የፍካሬ ኢየሱስና ወቅታዊ ጉዳይ…!!
ናምሩድ ዘርዓ ያዕቆብ
#Ethiopia | የንጉሥ ቴዎድሮስ ትንቢትና የኢትዮጵያውያን እጣፈንታ ምንድን ነው..!!
ሠሞኑን ይህንን መጽሐፍ አነበብኩ። መጽሐፉ የተዘጋጀበት አመትና በኢትዮጵያ ላይ እየተከናወነ ያለውን ሀቅ ስመለከት ነገሩ የሚገርም ትንቢትና ፍፃሜ ሆኖ አገኘውት።
ሀገሪቱ ብዙ መከራና ስቃይ አሳልፋለች ገና ብዙ አስደንጋጭ ኩኔታወችም ይጠብቋታል። ይህ መጽሐፍ ከዛሬ አንድ ሺ ዓመት በፊት የተዘጋጀና ፍፁም አነጋጋሪው የሆነ የትንቢት መጽሐፍ ሲሆን ትንቢቱ በዓለም ዙሪያ እየተፈፀመ ይገኛል።
በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትንቢት ተናጋሪ ሰወች እየበረከቱ ቢመጡም ከእነ አባ ዘወንጌል እስከ እማሆይ ወለተ መድህን ትንቢትና ንግግሮች አንፃር ተነስተን መጽሐፉን ስንመዝነው ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ወቅታዊ ችግሮች… ፍንትው አድርጎ አስቀምጦ ነበር።
ዓለማችን የገጠማትን አስደንጋጭና እጅግ ብዙ የመከራ ዘመናቶች እንዲሁም መጭው የፍሰሀና የደስታ ጊዜያት ተተንትነው የቀረቡበት የወቅቱ ድንቅ መፅሐፍ ሆኖ ማግኘቴ አስደንቆኛል።
ይህ መጽሐፍ በመግቢያው ጀምስ ብሩስ ወደ አውሮፓ ካሻገራቸው የኢትዮጵያ የምስጢር መጻሕፍቶች መካከል መሆኑንና የመጽሐፈ ሄኖክና ፣ የመጽሐፈ ኩፋሌ እጣፋንታ ደርሶበት ወደ አውሮፓ የተሻገረ መጽሐፍ መኮኑ ለብዙ ኢትዮጵያዊ ምስጢሩ ስውር ሆኖ የቆየና በአንዳንድ የአፍ ትርክቶች ብቻ የሚነገር ሆኖ ቆይቷል።
ይህ ፍካሬ ኢየሱስ የሣልሳዊ ቴዎድሮስ አነሳስ መፅሐፍ ታድያ በውስጡ ከትርክት በዘለለ……….. በታሪካዊ የኢትዮጵያ ገድላትና ድርሳናት ትንተናና ዋቢ ማስረጃ በልጽጎ የቀረበ የወቅቱን ችግርና ጦርነትና አለማቀፋዊ ስለሆነው የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ላይ ስለሚውምፈሳየረው የጦርነትና የርሀብ ችግሮችን ተንትኖ የቀረበ የሚስጥር መጽሀፍ ሆኖ ማንበቤ አስደንቆኛል።
በምሥራቅ በኩል ሥለሚወጣው ቴዎድሮስ የሚባል ደገኛ ንጉስ ይተርካል። የመከራው ዘመን በኢትዮጵያ ይመጣ ዘንድ ግድ ነበር ። ይህም ሆኖ ከሚያልፍው ዘመን በኊላ ፈቃዴን የሚፈጽሙትን ከመከራ ያተረፍኩዋቸውን የሚሰበሰብ ነው ሲል ይገልፀዋል።
ይህንን ትንቢት ታዲያ የማይቀበሉ የሚከራከሩ መብዛታቼው እንዳለለ ሆኖ በተለይ በዚህ አምስት አመታት ጀምሮ ባሳለፍናቸው ሦስት አመታት ላይ የተፈጠሩት የህይወትና የንብረት በኢትዮጵያ ላይ ያንዣበቡትና የተፈፀሙት አደጋወች በሙሉ ከትንቢቱ የዘለሉ አይደሉም።
