>

¨ሙቀቱን መቋቋም ከተሳነህ ከምድጃው ውጣ! ¨ (አሰፋ ታረቀኝ)

‘’ If you can’t stand the heat, get out of the kitchen’’ ሙቀቱን መቋቋም ከተሳነህ ከምድጃው ውጣ (አሰፋ ታረቀኝ)

ከደብረብርሐን ጥግ እስከ ቃሉ አውራጃ ከተማ  ኮምቦልቻ ድረስ ያሉት መከከለኛና አነስትኛ ከተሞች የኦነግ ኢላማ ከሆኑ ሰንብተዋል፡፡ ደካሞችን፣ እናቶችንና ህጻናትን አሳዶ ከምፍጀት በስተቀር የታጠቀን ሀይል ፊት ለፊት ገጥሞ የማያውቀው የኦነግ ‘ጦር’ ከነትጥቁ እንድገባ ከተደረገ በኋላ ቡራዩ ላይ ጋሞወችን ጨፍጭፎ ወደ ‘ነጻ ግዛቱ’ ወደ ወልጋ ወርዶ ከነ ትጥቁ እንድከትም ተደረገ፡፡ ኦነግ ከነጋደነት ወደ ‘ተዋጊነት’ የተሽእጋገረው አቶ ለማ መገርሳ አሥመራ ድረስ ተጉዘው በገቡት ውለታ ከነ ትጥቁ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ነው፡፡ ኦነግና አቶለማ የተዋዋሉት ምን እንደነበረ እስካሁን የኢትዮጵአያ ሕዝብ አያውቀውም፡፡ እርሳቸውም በምን ምክንያት ከፖለቲካው ገለል እንዳሉ ግልጽ አይደለም፡፡ ልክ እንደ ህዋህት የኦነግም ቀንደኛ ጠላት አማራ ነው፡፡ ምክንያቱም “ ቅኝ ገዥ” ነውና፡፡ በመረጃ የደለበው ታሪክ የሚነግረን ደግሞ ተቃራኒውን ነው፡፡ ኦነግ እንደ ሀረግ መንጠላጠያ ካላገኘ በስተቅር ዘመኑን ሁሉ ብቻውን ቆሞ አያውቅም፡፡ የ “ኦሮሚያ”ው ብልስጽና ውስጥ ተሰግስጎ የዶ/ር አብይን ራእይ ሽባ ለማድረና በኢቶዮጵያ መቃብር ላይ የሚመኛትን “ኦሮሚያ” ዕውን ለማድረግ የቋመጠ ይመስላል፤ ያቀደውን ፕሮጀክት ብቻውን መፈጸም እንደማይችል ኦነግ በሚገባ ያውቀዋል፡፡ ያገኘውን ቀዳዳ ሁሉ ተጠቅሞ “አማራውን” ማስቆጣትና በዶ/ር አብይ ላይ ማስነሳት አለበት፡፡ መልዕክቱም ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ቋንቋህን ቀይርና “ኦሮሚያ፣ ኦሮሚያ” በል ነው፡፡ በወለጋም ከሰሜን ሸዋ እስከ ወሎ ኮምቦልቻ ጥግ ድረስ በግፍ ለረገፉት ነፍሳት፣ ለይስሙላ እንኳ ከ “ኦሮሚያ”ው ብልጽግ የማጽናኛ መግለጫ አለማውጣታቸው፣ በኦሆዲድ ይመዝገቡ እንጂ፣ የብልጽግና አባላት ሳይሆኑ የኦነግ የአደባባይ “ ተዋጊ’ ካድሬዎች መስለዋል፡፡

