>

ሰልፉን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

ሰልፉን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ


ለአለፉት ሶስት አስርት አመታት በአማራ ህዝብ ላይ በየዕለቱ የመርዶ ዜናዎችን መስማት የተለመደ ሁኖዓል፡፡ በቅርቡ ከለውጥ በኃላ እንኳን በርካታ ሰቆቃዎች ተሰምተዋል፡፡ በቡራዬ፣ በዝዋይ፣ በሻሸመኔ፣ በመተከል፣ በቤኒሻንጉል፣በጅማ፣ በወለጋ፣ በአጣዬ፣ ሸዋ ሮቢት፣ በካራ-ቆሬ፣ በኮንሶ፣ በጌዲዬ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተደጋጋሚ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ወገኖቻችን ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል፣ ተሰደዋል፣ ለዘመናት ያፈሩት ጥሪት በመትረጊስና በእሳት ዶጋ-ዓመድ ሁኖዓል፡፡ 

ይህን ሁሉ እልቂት ለረጅም ጊዜ ከታገሰ በኃላ የአማራ ህዝብ በተለያዩ ከተሞች ክፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ተቃውሞ አሰምቷል፤ እያሰማም ነው፡፡ የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስቱ የህዝቡን ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ መስጠት የህግም፣የፖለቲካም፣ የሞራልም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በሰልፉ ላይ የተሰሙ እና የታዩ መልዕክቶችን በማጤን ለጉዳዩ መልስ መስጠት እንጅ መፈረጅ እና ጉዳዩን ወደ አንድ ፓርቲ ማላከኩ መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡ የአማራ ህዝብ ለዓመታት የደረሰበትን ግፍ እና ሰቆቃ አለባብሶ ማለፍ የከፋ ዋጋ ያስከፍላል እንጅ መፍትሄ አያመጣም፡፡

Filed in: Amharic