>

ግብጽና ሱዳን ማንን እየተጠቀሙ ነው ኢትዮጵያን ሲያዳክሙ የኖሩት? አማራን ወይስ ኦሮሞ ነን የሚሉትን?  (አቻምየለህ ታምሩ)

ግብጽና ሱዳን ማንን እየተጠቀሙ ነው ኢትዮጵያን ሲያዳክሙ የኖሩት? አማራን ወይስ ኦሮሞ ነን የሚሉትን? 

 
አቻምየለህ ታምሩ

 

የዐቢይ አሕመድ ቃል አቀባይ የሆነው የኦሮሙማው አስኳድ ታዬ ደንደአ እነሱ ሲያደርጉ  የኖሩትን አማራውም የሚያደርግ እየመሰለው መላው አማራ በዐቢይ አሕመድ የታወጀበትን የጅምላ ፍጅትና የዘር ማጥፋት በመቃወም የሚያደርገውን የኅልውና ተጋድሎ ከግብጽና ሱዳን ጋር ለማገናኘት እየኳተነ ነው። 
 
ታዬ ደንደአ ራሱ እድሜ ዘመኑን የታገለለት ኦነግ ከስንቅ እስከ ትጥቅ ሲቀርብለት የኖረው የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑት የግብጽና የሱዳን አገዛዞች ነው። በግብጽ ብሔራዊ ቴሌቭዥን በተላለፈውና ፕሬዝደንት ሙርሲ በመራው ጉባዔ ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ፍላጎት ለማስፈጸምና ኢትዮጵያን ለማዳከም ይጠቅመኛል ያለችውም ኦሮሞን እንጂ አማራን አልነበረም። ግብጽ ታላቁን የአባይ ግድብ በቦንብ ታጋየው ዘንድ በአደባባይ የጠየቁም እነ ታዬ ደብደአ የአበባ እቅፍ ይዘው የተቀበሏቸው የኦሮሞ ብሔርተኞች እንጂ የአማራ ልጆች አይደሉም።   
 
ዛሬም ድረስ መቀመጫቸውን በግብጽ ዋና ከተማ በካይሮ አድርገው የግብጽ መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ እየለገሳቸው በየቀኑ ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ሲያደርጉ የሚውሉት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና ማኅበራት በኦሮሞ ስም የሚጠሩ እንጂ በአማራ ስም የተቋቋሙ አይደሉም። 
 
ባጭሩ በኦሮሞ ስም ተደራጅቶ ኢትዮጵያን ለማዳከም ከግብጽና ሱዳን ጋር ያልተወዳጀ የኦሮሞ ብሔርተኞች ድርጅት የለም። በዛሬው ቀን የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ባሌ ውስጥ በስሙ ፋውንዴሽን ያቆመለት ዋቆ ጉቱ ራሱን ቀደም ሲል በሱማሌያ፤ ኋላ ላይ ደግሞ በግብጽና ሱዳን እየተረዳ ኢትዮጵያን እንዲያዳክም ያለቀረበለት ስንቅና ትጥቅ አልነበረም። 
 
ባጭሩ የግብጽ፣ የሱማሊያ፣ የሱዳን፣ የየመን፣ የሶሪያ፣ የአልጀሪያ፣ ወዘተ ማሕደሮች ሲገለጡ ተከዝኖ የሚገኘው የኦሮሞ ብሔርተኞች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከጠላቶቿ ጋር የገቡት ቃለ መሀላ፣ የተጻጻፉት የወዳጅነት ደብዳቤ፣ የጠየቁት ድጋፍና የተሰፈረላቸው ቀለብ ነው። አማራ ተበደልሁ ብሎ ኢትዮጵያን ለማተራመስ በግብጽ፣ በሱማሊያ፣ በሱዳን፣ በየመን፣ በሶሪያ፣ በአልጀሪያ፣ ወዘተ ሲታገዙ እንደኖሩት የኦሮሞ ብሔርተኞች የኢትዮጵያ ጠላቶችን የመወዳጀት ታሪክም ባሕልም የለውም። ኢትዮጵያን ለማተራመስ የኢትዮጵያን ጠላቶችን የመወዳጀት ታሪክና ልምድ ያለው ኦሮሞ ነኝ የሚለው እንደ ዋቆ ጉቱ አይነት የኦሮሞ ብሔርተኛ ናቸው። 
 
ስለዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶችን እየተወዳጁ ኢትዮጵያን ማዳከም የኦሮሞ ብሔርተኞች ጥርሳቸውን የነቀሉበት ፖለቲካ እንጂ የማንም አይደሉምና ኦሮሞ ነን በሚሉ ጉዶች  በሞሎፖል ተይዞ የኖረውንና ጥርሳችሁን የነቀላችሁበትን ኢትዮጵያን የማድማትና የኢትዮጵያን ጠላቶችን  ፍላጎት ያለ ገደብ የማስፈጸም የተላላኪነት ስራ የአማራው አታድርጉት።
Filed in: Amharic