ሌላው የሰሞኑ አስገራሚ ሁኔታ፣ የብልጽግናው ኦነግ ሲታጠቅና ሲደራጅ፣ የ “አማራው” ብልጽና ምን ይሰራ ነበር? በግዛት ክልሉ ውስጥ ያለውን ህዝብ ደህንነት የማረጋገጡ ኅላፈነት የማነው? ቢያንስ መረጃ መሰብሰብና ሕዝቡን በማስጠንቀቅ ጉዳቱን መቀነስ አይቻልም ነበርን? የአማራው ልዩ ኅይል በአራቱም አቅጫ መወጠሩ የኅይል መመናመን እንደሚያስከትል ግልጽ ነው፡፡ የ”አማራ ክልል” በተባለው አካባቢ የሚኖረው ሕዝብ ደግሞ እራሱን ለመከላከል ሥልጠና አያስፈልገውም፡በደሙ ውስጥ ያለ ነው፡፡ ራሱን ከጥቃት እንድከላከል ትጥቅ አይሰጠውም ነበር? የ “አማራው” መንግሥት የመረጃና ክትትል መምሪያ የለውምን? የ ኦነጉ ኦነግ አምስት ስድስት ቦታ ቢሰነጣጠቅም፣ የኦሆዲዱ ኦነግ የብልጽናን ካባ ደርቦ የዶ/ር አብይን ረጅም እቅድ ባጭር ለማስቀረት በትጋት እየሰራ ነው፡፡ የወከለውን ሕዝብ ደህንነት ለብልጽግናው ኦነግ ጥቃት አሳልፎ የሰጠው የ”አማራው” ብልጽና ፈርቶም ይሁን ተሞኝቶ ባይታወቅም፣ የሴራው ተባባሪ መስሏል፡፡ እነሆ ውጤቱ እየታየ ነው፡፡ ትናንት አብሯቸው ለመሞት ፈቃደኛ የነበረው የ”አማራ” ክልል ወጣት ዶ/ር አብይን ተቃውሞ በአደባባይ ወጣ፡፡ ይኽ ለብልጽናው ኦነግ የድሉ ግማሽ ነው፡፡ የ’አማራው”ብልጽና ተገቢ መረጃ አንኳ በመስጠት ሕዝቡን መጠበቅ ካልቻለ፣ ለምን ቦታውን ለሚችሉት አይለቅም? የብልጽናው ኦነግ ከዚሕም የከፋ ጥፋት ያልፈጸመው ዶ/ር አብይ ከላይ ስላሉ ነው፡ የ ‘’አማራው” ጽንፈኛ ይህንን ለምን እንዳልተረዳው እስከዚህ ሰአት ድረስ አልግባኝም፡፡ ለኢቶዮጵያ የተደገሰላት አደጋ እጅግ አስፈሪ ነው፡፡ በምኅረት የለሽ ደላሎችና ነጋዴዎች ተከባለች፡፡የሰሜኑ ደላላ በለኮሰው እሳት ተለብልቦ የደቀቀ ቢሆንም፣ የባህርይ ልጁ የሆነው የመሐል አገሩ ደላላ፣ የብልጽናው ኦነግ አሰፍስፎ እየጠበቀ ነው፡፡ የኔ ትውልድ የሠራው ስኅተት፣ ይኸ ትውልድ እንዳይደግመው ያሰጋል፡፡ ንጉሡን ስንቃወም የተሻለ የሚመጣ መስሎን ነበር፡ንጉሡ ሄዱ፣ ሐገር ከል ለበሰች፡፡ ደርግ ይሂድ ተባል፤ የተተካውን አይተነዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኦነግ አይደሉም፡፡ ጥራዝ ነጠቆች እንድሚሉት ፋሽስትም አይደሉ፡፡ አርቆ አስተዋይ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ዶ/ር አብይን እንድናጣ የሚጮሁት ቁጥራቸው ጨምሯል፡፡ ታስቦበት ይሆን? ዶ/ር አብይ ባይኖሩ፣ ሥልጣኑን የሚረከቡት የብልጽግናው ኦነግና እውጭ ያለው የህዋህት ደላላ ናቸው፡፡ የሁሉት ጥምረት ደግሞ የ አፍሪካ ቀንድ ፋሽዝም ከመመሥረት ውጭ ሌላ አያመጡም፡፡ ያኔ አፍሪካዊ አይሁድ የሚሆነው “አማራው” ነው፡፡ ናዚ ጀርመን በአይሁዳውያን ላይ የፈጸመችውን ያስታውሷል፡፡

የማን ቤት ወድሞ የማን ሊበጅ፣

የአውሬ መውለጃ ይሆናል እንጅ፡፡ እየትባለ ያደገን የ”አማራ’’ ልጅ አንገት አስደፍቸ እኖራለሁ ብሎ ማሰቡም ቂልነት ነው፡

Filed in: Amharic