>
7:18 pm - Monday May 29, 2023

በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እየተሽከረከረ ያለ  በደም የተሞላ ገንቦ አለ!!! ይህ የደም ገንቦ ከመፍሰሱ በፊት መንግስት ይፍጠን!!!!  (ደጀኔ አሰፋ)

በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እየተሽከረከረ ያለ  በደም የተሞላ ገንቦ አለ!!! ይህ የደም ገንቦ ከመፍሰሱ በፊት መንግስት ይፍጠን!!!! 
ደጀኔ አሰፋ

በአማራ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃትና ይህን ተከትሎ የታየውን የህዝብ ቁጣ በመጠቀም ኢትዮጵያን ማፍረስ ኢላማ ያደረጉ ሃይሎች ህልማቸውን እውን ለማድረግ ከውስጥም ከውጭም እየተጉ ናቸው!!! ከፍተኛ ቅንጅት አለ:: በጣም ይናበባሉ:: የእርስበእርስ ፍጅትን ለማየት ቋምጠዋል:: ዳግማዊት ሩዋንዳ ሲሉም ዝተዋል:: ነጮቹም ይህን ለማየት ጓግተዋል:: ነገሮች ካልተረጋጉ የምርጫ ታዛቢ ለመላክ አንችልም በማለት የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል:: ይህ ማለት ችግሩ ይፈጠራል … እንደሚፈጠርም እናውቃለን እንደማለት ነው:: ስለዚህ አድፍጠዋል:: ችግሩ ከተፈጠረ ሁሉም ነገር በእጃቸው ይገባል:: ከሞትና ከእርስበርስ መጠፋፋት ግን አያድኑንም:: ሊያድኑንም አይፈልጉም:: ምክንያቱም ከእነሱ ፍላጎት ውጭ እየሄድን ነው:: በግድቡ ዙሪያ እሽ አላልናቸውም:: በጁንታው ጉዳይ ፈቃደኛ አልሆንላቸውም:: በምስራቅ አፍሪካ ጉዳይ እነሱ በሚፈልጉት መንገድ እጃቸው ውስጥ አልገባንላቸውም::
የወንድ እና ወንድ የሴት እና ሴት የተመሳሳይ ፆታ የግብረሰዶሞች መብትን እምቢ አንፈቅድም ብለናል:: ብዙ ትዕዛዛቶቻቸውን እነሱ በሚፈልጉት ሁኔታ ሰጥ ለጥ ብለን አላጎበደድንም:: ጭራሽ ምዕራባዊያኑን ወደ ጎን እያልን ፊታችንን ወደ ራሽያ እና ቻይና በማዞራችን ከፍተኛ ቂም ይዘውብናል:: “ልክ እንደ ቻይና እና ህንድ ያሉት የኤሽያ ሃገራት ከምዕራባዊውኑ ተፅዕኖ ሾልከው እንዳመለጡ ኢትዮጵያም እያመለጠችን ነው:: ኢትዮጵያ ካመለጠችን አፍሪካም ታመልጠናለች:: ስለዚህ ኢትዮጵያ አሁን መፍረስ አለባት” ብለዋል:: ከወራት በፊት አቅደው እንደጨረሱ ከዚህ በፊት ገልጫለሁ:: ምዕራባዊያኑ ጨርስዋል::
 ከምዕራባዊያኑ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሃገራት ጀርባ እስራኤል አለች:: ግብፅ በእስራኤል እቅድ ትመራለች:: ሱዳን ደግሞ በግብፅ እቅድ ትሄዳለች:: ከውጭ ጠላቶቻችን በተጨማሪ በኢትዮጵያና በውጭ ሃገራት የሚገኙ ይህን እቅድ የሚያስፈፅሙ አካላት አሉ:: ውስጥ ለውስጥ ከሚሰሩት ህቡዕ አካላት ሌላ አሁን ወደ ሚዲያ መውጣት የጀመሩም ብዙ ናቸው:: አንዳንዶቹ መናሃሪያቸው እስራኤል ነች:: በዩቱይብም በሌላም እየመጡ ነው:: የመገንጠል ጥያቄን እንዳዲስ ማቀንቀን የጀመሩ ደግሞ አሉ:: በዚህም በዚያም ይሰማሩ እንጅ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው አላማቸው::
 አዎ! ጠበኛ የሚመስሉ ቢሆንም ተመሳሳይ ዓላማ ነው ያላቸው:: ተቀናቃኝ የሚመስሉ ሃይሎች እንደሆኑ አክት ቢያደርጉም ግባቸው ግን አንድ ነው:: ኢትዮጵያውያንን ሃገር አልባ ማድረግ ነው:: ኢትዮጵያን ሶሪያ ማድረግ ነው:: ለዚህም እርስበርስ ፍጅትን ማሳካት ነው:: ለዚህ ደግሞ አማራውን የጥቃት ታርጌት በማድረግ ነው:: ከዚያ ትርምስ በመፍጠር መንግስት አልባ ያደርጉንና በመጨረሻም ተባብረው ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው:: የኢትዮጵያ መፍረስ ማለት ምድራዊ ሲኦል ማለት ነው:: አንተም እኔም አንችም ልጆቻችንም ዘመዶቻችንም አይተርፉም:: የሚያመልጥ አይኖርም::
