው” ብላ ስትሰብክ ነበር በማለት በቤተክርስቲያን ላይ ጦርነት እያወጁ ነው። ነገሩ ከታዛዡ ታዬ በላይ ከአዛዦቹ የሚመዘዝ ነው
 ኦሮሙማ በቤተክርስቲያን ላይ እጁን አስረዝሞ የማፍረስ አባዜውን ከዘረጋ ቆይቷል። እውነቱ በገሐድ የሚታይ ቢሆንም ከልክ ያለፉ ብልግናዎችን በሂደት እንገላልጣቸዋለን። ለመነሻ ያህል ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ
-የቅዱስ ፓትርያርኩን የጥበቃ ሀላፊ አስሮ ፓትርያርኩን በሰላይ ያስከበባቸውና የፈለጉትን ሰው እንዳያገኙ የከለከላቸው ማነው?
-በፓትርያርኩ ሊሰጡ የነበሩ 2 መግለጫዎችን ፖሊስ ልኮ የከለከለው ማነው?
-ጥቅምት 26 ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፓትርያርኩ ቢሮ ድረስ ሔደው አቡነ ማትያስን ከፍ ዝቅ አድርገው በሀይለ ቃል የተናገሯቸው በየቱ ስልጣን ነው?
-ቅዱስ ፓትርያርኩ ለeotc ቴሌቪዥን የሰጡት ከ1 ሰአት በላይ ቃለመጠይቅ እንዳይተላለፍ በማን ተከለከለ? ከቀናት በፊት በቴሌቪዥን በሚተላለፍ ፕርግራም የሰበኩት ስብከትስ ለምን ታገደ?
-(ስማቸው ይቆየንና)ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ “ቤተክርስቲያን ሊቃጠል ነው ተነሱ ብሎ አነሳስቷል”ብለው ከመጋረጃ ጀርባ  ለመመስከር 3 ሰዎችን የመለመለው ማነው?
እግር በእግር እየተከታተልን ነው በቅርቡ ሁሉም ግልጥልጥ እያለ ይመጣል።
ከቤተክርስቲያን እጃችሁን አንሱ!!!
Filed in: Amharic