ቂም ያረገዘ አውሬ.. !!!
አሰፋ ሀይሉ
* … “ንጉስሽ ህፃን የሆነ: መኳንንቶችሽም ማልደዉ የሚበሉ አንቺ ሀገር ሆይ! ወዮልሽ!!
መክ 10:16
በግሌ የወያኔዎቹ ናዚ ሽማግሌዎች በዕድሜ ዘመናቸው በሕዝባችን ላይ ለፈፀሙት ግፍና ክፋት ዘሄግ ላይ ቀርበው ሞት ቢፈረድባቸው አያንሳቸውም ባይ ነበርኩ።
አብይ አህመድ ግን የቅርብ አለቆቹ በነበሩት የወያኔ የሥራ ባልደረቦቹ ላይ የፈፀመባቸው አሰቃቂ የግፍ ግድያ ግን ሲዘገንነኝ የሚኖር ነው።
የሽማግሎቹን ግንባር በጥይት ዘነጣጥሎ፣ የተቦዳደሰ ሰውነታቸውን የሚያሳዩ ምስሎችን አደባባይ እያስጣጣ፣ እኔን ያህል ጀግና እያለ ሲያቅራራ፣ ሲፎክር ስመለከት – ምን ዓይነት ከወያኔዎቹ የባሰ አስደንጋጭ አውሬ እላያችን ላይ እንዳወጣን ወለል ብሎ ነው የታየኝ።
ከትግራይ 20 ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ ተብሎ ሲጠየቅ ዓለም በሚያየው ቲቪ ፓርላማ ፊት ቀርቦ “20ሺህ ምን አላት? ይቺ ለኛ ቁርስ ነች! አንድ ሚሊየን ተፈናቅሎብን አይተናል!” ሲል ጆሮዎቼን ማመን ነው ያቃተኝ።
የ20ሺህ ዜጎች ነፍስ በመከራ እየተናጠ “ይቺ ምናላት ቁርሴ ነች” እያለ በአደባባይ ያላገጠ አረመኔ መሪ ኢትዮጵያ ገጥሟት አያውቅም! 20ሺህ ሰው ባንድ ቀን ቢያልቅ ደንታው አይደለም። In fact, እኔን ከነካችሁ በአዲሳባ ባንድ ቀን 100ሺህ ሰው ታርዶ ያድራል ብሎ የነገረንም ሰው ነው።
ባለፈው የወያኔ ደጋፊዎች (የትግራይ ተወላጆች) የሆኑ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ሠላማዊ ሸልፎችን ሲያደርጉ ነበር። ከእነዚያ መሐል መሬት ላይ በመተኛት “ሕዝባችን እየተገደለ ነው፣ ግድያው ይቁም!” የሚል የተቃውሞ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ አሉ። ይሄን ሁላችንም ያየነው ነው።
የሰዎቹ ብስጭት የሠላማዊ ዜጎች ሞት ነው? ወይሰ የፋሺስቱ ወያኔ ሞት? የሚለው ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እንደ ሀገር መሪ ግን አብይ አህመድ የሀገር መሪ ነውና የእነዚያንም የወያኔ አልቃሾች ጩኸትና ተቃውሞ ሰምቶ አግባብ ያለው የጨዋ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል።
ከአብይ አፍ በፓርላማ የተደመጠው ምላሽ ግን አስደንግጦኛል፦ “ከፈለጉ ዕድሜ ልካቸውን አስፋልት ለአስፋልት ሲንደባለሉ ቢውሉ ደንታችን አይደለም፣ ጥጋብ ነው የሚያንደባልላቸው!” የእውነት ስቅቅ ነው ያለኝ። አንድ የሰላም ኖቤል የተሸለመ መሪ እንዴት ለዜጎቹ ጩኸት የዚህን ያክል ንቀት (ዲስሪጋርድ) በአደባባይ ያስተጋባል??
