>
5:26 pm - Sunday September 17, 4851

አታምጣው ስለው፣ አምጥቶ ከመረው! (አሰፋ ሀይሉ)

አታምጣው ስለው፣ አምጥቶ ከመረው!

አሰፋ ሀይሉ

 

የወያኔ ለዘመናት በነፍጠኛ ጭቆና ሥር የኖረው ብሔር ብሔረሰብ… የሚል የጥላቻ ትርክት፣ የኦነግ የነፍጠኛ አማራና የምኒልክ ቅኝ ተገዢዎች ሆነን ኖረናል… የሚል ሃሳይ ትርክት፣ የወያኔንና የኦነግን ማኒፌስቶ ያዳቀለና ላለፉት 30 ዓመታት በወያኔ-ኢህአዴግ መንግሥት ህጋዊና ተቋማዊ ቅቡልነት አግኝቶ የገዘፈው የኦህዴድ ፀረ-አማራ ትርክት፣ አብይ አህመድ ነፍጠኞች ኦሮሞን በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በፖለቲካ ህልውናውን ለማጥፋት በቅኝ ግዛት ሥር አውለው ከባድ ግፍ ፈጽመውብናል ብሎ ሲናገር የተቀረጸው ማስረጃ፣ ከታምራት ላይኔ እስከ ደመቀ መኮንን ለዚሁ ሃሳይ የጥላቻ ትርክት የተቸረው ይሁንታና ማበረታታት – ይኸው አሁን ሥጋ ለብሶ፣ ጥርስ አግጦ – መንግሥትን እመራለሁ ከሚሉ ቂምበቀላችንን እንወጣለን ብለው በተሰለፉ የባርነት አስተሳሰብ ልክፍተኞች፣ ደም አፍሳሾች፣ አራጆችና የጥላቻ ሰባቂዎች አፍ እንዲህ በግላጭ እየተነገረ ነው፡፡ 
 
እኛም ኦሮሙማው ያነገበውን የጥላቻ ክምር፣ ስልቱም ሆነ ግቡ ይህ እና ይህ መሆኑን ደጋግመን ተናግረናል፡፡ የምታደርጉት ሁሉ ነገር ይህንኑ በደማቁ ይናገራልኮ ቃላት ማባከን አያስፈልጋችሁም ነበር! እንዲህ በግልጥ ስታምኑ ግን ጥሩ ነው! የኦሮሙማው አጀንዳ በውሸት ትርክት ላይ የተመሠረተ ደም የጠማው ቂም በቀል ብቻ ነው፡፡ በቂም በቀልና በጥላቻችሁ ግዝፈት የሒትለርን ናዚዎች ታስንቃላችሁ፡፡ ባጠለቃችሁት የዘረኝነት ካባና ለራሳችሁ በሰጣችሁት የውሸት ነጻ አውጪነት ሥፍራ የሙሶሎኒን ፋሺስቶች ታስከነዳላችሁ፡፡ ግፋችሁ ሞልቶ ፈሷል፡፡ ጥላቻችሁ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር የሰውን ልጅ ነፍስ እየሰለቀጠ ነው፡፡ ሁሉ ነገራችሁ ከነጥላቻችሁ የምትቀበሩበት ወቅት እንደደረሰ ይመሠክራል፡፡ 
 
ቂም በቀላችንን ለመወጣት የኢትዮጵያን ሕዝብ እንድንጠብቅበት የተሰጠንን የመንግሥት መከላከያ ሠራዊት አሰልፈን ሶማሊዎችን የወጋነውና ያስገበርነው እኛ አማራዎች ነን፡፡ አንድ ሚሊዮን ጌዲዮዎችን ያፈናቀልነው እኛ አማራዎች ነን፡፡ የሲዳማዎችን ደም ያፈሰስነው እኛ አማራዎች ነን፡፡ ሰው ዘቅዝቀን በአደባባይ የሰቀልነው እኛ አማራዎች ነን፡፡ ሻሸመኔን ዝዋይን ያነደድነው እኛ አማራዎች ነን፡፡ የጅማው አባ ጂፋር መንፈስ ባርያ ፈንጋዮች የነበረ ማን እነደሆነ ይመሰክርብናል፡፡ የከፋው ንጉሥ ሴሮቾ፣ የወላይታው ንጉሥ ጦና፣ የወለጋ፣ የባሌ ነገሥታትና ገዢዎች ሁሉ ነፍጠኛ አማሮች ነበሩ፡፡ ከጥንት ጀምሮ በነፍጠኝነት ሀገር ምድሩን ያስተዳደርነው እኛ አማሮች ነን፡፡ ውሸት፣ ውሸት፣ ውሸት፣ የውሃ ላይ ኩበቶች ናችሁ፡፡ በውሸት ላይ የቆማችሁ፣ እውነት የሚያንገፈግፋችሁ፣ እውነት የሚያርዳችሁ የውሸት ነጻ አውጪዎች፡፡ 
 
ሌላም ውሸት እየፈጠራችሁ ጨምሩበት፡፡ ቅኝ ገዢዎቻችሁና የባንዲራችሁ ጌቶች የፈጠሩላችሁ ሌላም የውሸት ታሪክ ሞልቶላችኋል፡፡ የውሸት ታሪካችሁን በመደጋገም እውነት አታደርጉትም፡፡ የገነባችሁት የጥላቻ ተራራ ሰው ክቡሩን የሰውን ልጅ ከማረድ፣ የንጹሃንን ደም ከማፍሰስ፣ ለፍቶ አዳሪውን ሕዝብ ከማፈናቀልና ከማሰቃየት፣ የሀገርና የህዝብ ንብረት ከማውደም፣ እና በመጨረሻ እንወክልሃለን የምትሉትን ለዘመናት በሠላም በንጹህ ወዙ የኖረውን የኦሮሞን ሕዝብ ከማስጠላት፣ ከማዋረድና ከማስጨረስ የዘለለ ፋይዳ አያመጣላችሁም፡፡ 
 
ማንነታችሁን ግን እንዲህ ግለጡልን፡፡ እኛንም ያሰባስበናል፡፡ ያልተገለጠልን ይገለጥልናል፡፡ ያልገባን በደንብ ይገባናል፡፡ ገና ከሩቅም ከቅርብም የሚያያችሁ በጥላቻችሁና በክፋታችሁ ብዛት በቀላሉ አይቶ እስኪያውቃችሁ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያውያን ማንነታችሁ፣ እርቃናችሁን እስክትቀሩ ይጋለጣል! ከትናንት ይልቅ ዛሬ ማንነታችሁንና ያነገባችሁትን የጥላቻ ስንቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ አውቆባችኋል፡፡ ከዛሬ ይልቅ ነገ ደግሞ ይበልጡን እርቃናችሁን ትቀራላችሁ፡፡ ኢትዮጵያውያንን ሰልቅጣችሁ፣ የኢትዮጵያውያንን ደም ሰልቅጣችሁ፣ ታታሪውንና ቀናውን የኦሮሞ ህዝብ በነጻነት ስም ለመከራና ለእልቂት ዳርጋችሁ፣ እናቋቁማታለን ብላችሁ የምታልሟትን የግብጽን ባንዲራ ስታውለበልቡላት የኖራችኋትን ታላቋን ህልመኛዋን የምኞት መንግሥት – ኦሮሚያችሁን – መቼም አታገኟትም!
 
ኢትዮጵያን አፈራርሰን በኢትዮጵያ ፍራሽ ላይ ነጻዋን የኦሮሚያ አገር እንመሠርታለን ብላችሁ በሕዝባችን ደም የምትቆምሩት እናንተ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ የመምራት የህሊና ብቃት የላችሁም፡፡ ኢትዮጵያን የሚረግም፣ ኢትዮጵያውያንን የሚያርድና የሚያቃጥል፣ ኢትዮጵያውያንን ወግቶና ሰልቦ ቂሙ አልወጣ፣ አልበቃ ያለው እንደ እናንተ ያለው የጥላቻ ጎተራ፣ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድር አይችልም፡፡ ትውልድን ሊያሻግር አይችልም፡፡ ከዚህ በላይ በምላስ እየደለላችሁ፣ በተግባር ኢትዮጵያን እያፈራረሳችሁ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ የናዚ ካምፕ እየገነባችሁ፣ በማደናገር ልትቀጥሉ አትችሉም፡፡ ሁሉም ዓላማችሁንና ማንነታችሁን በግልጽ እያወቀባችሁ ነው፡፡ 
 
እናንተ በዚህ አያያዛችሁ ከእንግዲህ ወዲያ እንኳን የኢትዮጵያን ሕዝብ፣ የመዋዕለ ሕጻናት እምቦቃቅላዎችን ማታለል አትችሉም፡፡ ጨፍኑ እናሞኛችሁ ስትሉ፣ እኛ ደሞ ሀገርን በዘረኛ ጥላቻችሁ አንቀይርም እንላችኋለን፡፡ ከአሸባሪ ጋር በሀገር ጉዳይ አንደራደርም እንላችኋለን፡፡ ሽብራችሁ ማብቂያው ተቃርቧል፡፡ እስከዚያ ማንነታችሁን እንዲህ እየገለጻችሁ አስረዱን፡፡ ታዬ ደንደአ አረደ፡፡ መልካም የጥላቻ ጊዜ ይሁንልህ፡፡  
 
ኢትዮጵያውያን ያሸንፋሉ!
 
የጥላቻ ጎሳሚ ዘረኞች ይወድማሉ!       
 
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
 
_________________________
ማስታወሻ፡- ከላይ የቀረበው ታዬ ደንደአ አረደ አምጥቶ በከመረው የጥላቻ መግለጫ ላይ የቀረበ የግል አስተያየቴ ሲሆን፣ ያያያዝኩት ምስል ደግሞ የታዬ ደንደአ አረደ መግለጫ ነው፡
Filed in: Amharic