>

"ከኔ የተለየ አመለካከት ያለው ሁሉ የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው...!!!"   የኢዜማ  የደህንነት ሰነድ (ደረጄ ገረፋ ቱሉ)

“ከኔ የተለየ አመለካከት ያለው ሁሉ የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው…!!!”  

የኢዜማ  የደህንነት ሰነድ

ደረጄ ገረፋ ቱሉ

ኢዜማ አወጣ የተባለው ሰነድ  ላይ
ሀ የጠቅላይ ሚንስትሩ የውስጥ ጠላቶች
1 የኦሮሞ ብልፅግና
2 የአማራ ብልፅግና
3 የአሮሞ ብሄርተኛ
4 የአማራ ብሄርተኛ
5 የሙስልም አክራሪ አማኞች
6 የኦርቶዶክስ አክራሪ አማኞች
7 የታጠቁ ኃይሎች በተለይ ህወሃት ፣ኦነግ እና ፋኖ
8 የትግራይ ወጣቶች ህወሃትን ስለሚወዱ
9 የኦሮሞ ባለሀብቶች (ኦነግን ስለሚደግፉ)
10 የአማራ ባለሃብቶች( ፋኖን ስለሚደግፉ)
ለ የጠቅላይ ሚንስትሩ ወዳጆች
1 ኢዜማ
2 የኤርትራ መንግስት
የኢዜማ በተባለው  ዶክመንት መሰረት  መፍትሄው ጠቅላይ ሚንስትሩ የደህንነት መዋቅሩን እና የፀጥታ መዋቅሩን በማጠናከር የብሄራዊ ስጋት የተባሉትን  መመንጠር አለበት አይነት ነገር ነው።
ልብ አርጉ ሰላም ለማስፈን ውይይት ፣ድርድር ያስፈልጋል አላሉም። ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ያላቸውን የደህንነት መዋቅር አጠናክረው ይመንጥሩ ነው ።
እዚሁ ላይ ሌላም ነገር ብለዋል። ወታደሩ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ ይችላል። የደህንነት መዋቅሩ በኦነግ እና በህወሃት ተወሯል ።ስለዚህ እነዚህም ይመንጠሩ ዓይነት ነገር አለው። እዚህ ላይ መቼም አንድ ሰው ኦነግ ከሆነ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ነው። ህወሃትም ከሆነ ትግርኛ ተናጋሪ ነው። ስለዚህ በኢዜማ ዶክመንት መሰረት ኦነግ እና ህዋሃትን ለመለየት  ኦሮሚኛ እና ትግርኛ ተናጋሪዎች የተለየ ክትትል ሊደረግባቸው እና መመንጠር አለባቸው።
ባልተያያዘ ዜና የEthio 360 ሰዎች   ፋኖ፣የአማራ ብልፅግና፣የአማራ ባለሃብት ፣አብን ፣የአማራ ብሄርተኛ እና የትግራይ ወጣት እንደ ብሄራዊ  ደህንነት ስጋት ከተወሰደ ቀጥሎ ያለው መመንጠር እና መጨፍጨፍ ነው እያሉ በምሬት ይገልፃሉ።
እሄ ትክክል ነው። አንድ ህዝብ ወይም ቡድን   እያነሳ ያለው ጥያቄ እንደ መብት ሳይሆን እንደ ብሄራዊ ደህንነት ስጋት ከተቆጠረ ቀጣዩ እነሱ እንዳሉት መመንጠር ነው።
ነገር ግን ለነሱ ( ለ Ethio360) የኦሮሞ ብሄርተኛ፣ የኦሮሞ ወጣት በኦነግነት ተፈርጆ ፣የኦሮሚያ ብልፅግና  እና የሙስልም አማኞች አክራር ተብለው በብሄራዊ የደህንነት ስጋት መፈረጅ እና መመንጠር አላሳሰባቸውም። ያው የነሱም አልሸሹም ዞር አሉ ነው።
ሀሳባቸው ኢዜማ በዚህ መልክ ለምን አሰበ ሳይሆን ለምን የኛ የሚሉት የብሄራዊ  ደንነት  ስጋት ውስጥ ተካተቱ ነው።ለምን የኛ ወገን  በኢዜማ  ለምንጠራ ተመለመለ ነው። በኔ አመለካከት የኢዜማ አካሄድ (ከኔ የተለየው በሙሉ የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው እና የችግሮች መፍቻ በሙሉ የደህንነት መዋቅር ማጠናከር እና መመንጠር ነው የሚለው)እጅግ አደገኛ የሆነውን ያህል የነሱም አደገኛ ነው።
ለማጠቃለል
1 ኢዜማ ሸገር ላይ ካላሸነፍኩ ሞቼ እገኛለሁ የሚለው ጠቅላይ ሚንስትሩ ናቸው እንዴ የኢዜማ ሊቀመንበር? ብልፅግና የጠቅላዩ ጠላት እና የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ተብሎ በኢዜማ ከተፈረጀ ቢዬ ነው።
2 ኢዜማ ከላይ የዘረዘራቸውን በሙሉ ስልጣን ቢይዝ ከማንኛውም ጋር ውይይት እና ድርድር አያደርግም ነው ማለት ነው? በቃ ይዘው እየመጡ ያለው መመንጠር ብቻ ነው?
Filed in: Amharic