የአቢይዝም ቫይረስ ያላጠቃው የታደለ ነው!
ግርማ በላይ
ዓለማችን ቫይረስ በቫይረስ ከሆነች ሰነባበተች፡፡ የቅርብ ዓመታት ቫይረሶች ግን ኤች አይ ቪን ጨምሮ እጅግ አደገኞችና መድሓኒት ያልተገኘላቸው ናቸው፡፡ ከነዚህ የለዬላቸው የሰው ልጅ ጠላቶች ጎን ለጎን የመጣብን ሌላው አደገኛ ቫይረስ ደግሞ በግለሰቦች የማምለክ ሳይገድል የማይተው ቫይረስ ነው፡፡ ይህን ቫይረስ መቋቋም የሚችል በርግጥም ትክክለኛና ዕድለኛ የሆነ ሰው ነው፡፡ ከዚህ ዓይነቱ ቫይረስ መጠቃት በኋላ ለመዳን እያገገመ የሚገኝ አንድ ብርቱ ሰው አውቃለሁ – “ታማኝ በየነ” ነው በሉና ደግሞ ምሥጢሬን ዘክዝኩት፡፡
አቢይዝም የሚባል ቫይረስ ከሲዖል የመለስ ዜናዊ ቤተ ሙከራ አምልጦ በሀገራችን መሰራጨት ከጀመረ በዛሬዋ ዕለት እነሆ ድፍን ሦስት ዓመት ከ24 ቀናት ሆነው – ያ የተረገመ መለስ ሞቶም አልተወንም ማለት እኮ ነው እናንተዬ፡፡ እናም ቫይረሱም መበከሉን “ፒፕሉ”ም መበከሉን እንደጉድ ተያይዘውታል (በሁለተኛው መበከል ላይ ያለችው “በ” ትጥበቅ)፡፡ አንዳንድ ቫይረሶችን በአንዳንድ ነገሮች መከላከል ይቻላል፡፡ አንዳንድ ቫይረሶችን ግን በምንም ነገር መከላከል አይቻልም ወይም እጅጉን አስቸጋሪ ነው፡፡ የአቢይዝም ቫይረስ እኛን ለመቅጣት ከጥልቁ ባሕር የተላከ ይመስላል፡፡ ቫይረሱ ባልተለመደ ሁኔታ መልከ ቀና በመሆኑ በተለይ ብዙ ሴቶች የተከበረ ምራቃቸውን ለትዝብት እስኪዳርጉ ድረስ አገጫቸው ላይ እያዝረበረቡ እንደሚነፋረቁ አንዳንድ የሚዲያ አውታሮች በማጋለጥ ላይ ይገኛሉ – በተለይ ደግሞ መረጃ ቲቪ ላይ የሚተላለፈው ‹ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር› የተባለው ዋናው መሆኑ ተደርሶበታል፡፡ ተጠቂዎችን እስኪ በጥቂቱ እንቃኝ፡፡
- ከሚዲያዎች እንጀምር – ኢካድፍ የተባለው በፊት የግንቦት ሰባት አሁን የኢዜማ ድረ ገጽ በዚህ ርዕስና በዚህ ቀን በለጠፈው ጽሑፍ እንደጅብራ ከተገተረ መንፈቀ ዓመት ሆነው – “
የህወሓት ጉዳይ — የተገኘው ድል፤ ትልቅ ድል ነው፣ ሆኖም አንዝናና፣ አንዘናጋ! ecadforum November 29, 2020ጦማሮች እና አስተያየቶች ”፡፡ ጓደኛው የኢሳት ድረ ገጽም “ግንቦት 20 ከትግራይ ክልል በቀር በሌሎች አካባቢዎች ሳይከበር ቀረ (ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 20/2011) – ግንቦት 20 ከትግራይ ክልል በቀር በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች አለመከበሩ ታወቀ።” የሚለውን የመጨረሻ ዜናውን ከለጠፈ በኋላ እንደተርኪስ ባቡር ከተገተረ ሁለት ዓመት ሊሆነው አንድ ወር ከሁለት ቀናት ብቻ ቀርቶታል – የሚገርም የአቢይ ባርነት ነው፤ በሕዝብና በሀገር ነፃነት ስም የተደረገው ያ ሁሉ የቀን ከሌት ቱሪናፋና መቅመድመድ ለአንድ ልዝብ ሰይጣን ሲባል ነበር ማለት ነው – አዲዮስ ሀገር! አዲዮስ ሕዝብ! ኢትዮሚዲያና መሰል የቀድሞ የወያኔ የሙሉ ጊዜና የትርፍ ሰዓት ተቃዋሚዎችም በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ፈዘውና ደንግዘው ባሉበት ቆመዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ከበፊትም በበለጠ ቅልጥፍና ሥራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ከነዚህም በፊደል ተራ ቅደም ተከተል መሠረት ኢትዮሪፈረንስ፣ ኢትዮኢክስፕሎረር፣ ኢትዮላየን፣ ዘሀበሻና ማለዳታይምስ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ “ስንቱን አየን!” አለች አሉ ቦለቅያ፡፡ (ቦለቅያ በራያዎች የሴቶች ጪሳጪስ መሞቂያ ምድጃ ናት፡፡) - በግለሰብ ደረጃ ካየን ሁኔታው ይዘገንናል፡፡ ቀድሞ እንደፈረንሣይ ሽቱ አልባብ አልባብ ይሉ የነበሩ ግሩም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ዛሬ ነገሩ “ሲያልቅ አያምር” እንዲሉ ሆነና እንደገማ ዕንቁላል ከሩቁ የሚቆንሱ ለእግዜር ይማራችሁ እንኳን የማይመቹ ሆነዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የተወሰኑትን በስም መጥራት ለወደፊቱ እንደሸንበቆ ወጥተው እንደሙቀጫ እንዳይንከባለሉ ጥቂቶችን በማስተማር ረገድ አቅጣጫ ያስቀምጣልና መጥፎ አይደለም፡፡ አካሄዳችን ሁሉ እያስጠላ በመምጣቱ ይህን ማስታወሻ በግልጽና በድፍረት የምጽፍበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነው ያለ፡፡ (የወያኔን አማርኛ መኮረጄን ሳትረዱልኝ ከቀራችሁ መቼስ በከንቱ ለፋሁ ማለት ነው፡፡)
2.1 አለማየሁ ገረማርያም (“ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ” ያስባለን በአፍ ጂዶ ጉድ የሆነ የወያኔ ዘመን የነጻነት ተጋዳላይ)
2.2 ሲሳይ አጌና (ከንቱ ውዳሤ ያበላሸው፣ ምናልባትም ተደብቆ የነበረ የዘረኝነት ውርዴ እንደኩፍኝ ያገረሸበት ምሥኪን)
2.3 ብርቱካን ሚዴቅሣ (ምናልባት የ“ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” እና በእጅ አጨባበጥ የንክኪ ማፍዘዣ የተመረዘች ምሥኪን)
2.4 ዝንታለም ዳቆን ዳንኤል ክስረት ( በንክኪ በሚተላለፍ ማፍዘዣ ቅብዓ-ሣጥናኤል መርገመ ነፍስ ወሥጋ የተነደፈ)
2.5 ብርሃኑ ነጋ (በፀረ አማራነት የጋራ አቋም ተማርኮ የአቢይዝምን ቫይረስ አብሮ የፈጠረና ለሚለው ሳይሆን ለሚመኘው የሥልጣን አምሮት ለመሞት የቆረጠ፣ ለንግግሩና ለተግባሩ ኅብረትና ሥምረት እንደቫይረስ ልጁ ግድ የማይሰጠው)
2.6 ዮናስ ዘውዴ (በአፍ ጂዶ የተመታ ታዳጊ ቫይረስ፣ በሥልጣን ተስፋ በለደለደ ሞራል ከእውነታው ያፈነገጠ ምሥኪን)
2.7 ምሕረት ደበበ (በአፍ ጂዶ የተመታና የአሁኑን ሁኔታ የማላውቅለት)
2.8 ግዛው ለገሠ (በአፍ ጂዶ የተመታና አሁንም በቫይረሱ ፍቅር የሚንገላታ ምሥኪን የቤተ መንግሥት ተወዛዋዥ)
2.9 መሣይ መኮንን (በአፍ ጂዶ የተመታና ከበሽታው ለማገገም በመፍገምገም ላይ ያለ – እመብርሃን ትጎብኘው!)
2.10 አገኘሁ ተሻገርና አብዛኛው የበድኑ ብአዴን አመራር አባላት ( የይሁዳን የክርስቶስ ሽያጭ የ30 አላድ የብር ምንዛሬ የቀመሱና ቫይረሱ በመሀከላቸው ገብቶ አዚሙን የጣለባቸው የሀገር ሸክሞች፤ በመጨረሻም የመዘበሩትን ሳይበሉ ጨርቃቸውን ጥለው የሚያብዱ ወይም አማራን ለማጥፋት ባደረጉት ወያኔያዊና ኦህዲድ/ኦነጋዊ ትብብራቸው በጉጉት በምንጠብቀው የነፃነት ሠራዊት በሰፈሩት ቁና የሚሰፈርላቸው፡፡ ( በነገራችን ላይ እግዚአብሔርም በአነጋገር ድፍረቴ ይቅር ይበለኝና አገኘሁ ተሻገር ልክ እንደ ደብረፅዮን ገረሚካኤል ዘገምተኛ ነው፤ የፊት ገጽታውንና ሲናገር የሚያሳየውን የተለዬ እንቅስቃሴ እዩና እናንተም ፍረዱ፡፡ (ወልጄ እንደሁ ጨርሻለሁ) አፈሩን ገለባ ያድርግለትና “የውጪው የውስጡን ይናገራል” ይል ነበር አንዱ አጎቴ፡፡)