>

"ከእንግዲህ ወገንም ሀገርም መንግሥትም ዜግነትም... የለኝም....!!!"  (ታዬ ቦጋለ አረጋ)

“ከእንግዲህ ወገንም ሀገርም መንግሥትም ዜግነትም… የለኝም….!!!”

 ታዬ ቦጋለ አረጋ

የአማራ ልዩ ኃይል ኢትዮጵያን ለመታደግ ሲል፤ ለ46 ዓመታት ዘመን የወለዳቸውን ዘመናዊ መሳሪያዎች እስከ አፍንጫው ታጥቆ፤ በአስቸጋሪ ተራሮች ጠንካራ ምሽግ ቆፍሮ… ከተደራጀው ትህነግ (TPLF) እና ዓለማቀፍ ኃይል ጋር በወኔ ሲፋለም፤ // ጀግኖች በመስዋዕትነት ኢትዮጵያን ሲታደጉ…
የተገላቢጦሽ በሰላማዊ የአማራ ተወላጆች (ህፃናት ሴቶች አዛውንት እና ነፍስ ወከፍ ተራ መሳሪያ በታጠቁ ጥቂት ሚሊሺያዎች) ላይ ድሽቃ ባዙቃ እና ረጂም ርቀት ተተኳሽ አንግቦ ወረራ መፈፀም፤ ከተማ ውስጥ በወገን ላይ ጀግና _ ጀግና መጫወት ያሳፍራል፤ ያሳቅቃል፤ ያሸማቅቃል። በአዋራጅነቱ በታሪክም ይመዘገባል። ከእንግዲህ ወገንም ሀገርም መንግሥትም ዜግነትም… የለኝም።
Filed in: Amharic