ሰልፍ በራሱ ብቻ ግብ አይደለም….!!!
መስከረም አበራ
መሰለፍ አማራም ሲገረፍ የሚያመው፣ሲያመው የሚቆጣ መሆኑን ማሳያ ብቻ ነው። ከሁሉም በላይ አማራ የለም” ለሚሉ ከሃዲያን “አለን ያውም ተቆጥተን!” የሚል ጥሩ መልዕክት ይልካል።መኖሩን ያሳወቀ ህዝብ ደግሞ ሰብዓዊነቱን የሚመጥን ክብርን መጠየቅ ይችላል።
ሆኖም ሰልፍ በራሱ ግብ አይደለም። መሰለፍ የታገቱ እህት ወንድሞቻችንን ጉዳይ መንግስት ነገሬ ብሎ እንዲይዘው አላደረገም። የአማራ ህዝብ ላይ ያንዣበበው አደጋ በመሰለፍ ያውም በአንድ ቀን ሰልፍ የሚቃለል አይደለም። አንድ ቀን ተሰልፈን ወደቤታችን መመለሳችንን ሃፍረተ-ቢሱ መንግስት እንዴውም ለዲሞክራትነቱ ምስክር ያደርገዋል እንጅ ከቤት ገፍቶ ጎዳና ያፈሰሰን ብሶታችን አያሳስበውም።
ስለዚህ ከሰልፍ ባሻገር የተለያዩ ሰላማዊ የትግል ስልቶችን ማከታተል ያስፈልጋል(ለምሳሌ የክልልም ሆነ የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ እንዲያደርግ የምንፈልገውን እርምጃ በመጥቀስ ይህ እስኪደረግ ድረስ ስራ የማቆም አድማ ፣ቤት የመቀመጥ አድማ ማድረግ)።
በስተመጨረሻም ዛሬ የተደረጉ ሰልፎች ከጨዋነታቸው ጀምሮ ሁለመናቸው እርካታን እንደሰጠኝ፣ተስፋ መቁረጤን እንዳከመው መግለፅ እፈልጋለሁ! በሰልፎቹ የተሳተፋችሁ ሁሉ ክብር ይግባችሁ !