አሳምነው ደጀኑ
ስለአገር አንድነት ተግተን…መፋፋት
ስለመለያየት ሰርተን ብን ብለን መጥፋት
የሶሪያን የወርደት ፅዋ መጋት
አባቶቻችን እርስ እርስ ተጣልተዋል፤ ተዋግተዋልም፤ ግን በጠባቸው መካከል እንኳን ለሃገራቸው ተባብረዋል እንጅ ምንጊዜም ሕልውናዋን ለጠላት አሳልፈው ሰጥተዋት አያውቁም” ይልቅ የውጭ ጠላት በመጣ ጊዜ ልዩነታቸውን ወደጎን ትተው፣ ነገራቸውን ከሆዳቸው ከተው፣ ልባቸውን በጀግንነት ቀለም ተነቅሰው ሀሞታቸው በኢትዮያዊነት ወኔ ሞልተው፣ ክንዳቸውን አንድነት መንፈስ ቃኝተው፣ከጠላት ተፋልመዋል። ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ዳር ድንበራቸውን አጥንተው፣ ነፃነታቸውን አስከብረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በነፃነቷ ቆማ፣ በኩራት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስትተላለፍ ዛሬ ላይ ደርሳለች።
ጠላቶቻችን ሁሌም የሚያጠቁን አንድነታችን በላላበት፣ እርስበርስ መኖቆራችን በጋመበት ወቅት ነው። በእንዲህ ያለው ወቅት ታዳያ ቱርከና ግብጽ መጥተው ሄደዋል፤ፖርቱጋል መጥቶ ሄዷል፤ እንግሊዝ መጥቶ ሄዷል፤ ኢጣልያ ጥቶ ሄዷል፤ ጠላቶች እየመጡ በመጡበት ተሸኝተዋል፤ ወዳጆች በጨዋነት ተስተናግደው ተዋኅደዋል። ዛሬም የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ለጠላቶቻችን ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
ጠላቶቻችንም ሁኔታውን ተረድተው እንደ ቀትር ጋኔን ሊቀራመቱን አሰፍሰፈዋል፣ እንደ እምቧይ ካብ በገዛ እስትንፋሻችን ሊንዱን ቆርጠው ተነስተዋል። በአደባባይ ዝተዋል። ግና ፊትለፊት እንዳይገጥሙን ፈርተዋል። አዎ የሽንፈትን ፅዋ ደጋግመው ጨልጠዋልና፣ እንደ አቶን የሚፋጀውን የአባቶቻችንን የአንድነት ክንደ ቀምሰው አፍረው ተመልሰዋልና እንዴት ፊትለፊት ይገጥሙናል።
አዲስ ዘዴ ባይሆንም እርስበአርሳችን ማባላትን የሙጥኝ ብለዋል። የከረመ የጓዴ ቂም እየጎተትን ያጋምነው የጥላቻ ፍም እያራገብ ማጋም። ቆያው ፍጅቶ እስኪማበጀት። የጥላቻ እነጨት እየቆሰቆሱ ማፋም።
በተሳሳተም ይሁን በእውነተኛ ትርክት ላይ የተመሰረተውን የታሪክ ንትርክቻንን በጥላቻ ስብከት በማካረር፣ አንዳችን በአንዳችን ላይ ማነሳሳት፣ በቅጥር ነፈሰ ገዳዮች ብሔር መርጦ በገፍ እና በግፍ ማስገደል። ከዚያም የአከሌን በብሔር የከሌ ብሔር ገደለው በማለት ለእርስ በእርስ ፍጅት የግጥሚያ ሜዳ ማበጀት። መጨረሻም የገበያ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንዲሉ እኛ በግርግሩ ተፋጅተን እናልቃለን። የአባቶቻችን አደራ እነደ ድመት ልጅ በልተን ክብራቸውን አናዋርዳለን። አገራችን በማፍረስ የሊቢያን የውርደት ሸማ እንደርባለን። የሶሪያን የውድቀት ፅዋ እንጨልጣለን ። ከአፍሪካ የአረፋት ተራራነት፣ የነፃነት ኩራት ምንጭነት በጩኸት እንደፈረሰው የእያሪኮ ግምብ ወደ ፍርስራሽ ትቢያነት እንቀየራለን።
እነርሰሱ ደግሞ ከትቢያው እንዳንነሳ ይተጋሉ የአገራቸውን ጥቅም በእኛ የውረደት አሰከሬን ላይ ያበጃሉ። እና ምን ይበጃል አትሉም! አላችሁ..
የሚበጀውማ የውስጥ ጉዳያችንን በሆዳችን ከትን፦
ለኢትዮጵያ አንድነት መትጋት፣ ከአባቶቻችን የክብር ማማ መውጣት፣ የአፍሪካ የአረፋት ተራራ ተምሳሌትነትን ዳግም መቀዳጀት..እንደቀድሞው የአፍሪካ የነፃነት የኩራት ምንጭ ሆኖ መገኘት።