>
5:13 pm - Saturday April 19, 3119

የአቢይ ኦሮሙማ በኢትዮጵያ ላይ ከከፈታቸው ዐውደ ውጊያዎች ጥቂቶቹ! (አምባቸው ደጀኔ) 

የአቢይ ኦሮሙማ በኢትዮጵያ ላይ ከከፈታቸው ዐውደ ውጊያዎች ጥቂቶቹ!

አምባቸው ደጀኔ 


  1. በኔ ላይም ከታወጀው ትልቅ ጦርነት ልጀምር፡፡ በኔና በመሰሎቼ ላይ ከተከፈቱብን ጦርነቶች አንዱና ሕይወት ቀጣፊው በብስጭት ምክንያት የሚከሰቱ ህመሞች ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ ሰው እየቀወሰና ጨርቁን ጥሎ እያበደ ነው፡፡ ሰካራም በዝቷል፤ ጎዳና ተዳዳሪ በዝቷል፡፡ ከለዬለት ዕብደት በመለስ በደም ግፊትና ስኳርን በመሰሉ ተዛማጅ በሽታዎች የምንሰቃይ በዝተናል፤ ኦሮሙማ በዚህም የጦር ግምባር ድል በድል እየሆነ ነው፡፡
  2. አማራንና አማራ ነክ የሆነን በሙሉ ማውደም፡፡ የምታውቁትን ስዘረዝር አልገኝም፡፡ ለኔ አዲስ የሆነ አሁን የሰማሁትን ግን ልጠቀስ፡፡ እሱም በሰሜን ሸዋው ሰሞነኛ የኦሮሙማ ወረራ የአማራ ገበሬዎችን ከነቤተሰባቸው ከመግደል ጎን ለጎን የጎተራ እህል እየገለበጡና የሚዘረፍን ተንቀሳቃሽ ንብረት እየዘረፉ በአይሱዙ እንደሚጭኑ የተሰራጨው አሳዛኝ ዜና ነው፡፡ ወሰን የሌለው ዕብሪትና ጥጋብ፡፡ ብቻ ኦሮሙማ ድል በድል እየሆነ ነው፡፡
  3. የዕቃና የኑሮ ውድነት፡፡ ይህ ነጥብ ነው አሁን ልጽፍ ያነሳሳኝ፡፡ በአንድ ወዳጄ የሥራ ቦታ እያወራን ሳለ አሁን የምነግራችሁን አስደንጋጭ የዕቃ ዋጋ ሲነግረኝ የጀመረውን ዐረፍተ ነገር እስኪጨርስ(ልኝ) አልታገስኩትም – ለመጻፍ ቸኩዬ፡፡ ቀደም ሲል በወያኔ ዘመን ዋጋው 55 ብር የነበረ ባለ 1.5 ሚሊም የብረት ሣንቃ (ላሜራ) አሁን ብር 2000፣ … ብር 400 የነበረ ባለ 6 ሚሊም ላሜራ አሁን ብር 10500 (አሥር ሽህ አምስት መቶ!)፡፡ ሰውዬው ሊያብድ ምንም አልቀረው፡፡ በዕቃዎች ውድነት ሳቢያ አንድም ደምበኛ ሊመጣለት እንዳልቻለ ከማልቀስ ባልተናነሰ ምሬት ሲነግረኝ እኔም አበድኩ – ማበድ ለውጥ ያመጣ ይመስል፡፡ ይሄ በግንባታና በቤት ዕቃ ምርት ላይ ያለውን የዕቃዎች የዋጋ ንረት ሲጠቁም በምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች በኩል ያለው ደግሞ ለማመን ይከብዳል፡፡ ትናንት በአላሙዲን መደብር የምግብ ዘይት ልገዛ ብል ሊትሩን ብር 116 ተባልኩና ትቼው ወጣሁ፡፡ ሰፈር ውስጥ ባለ 5 ሊትሩ ዘይት ብር 570 ነው፡፡ ሁሉም ዕቃ “ዋጋው ሰማይ ወጥቷል” የሚለው ነባርና