>

በእስር የሚቆም የነፃነት ትግል የለምና የታሰሩ ንጹሀን ወጣቶች ይፈቱ። (ከዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት የተሰጠ መግለጫ...)

ከዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት የተሰጠ መግለጫ…

በእስር የሚቆም የነፃነት ትግል የለምና የታሰሩ ንጹሀን ወጣቶች ይፈቱ።


የዐማራ ሕዝብ ለተከታታይ ሶስት አስርት ዓመታት በግልጽ ግብር በሚከፍለው ታክስ በሚቆርጥለትና ይመረኛል ጥያቄየን ይመልስልኛል ብሎ ተስፋ የጣለበት መንንግስት ከቦታ ቦታ ሲያሳድደው:ሲገለው:ንብረትና ሀብቱን ሲያወድመውና የመሠረተ ልማት ጥያቄው በዜሮ ተባዝቶ መኖሩ የታወቀ ነው።
 ይሁን እንጅ በየትኛውም ዓለም የባለ ስልጣን ሳይሆን የሕዝብ ፍላጎትና መርህ አሸናፊ በመሆኑ ለተከታታይ ብዙ ዓመታት   የተደረገው የዐማራው ትግል በደንብ ተደራጅቶ ከ2008 – 2010 ዓ.ም ባደረገው ሕዝባዊ ትግልና በንጹሀን ደም ጭላጭል ለውጥ ቢታይም የሰው ደም የፈሰሰበትና ንብረት የወደመበት ትግል ትላንት በታገልናቸው ባለ ስልጣናት ላይ በማረፉ የዐማራ ሕዝብ በሰላሳ ዓመት  ከደረሰው በለይ በዚህ 3 ዓመት ውስጥ  በገፍ ተገድሎ
 በግሬደር ተቀብሯል :ተሳዷል :ታግቷል :ሀብት ንብረቱ ወድሟል።
በመሆኑም ይህ ሕዝብ በደሉንና መከራውን ለሶስት ዓመታት መብቱ እንዲከበር ያለ ወንደሉ መወንጀሉ እንዲቆም በተለያዩ አጋጣሚዎች እመረዋለሁ ለሚሉት ባለ ስልጣንና መንግስት ቢያሳስብም ባለመሠማቱ በመጋቢት ወር ሞት: ስደት : በጅምላ መቀበር:ውርጅብኝ  የደረሰበት የመተከል ወጣት የጀመረው መሞት መፈናቀል በጅምላ መቀበር” በቃን “የሚለው ሕዝባዊ ተቃውሞ እራሱን አስፍቶ ፍኖተ ሰላም:ደሴ:ደብረ ብርሃን: ማርቆስ :ወልድያ:ባህርዳርና በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ሰልፎች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂደዋል እየተካሔዱ ይገኛሉ።
 ይህ በንዲህ እንዳለም የአማራ ክልል መንግስት የሰልፉን ጠቅላላ ሁኔታ በመገምገም በርዕሰ መሥተዳድሩ በአቶ አገኘሁ ተሻገር  በሰጡት መግለጫ በተሰጠበት ጊዜ  ይሄን ብለው ነበር:- በክልላችን የተደረጉ ሰልፎች በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ትልቅ ተሳትፎ ያደረጋችሁ :ወጣቶች አባቶች :የጸጥታ አካላት በጠቅላላው የአማራ ሕዝብ በመላ  በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስም ከልብ አመሥግናለሁ ማለታቸው የማይረሳ ነው።
 ይሄም ይባል እንጅ የርዕሰ መሥተዳድሩ የቃል መግለጫ የጓሮ ድብቅ  አጀንዳ  በተግባር ተለውጦ ሰልፍ በተደረገባቸው የክልላችን ከተማዎች በሕዝባዊ ሰልፉ የወጡ ወጣቶችን በገፍ ወደ እስርቤት በማጎር ይገኛል።
ይህ አካሔድ አደገኛና ለሕዝባችንም ሆነ ለአሳሪ ፓለቲከኞች የማይጠቅም በመሆኑም  የሚከተሉትን መንገዶች መከተሉ ለህዝባችን የሚጠቅም መሆኑን ዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት ያሳስባል:-
 1ኛ. የአማራ ክልል ከፍተኛ የፓለቲካ ባለ ስልጣኖች ይህ ህዝብ ተገፍቶ ተገድሎ ተሳዶ ንብረቱ ወድሞ እናቱ ታርዳ እህቱ ታግታ እንጅ የቅንጦት ጥያቄ ይዞ እንዳልወጣ እናንተ በመግለጫችሁ ያመናችሁት በመሆኑ  ለቀረበው ችግር መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ የህዝብን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው የፓለቲካ ፍላጎታችሁን ለማሳካት ከምትሰሩት ከእኩይ ስራችሁ  እንትቆጠቡ እና የታሰሩ ወንድሞቻችንን ትፈቱ ዘንድ በጥብቅ እናሳስባለን።
2ኛ. የዐማራ ሕዝብ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ በመሆን የክልሉ መንግስት እየሔደበት የለለው   አደገኛና ሕዝብን የማይጠቅም ስሁት መንገድ የሚቆምበትና የሚታረምበትን  ሁኔታ ማስተካከል እንድትችሉና አባታዊ አደራችሁን እንድትወጡ በአጽንኦት እናሳስባለን።
3ኛ. በአማራ ስም የተደራጃችሁ ሲቢክ ማህበራት በሙሉ ወደ አንድ በመምጣት በሕዝባችንና በመንግስት መካከል ያለውን ክፍተት በመመካከር እንፈታ ዘንድ  ጥሪያችን ጽኑ ነው።
4ኛ. የዐማራ ክልል የፍትህ ተቋማት ከዚህ በፊት ከነበረ የፓለቲካ ተጽኖ ወጥታችሁ የሙያ ስነምግባራችሁ በሚፈቅደው መሠረት የዚህን ከውጭ ከውስጥ በግፍ የሚናጥ ንጹህ ሕዝብ ያለምንም ፓለቲካዊ አድሎ በዚህ ወሳኝ ሰዓት የበኩላችሁን እንድትወጡ በታላቁ የዐማራ ሕዝብ ስም እንጠይቃለን።
5ኛ. ዐማራውን ወክላችሁ የዐማራን ሕዝብ መሠረታችሁ አድርጋችሁ የምትታገሉ  የፓለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች :አብን : መኢአድ:አዴሃን: መአሀድ እንዲሁም ለሕዝባችን የምትጨነቁ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ልዩነታችሁን ትታችሁ በጋራ ቁጭ ብላችሁ እንድትመክሩና ስምምነት ለይ በመድረስ በአማራ ሕዝብ ላይ የታወጀውን   መከራና ስቃይ የሕልውና አደጋ  ለማስወገድ  ከሕዝባችሁ ጋር ፍላጎቱን በማክበር በትኩረት ትሰሩ ዘንድ ዓለም ዐቀፍ የዐማራ ኅብረት በጽኑ ያሳስባል።
ዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት
ሚያዚያ 19/2013 ዓ. ም
ለሕዝባችን መብት ኑ እንስራ በኅብረት!!!
Filed in: Amharic