>

"የኦሮሞ ብልጽግና የማይነካ ነገር ነክቶ የመይሳው ካሳን ትውልድ ከእንቅልፉ ቀስቅሶታል" (ዶክተር መኮነን ብሩ)

“የኦሮሞ ብልጽግና የማይነካ ነገር ነክቶ የመይሳው ካሳን ትውልድ ከእንቅልፉ ቀስቅሶታል”

 
(ዶክተር መኮነን ብሩ)
 

እናንተ የኦሮሞ ብልፅግና ጠባቦች ሆይ …. 
 
በኦሮሞ ብልፅግና ዉስጥ በአመራርነት ተሰግስጋችሁ ወገናችንን የአማራ ሕዝብ በተለያየ አራት አቅጣጫ ልትወሩት አሴራችሁ። በሱዳን፣ በአፋር፣ በወለጋ፣ በሸዋ በኦነግ አርማ ዉስጥ ተሸሽጋችሁ እንደምስጥ ዉስጥ ለዉስጥ ልትገዘግዙት ቆቋመጣችሁ። አንዴ ወሎ ኦሮሞ ነዉ ሌላ ጊዜ ፊንፊኔ ኬኛ በማለት ዝንተዓለም የሚቆረጥማችሁን አፈር መላስ የፈለጋችሁ ይመስል አቅራራችሁበት። ይባስ ብሎ የወለጋዉ ሳያንስ በራሱ ክልል ገብታችሁ በርካቶችን ጨፈጨፋችሁ ሺዎችንም አፈናቀላችሁ። በዚህም የተመኛችሁትን የአማራ ብልፅግናን አንኮታኮታችሁ። 
 
ይሁን እንጂ ነገሮች በአጭር ጊዜ ከቁጥጥራችሁ ዉጪ ሆነ። እንደ ግመል የነዳችሁትን የአማራ ብልፅግና ወደ ገደል ስትወረዉሩ ተኝቶ የነበረዉን የመይሳዉ ካሳ ትዉልድ አንበሳ ቀሰቀሳችሁ። አንበሳ ኩሩ ነዉ። ሁሉ የእሱ መሆኑን ስለሚያዉቅ እንደድመት በየዞኑና በየጥጉ ጠረኑን ሲረጭ አይታይም። የእሱ ጠረን በሰሜን ኤርትራ፣ በደቡብ ኬኒያ፣ በምህራብ ሱዳን እንዲሁም በምስራቅ ጅቡቲና ሱማሊያ እንጂ የሐቃቂን ወንዝ በተሻገረ ቁጥር ኬኛ እያለ አይሸናም። 
 
የእኛም የኩሩ ኢትዮጵያዊያን ጠረን የአንበሳዉ ዓይነት ነዉ። ኢትዮጵያዊ ኩሩና ደግ ነዉ። የገበሬ ቤትና ጎተራ አያቃጥልም። እርጉዝ ሴት አያመክንም። ሕፃናት አይገድልም።ኢትዮጵያዊ አንበሳ ነዉ። ይታገስሃል በመጨረሻ ግን በጣጥሶ ይጥልሃል። ምሳሌ ከፈለክ ጄኔራል ታደሰ ብሩ እግር ስር ወድቆ ምህረት የጠየቀዉን የሱማሌ ጀሌ ዋቆ ጉቱን ርዝራዥ ፈልገህ ጠይቅ። 
 
እናንተ የኦሮሞ ብልፅግና ጠባቦች ሆይ … እመኑኝ በቅርቡ በአጣዬ መንካት የሌለባችሁን እንደነካችሁ በመረዳት ትፀፀታላችሁ። 
 
ወገኔ የአማራ ሕዝብ ሆይ …. ኢትዮጵያዊ ብቻ ነን የምንል በርካታ ሚሊዮኖች አብረንህ ነን። ከየትም እንምጣ ከየትም ኢትዮጵያዊ ነንና አንተ ከሌለህ ኢትዮጵያ ስለማትኖር አብረንህ እንዋደቃለን። 
 
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች።
ሁሌም ኢትዮጵያዊዉ
Filed in: Amharic