የተለመደ አባባል አይገልጸውም፡፡ ኑሮው ሆን ተብሎ እንዲህ የሚንረው በመንግሥት ትዕዛዝ አዲስ አበባን ለኑሮ የማትመች (Irrelevant) እናደርጋታለን ካሉት ዛቻና የዛቻ ትግበራ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው፡፡ እንጂ ቢያንስ በወያኔ ጊዜ በነበረው የዋጋ ተመን ማስኬድ ይችሉ ነበር፡፡ ችግሩ ኦህዲድ ሠራሽ ነው – ሰውን ለማበሳጨትና በጥይት አናቱን መበጥረቅ ያልቻሉትን በርሀብ ለመግደል፡፡ በዚህም ግምባር ኦሮሙማ ድል በድል እየሆነ ነው፡፡
  4. የፌዴራሉንና የአንዳንድ ምናልባትም በግልጽ በማይታይ ሁኔታ የሁሉንም የክልል ባለሥልጣናት በኦሮሞ መተካት፡፡ ይህ ሽመልስ አብዲሣ በዝግ ስብሰባቸው “ኦሮሙማን እንዴት እንደምናስፋፋና አማራንና ኢትዮጵያን በኦሮሙማ እንዴት እንደምንተካ አትጠይቁን፡፡ ሥራውን በህግም ከህግ ውጪም እያቀላጠፍን እንገኛለን፡፡ የሀገሪቱን የሥራ ቋንቋ ከአንድ ወደ አምስት ከፍ እንዲል ያደረግነው ለአማርኛና ለሌሎቹ አዝነን ሳይሆን ለዘዴ  ነው፡፡ ለዚህም ስኬት አባይን ተሻግረን በማሳመንም በማታለልና በማምታታትም ብዙ ሥራ ሠርተናል፡፡” ብሎ የተናገረውን እዚህ ላይ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የኦሮሙማ ከሆነ ሰነበተ፡፡ ትግራይንም በስተጀርባ የሚመራት ኦሮሙማ ነው (“አንበሣ ሲያረጅ የዝምብ መጫወጫ ይሆናል” ብለህ አትተርትልኝም እዚህ ላይ ታዲያ ወንድማለም? – “አንቺም ጨካኝ ነበርሽ ጨካኝ አዘዘብሽ፤ እንደገና ዳቦ እሳት ነደደብሽ” ብለህም ጨምርበት ከፈለግህ)፡፡ አማራን በተዛዋሪ ሳይሆን በቀጥታ ኦሮሙማ ነው እያስተዳደረው የሚገኘው (ያቺን ነገረኛ ተረት እዚህም በደምብ ጮክ ብለህ ድገምልኝማ!)፡፡ ፌዴራሉ ከኦረመመ (ኦሮማይዝድ ከሆነ) ቆዬ፡፡ ምን አለፋህ – አቢይ ያልተቆጣጠረው የኔን ባለቤት ወ/ሮ ጠንፍየለሽን ብቻ ነው ወንድሜዋ – ለነገሩ ይህንንስ እንዴት ላውቅ እችላሁ? እኔ እምውል ሥራ፡፡ ለማንቻውም በዚህም ኦሮሙማ ድልን በድል ላይ እየተቀዳጀ ነው፡፡ ‹ደስ ሲል!›
  5. ህዝብን ማደንቆር፤ ማይምነትን ማስፋፋት፡፡ ዜጎችን አደንቁሮ እንደእንስሳት እየጋለቡ መግዛት የብዙ አምባገነኖች የጋራ ባሕርይ ነው፡፡ በመሆኑም ባለዶክትሬት ዲግሪ ማይም ሥልጣን ይዞ በሚፏልልባት ኢትዮጵያ፣ ስሙን በእንግሊዝኛ ይቅርና በአማርኛና በገዛ ቋንቋው አስተካክሎ የማይጽፍ ባለማስትሬትና ቢኤ ዲግሪ ጀንፈል የፓርላማ፣ የዞንና የወረዳ ካቢኔ አባል ሆኖ በህዝብ ላይ በሚኮፈስባት ኢትዮጵያ 30 እና 40 ዩኒቨርስቲዎች መኖራቸው ቢነገርም ከዕቅድ አፈጻጸም እስታቲክሳዊ ላንቲካነት አያልፉም፡፡ የትምህርት ጥራት ወርዶ ወርዶ ወርዶ …. አሁን አሁን በቋንቋም በሃሳብም የደኸዬው ዜጋ በተመሪነት ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ የአመራር ሰጪነት ቦታ ላይ ተኮፍሶ ልታገኘው ትችላለህ፤ ይህ ዓይነቱ ግብዝ ታዲያ ሰው መሆኑን እስከመርሳት ይደርስና በፈጣሪ ቦታ ላይ ተቀምጦ ለመመለከም ሲዳዳው ታያለህ፡፡ በድንቁርና ዱላ በተመታ በዚህን መሰል ሕዝብ መሃል ማንም ሞሽላቃ ሌባ እየተነሣ “እኔ ከመራሁህ ዝናብ አዘንብልሃለሁ፤ ማርና ወተትም በየቤትህ በቧምቧ አስገባልሃለሁ” ቢል “አሜን! በእናንተ መጀን” እያለ እልልታውን የሚያቀልጥ አሸርጋጅ አይጠፋም፡፡ በዚህ ዘመን ከብዙ ዜጎች ጋር ተነጋግረህ መግባባት አትችልም – በአንድ ቋንቋም እኮ ነው ደግሞ፡፡ የሃሳብ ዕጥረት በሽ ነው፡፡ የዕውቀት ዕጥረት እንጢቅ ነው፡፡ የቋንቋው ችግርማ አይነሣ፡፡ መደማመጥም ዕርም እየሆነ ነው፡፡ ለምሣሌ ሲሳይ ዳምጤ ከሚባለው የአማራ ባለሥልጣን ጋር ስለዝምብ ወርድና ቁመት ተወያይተህ መስማማትና በወያኔ-ወለድ ቋንቋ “የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ” አትችልም፤ አንተ “ዝምብ ከጎጂ ነፍሳት አንዷ ነች” ብትል እርሱ ማለትም ሲሴ “ዝምብ ለጭነት አገልግሎት የምትውል የቤት እንስሳ ናት” ሊልህ ይችላል – “አልተገናኝቶም”፡፡ ወያኔና ኦሮሙማ ትውልዱን እስከዚህ በዕውቀት አደኽይተውታል፡፡ ለተረዳው አገርን በማይምነት ጨንገር መግረፍና የአእምሮ ዕድገትን ማቀጨጭ ትልቅ ጦርነት ነው፡፡ እናም ድል በድል እየሆኑ ኦሮሙማዎች፡፡
  6. ሙስናና ዘረፋ፡፡ ይህንንም ታውቁታላችሁ፡፡ ምድረ ደንቆሮና ማይም ባለሥልጣን ከሀገርም ከህዝብም አስተሳሰብ ወጥቶ ከዝንጀሮም ባነሰ ደረጃ ራስ ወዳድ በመሆኑ ህዝብንና ሀገርን እየዘረፈ ሚሊዮኔር ሆኗል፡፡ እጅግ ብዙው የመንግሥት የሥራ ኃላፊ ደሞዙን አያውቀውም፤ ሙስናም በህግ የተደገፈ እስኪመስል በጠራራ ፀሐይ የሚከናወን ተራ ነገር ነው – የማይሞስን እንዲያውም ፋራ ወይ ሰገጤ ይባላል፡፡ ሙሰኛው ከመንግሥት ይዘርፋል፤ ከህዝብ ይዘርፋል፤ ከኢንቬስተሮች ይዘርፋል፡፡ ከፈጣሪም የምስኪኖችን ነፍስ ይዘርፋል፡፡ ሀገር አለች የምንለው በሚዲያ እንጂ በተግባርና በካርታም ጭምር የለችም፡፡ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ “ኢትዮጵያ የምትባል ገናና ሀገር በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ነበረች፤ ግን በገዛ ልጆቿ ወደመች” የሚባልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ 