እንደኔ የአውሮፓውያኑና የአሜሪካ የሀሳብ መገለባበጥና በኢትዮጵያ ላይ የሚፈፀሙት ችግሮች ጀርባ እጃቸው እረጅም መሆኑ አያስገርመኝም ምክንያቱም አየተፈፀሙ የሚገኙት ታላላቅ ንግርቶችና ትንቢቶችን የያዙት መጽሐፍት በየጊዜው እየተዘረፉ በመውጣት በአውሮፓ ሙዚየምየሞችና ቤተ-መጽሐፍት ውስጥ መቀመጣቸው ኢትዮጵካኑ የእነዚህ ስውር ምስጢራት ባዳ እንዲሆን መደረጉ ነገሮችን በትኩረት እንዳያይ ሆኖ ይገኛል። ለዚህም ምሳሌ ከመቅደላ የተዘረፉት መጽሐፍት በቂ ማስረጃ ሲሆኑ በአውሮፓ ውሥጥ የተቀመጡት የተለየ ልዩ ቁጥር በኮድ በዘመን ክፍፍል ነው፡፡
በብሪቲሽ ሙዚየም የሚገኘው ታዋቂው ካታሎግ በዊሊያም ራይት የተቀነባበረው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሙሉ ገለፃው ይህን ይገልጣል፡፡
“Catalogue of the Ethiopian Manuscripts in the Biritish Museum acquired since the year 1847. William Wright. Landon; British Museum .1877.365 P,”
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የግእዝ ሊቃውንት በደማቅ ብራና የጻፏቸው መጽሐፍት ዝርዝር የሚገኝበት በተለያዩ እንግሊዛዊያን ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ከጄኔራል ናፒየር ጋር መቅደላ የመጣው ሪቻርድ ሆልመስ ከሠራዊቱ ያሰባሰበው ብራና ሁሉ በዊሊያም ራይት ካታሎግ ተዘግቧል፡፡
ከብራና መጽሐፍት መካከል ትልቁ ፍካሬ ኢየሱስ (Prophecy of Jesus)160 ቅጠሎች (Folio 1609q) በኢትዮጵያ በንግርት የሚጠበቀው ኢትዮጵያዊው ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ የሚመጣበት ጊዜ የተገለጸበና የተብራራበት መጽሐፍ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የነበረውን አንድ ቅጅ መጽሐፍም በሀይለስላሴ እጅ እንደነበረና ኃይለስላሴም ንጉሱ የሚመጣበትን ቀን የሚጠቁመውን ገጽ ነቅለው እንዳወጡት ተጠቅሷል። ያዲያ ይህ ንጉሥ ሲነሳ አቡነ ፀሐይ ምድርን ሲባርኩ ንጉሥ ቴዎድሮስ ዓለምን ሲመራ ዓለም ለሺህ ዓመታት የተጓዘበት አወዛጋቢው የሐይማኖት ጉዳይ በእግዚአብሔር ፍቃድ የዓለም ሥርዓተ-እምነት መቋጫውን ያገኛል፡፡
መላው ዓለም በተለያዩ ሐይማኖት ተከፋፍሎ ለሺህ ዓመታት ሲያመልክ ቆይቷል፡፡ የተለያዩ ሐይማኖቶችና ሰባኪያን ፈልቀው ዓለም በተለያየ የእምነት መስመር ኖሯል፡፡ በቴዎድሮስ ዘመን በአቡነ ፀሐይ ዘመን ግን የአባ ሲኖዳ የመጨረሻ ዘመን ራዕይ በገሐድ ይታያል፡፡ መጽሐፉ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን ይዟል እኔ እንዲያውም አስፈሪውን ንግግር ለአንባቢ ትቸ በግርድፉ አካፈልኳችሁ…!!
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከክፉ ነገር ሁሉ ከጥፋት እርኩሰት ይጠብቅልን… !!!