ያ ምላሹ ያስደነገጠኝ ወያኔዎቹን ደግፌ አይደለም። ምናልባት ወያኔ አሸንፋ ቢሆን እነዚያው ሰዎች “ወያኔ ጀግናው!” እያሉ ሲጨፍሩ እናገኛቸውም የነበረ ይመስለኛል። ዋናው ጥያቄ እነሱን የመደገፍና ያለመደገፍ ሳይሆን የአብይ አህመድ አረመኔ ሰብዕና ግልፅ ብሎ የመውጣቱ አስደንጋጭነት ነው።
የዜጋውን ተቃውሞ ወደ አህያ ርታ አውርዶ ሲንደባለሉ ይክረሙ ማለት ለአንድ መሪ አስፀያፊ ነው። በሌላው ዓለም አንድ ሰው ብቻውን ተቃውሞ አለኝ ብሎ ሲወጣ በክብር ችግርህ ምንድነው እናጤነዋለን የሚል ሥልጡንና ትሁት ምላሽ ነው የሚቸረው። እንጂ ስትንደባለል ኑር አይባልም። ነውር ነው። አውሬያዊ ሰብዕናንም ገልጦ ያሳያል።
ያን ባለበት አፉ፣ ሰሞኑን በሚደረግበት መንግሥት መር ሽብርና ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ ገንፍሎ ለሠላማዊ ተቃውሞ የወጣውን የአማራውን ሕዝብ ለቅሶና ጩኸት አብይ አህመድ ሺህ ዓመት ስትጮኹ ብትከርሙ አንዳችም የሚለወጥ ነገር የለም፣ የሥልጣን ጥያቄ ነች፣ ይቺን ዘዴ እናውቃታለን እያለ ነው የተሳለቀው።
የእውነት የእውነት እኔ ግን ሰብዕናውን ስላወቅኩት ምንም ቢል አይገርመኝም ብዬ ገምቼ ነበር። በዚህን ያህል ደረጃ ወርዶ ይበሸቅጣል የሚል ግምት ግን አልነበረኝም። ፈጣሪ ምስክሬ ነው በዕድሜዬ ሙሉ እንደዚህ ዓይነት አረመኔ ደናቁርት ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም! እመቤቴን! ምን ዓይነቱን ሰብዓዊ ስሜት የራቀው አውሬ ነው በላያችን ላይ ያነገሥነው?!! ዕድሜልኬን ሲነደኝ ይኖራል!
ሰብዓዊ ስሜት የሚባል፣ ይሉኝታ የሚባል፣ ርህራሄ የሚባል ያልፈጠረበት፣ ቂም የለበሰ አውሬ ነው ሰውየው። አቋሙን እንደ እስስት ሺህ ጊዜ የሚቀያይር፣ ዛሬ ያቀፈውን ነገ ገሎ የሚቀብር፣ ዘረኛ አቋሙን ለማራመድ አይኑን የማያሽ፣ ለሕዝብ ያለው ንቀትና እብሪት በታሪክ በእብሪቱ ከምናውቀው ከመለስ ዜናዊ ራሱ በሚሊዮን እጥፍ የሚልቅ፣ እጅግ አደገኛና ደም የተጠማ አውሬ ነው።
እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን ደም የተጠማ ቀውስ ዘረኛ እንዴት ባለ ነሆለልነት ወደ መሪነት ወንበር እንዳመጡት የሚያውቁት ሀገር-አውዳሚዎቹ ወያኔ-ኢህአዴጎች ብቻ ናቸው።
ይሄንን ቀውስ አራጅ በጊዜ በቃህ ብለን ካላሰናበትነው፣ በታሪካችን ሰምተናቸው ከምናውቃቸው ሁሉ በከፋ መልክ የሕዝባችንን ደም አፍስሶ፣ ሀገራችንን በታትኖ፣ ህዝባችንን አባልቶ፣ በደም የራሰች መንግሥት አልባ ምድርን እንካችሁ ብሎ ወደአንዱ ሀገር ይፈተለካል!
ይህን ያፈጠጠ እውነት ቸል ብለን፣ በጊዜ ሰውየውን በቃህ ማለት እየቻልን እጃችንን አጣጥፈን ተቀምጠን፣ ሰውየው በሥልጣኑ ቀጥሎ… በህዝባችንና ሀገራችን ላይ ሊመጣ ያለው እጅግ የከፋና የሚዘገንን እልቂትና መከራ ሲወርድብን ግን፣ እውነቱ ታይቶት ሲነግረን ያልሰማነው ኢትዮጵያዊ ብላችሁ ብቻ አስቡኝ። ከዚህ ሁሉ መዓት ፈጣሪ ይጠብቀን።
ይህን የምፅፈው ለታሪክ እንዲቀመጥ ነው።
ይኸው ነው።