በቃኝ እባክህን ወንድሜ፡፡ ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፡፡ ከመሰናበቴ በፊት ግን አንድ ነገር ልማጠን፡፡ የአማራ ክልል ባለሥልጣናት ከግርድናና ከኩሊነት እንዲወጡ እንጸልይላቸው – ደግሞም እኮ አሳፋሪው ነገር ግርድናቸው ከነሱ በኋላ ወያኔ ሰሜን ሸዋ ደራ ከተማ ላይ – ትዝ ይለኛል – መጋቢት 17 ቀን 1981 ዓ.ም በምርኮኛ የኦሮሞ ወታደሮች ኦህዲድ ብሎ ለጠፈጠፋቸው የትህነግ የእጅ ሥራዎች መሆኑ ነው፡፡ “አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል” መባሉ እውነት ነው፡፡ “ጀግናው” ኦህዲድ ፈጣሪውን ሕወሓትንም፣ ታላቅ ወንድሙን ብአዴንንም ዙቢት ብሎ እንደፈረስ ይጋልባቸው ገባ፡፡ “በኋላ የመጣ ቀንድ በፊት የወጣን ጆሮ በለጠው” ይሏል ይሄኔ ነው፡፡ ለነገሩ እነዚህ የብአዴን ደናቁርት በምንም መንገድ ዓሣማና ጅቦችን ካልሆነ አማራን ሊወክሉ አይችሉም፡፡ በየብሔሩ “ወላድ አትያችሁ” የሚባሉ ማፈሪያ ጉግማንጉጎች እንደሚፈጠሩ ይታወቃልና እነዚህም እንደነዚያ ያሉ ጉዶች ናቸው፡፡ የሚጠፉበት አበቅቴያቸውም ደርሷል፡፡ “አይቶ አያውቅ ዳቦ ፊሪዳው” እንዲሉ ሥልጣንና ሀብት ብርቁ የሆነው አለቃቸው ኦሮሙማ ደግሞ አካሄዱን ስላላወቀበትና ምድርንም ሰማይንም በሚዘገንን ሁኔታ ዐረመኔነቱ አገር ምድሩን ስላጥለቀለቀ በማያውቀው ኃይል ወገብ ዛላው ይመታና ልክ እንደአባቱ ሕወሓት የታሪክ ጥጋቱን ይይዛል፡፡ ኦህዲድ/ኦነግ የእርጉዝን ማኅጸን ቀዶ ሽል በማውጣት ሟችን እናት እንዳስታቀፈ፣ ኅያው እግዚአብሔርም በተለይ ከአድማስ ወዲያ ማዶ አገር ስለመኖሩ እንኳን ምንም የማያውቁ ሕጻናትና አእሩግ ንጹሕ አማሮች ላይ የሠራውን ግፍ ሁሉ ቆጥሮ በጅምላም በችርቻሮም ዋጋውን ያስታቅፈዋል፡፡ ግን ደግሞ ጸልዩ እንጂ አትቸኩሉ – ማለቴ እንጸልይ እንጂ አንቸኩል፡፡ ታች አምናን፣ አምናን፣ ትናንት በስቲያንና ትናንትን ያዬ ስለነገው የአምላክ ፍርድ በፍጹም አይጠራጠርም፡፡ ማይም ጉልበተኞች ግን – ለምን እንደሆነ ብዙም አይገባኝም – በተለይ አሁን አሁን ከተጎጂዎቻቸው ባልተናነሰ ያሳዝኑኛል፡፡ ወደው አይምሰለን እንዲህ የሚጨክኑት …

Filed in: Amharic