እድለኛ ከሆንክ ሃገር አልባ ሆነህ የበርሃ ተንከራታች ትሆናለህ:: በብሄርህ ሳቢያ ከሞት አትተርፍም:: ያኔ ብሄር ተለይቶ ሟችም አይኖርም:: ከሰማይም ከምድርም በሚወረወር ቅንቡላ ሳታስበው ትገደላለህ:: ከቆምክበት ትወድቃለህ:: በተቀመጥክበት ታሸልባለህ:: ገዳይህን እንኳን አታውቀውም:: ማንም ማንንም አያስጥልም:: ያኔ አማራውም ኦሮሞውም ሶማሊውም አፋሩም ሃረሪውም…. በጅምላ መቃብር አብረን አንድ ላይ እንቀበራለን:: አንድ ላይ መኖር ካልቻልን አንድ ላይ መሞት እና በጅምላ መቀበር ግድ ይሆናል:: ከዚያም ከአመታት በኃላ አፅማችን በመደርደሪያ ላይ ተቀምጦ ለነጮቹ ጉብኝት ክፍት ይሆናል:: ዶክመንተሪ ይሰራበታል::
 ከሩዋንዳ የከፋ ተብሎ ብዙ መፅሃፍት ይፃፍበታል:: ዛሬ ከስሜት ካልወጣን የጠላቶቻችንን ህልም እያሳካን መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል:: የማንም መጠቀሚያ ላለመሆን ማስተዋል አለብን:: ችግር ለማስቆም ችግር ማባባስ አያስፈልግም:: ከዚህና ከዚያ ድንጋይ መወራወር ተው!!! በቃላት አትጠዛጠዝ:: ምን እየዘራህ መሆኑን አስተውል!!! ቁም ወገኔ! ዙሪያህን ተመልከት:: ሞት አንዣቦብሃል!!!! አሁን በሰከነ መንፈስ ኢትዮጵያን ለማዳን በጋራ ካልቆምን ማንም አይተርፍም!!! የኢትዮጵያ ህዝብ አስተውል!!!! ምሁራኖች በፈጠራችሁ አምላክ ስከኑ!!!! አክቲቪስቶች በፈጠራችሁ አምላክ ስከኑ!!!! ውጤቱ ለማናችንም አይበጅም!!!!
በአንፃሩ መንግስት ሆይ ፍጠን!!!! ጊዜ የለህም!!!! ፍጠን!!!! የንፁሃንን ሞት ዛሬውኑ አስቁም!!! የህዝቡን እንባ አብስ!!! ተቀዳሚ ተግባርህ ይህ ነው!!! ይህንን ዛሬውኑ አድርግ!!!! የንፁሃን ሞት መቆም አለበት!!!! የግድ ነው!!!! ጎን ለጎን ደግሞ ፅንፈኞችን በቁጥጥር ስር አውል!!!! ዛሬውኑ በህግ ቁጥጥር ስር አውላቸው!!!! በግራ እና በቀኝ ያሉትን ፅንፈኞች ታውቃቸዋለህ!!! ዛሬውኑ ጨክነህ በቁጥጥር ስር ካላዋልክ አደጋው እጅግ የከፋ ነው!!!! ከዚህ በተጨማሪ ብልፅግና ውስጥ ያሉ ፅንፈኞች ላይ ዛሬውኑ እርምጃ ውሰድ!!!! ለነገ አትበል!!!! ነገን ካደሩ ብዙ ክፋት ይፈፀማል!!!! እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬውኑ በህግ ጥላ ስር አውላቸው!!!! ጊዜ የለህም!!!! ከኦሮሞ ከአማራ ሳትል ዛሬውኑ እርምጃ ውሰድ!!!! ዝግጅታቸው ሰፊ ነው!!!! አፋጣኝ እርምጃ ወስደህ ካልቀደምካቸው በቀር መንግስት አልባ ሆነን ፍጅት ይሆናል በዚያም ሃገር አልባ መሆናችን ነው!!!! የሚተርፍ አንዳች እንኳን የለም!!!! መንግስት ኢትዮጵያን ለማትረፍ ትልቅ ሃላፊነት አለብህ!!!! ለዚህ ደግሞ ደስ የማይሉ ውሳኔዎችም ቢሆኑ ቁርጠኛ እርምጃዎችን መውሰድ ግድ ነው!!!! ህዝቡ ችግር የለበትም!!!! ችግሩ ያለው ፅንፈኞች እና ብልፅግና ውስጥ ባሉ ሴረኞች ነው!!!! ሁሉንም ቅደማቸው!!!! በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እየተሽከረከረ ያለ በምድራችን ላይ ሊደፋ የተዘጋጀ በደም የተሞላ ገንቦ አለ!!! ይህ የደም ገንቦ ከመፍሰሱ በፊት መንግስት ይፍጠን!!!! ካስፈለገም በመላው ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጅ!!!! ካስፈለገም ኢንተርኔት ይዘጋ!!!! ይህ ክፉ ጊዜ ካላለፈ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነገር እንሰማለን!!!! እባክህ መንግስት ሆይ ፍጠን!!!! ድፈርና ዛሬውኑ እርምጃ ውሰድ!!!! ኢትዮጵያን አድን!!!!! ብሄር ብሄር ስንጫወት አገር አልባ ልንሆን ነውና ፈጣሪ ከኢትዮጵያ ጋር ይሁን!!!!
Filed in: Amharic