>

አሜሪካ "የአማራ ኃይል ለቆ ይውጣ" በሚል አቅም ገፍታበታለች...!!! (አህመድ ሱሌይማን)

አሜሪካ “የአማራ ኃይል ለቆ ይውጣ” በሚል አቅም ገፍታበታለች…!!!

አህመድ ሱሌይማን

 

 *….ከሰሞኑ በኢትዮጲያ ላይ ጫና ለማሳደር በአዲስ መልክ ወደ ሥራ እንገባለን ያለችው አሜሪካ፣ ዛሬ በውጭ ጉዳይ መ/ቤትዋ በኩል እንቅስቃሴዎችን መጀመርዋን አስታውቃለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ከጠሚው ጋር ሰኞ ዕለት በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን እና አብይ ባለፈው የኤርትራ ሠራዊትን ከኢትዮጲያ እንዲወጡ አደርጋለሁ ብሎ የገባውን ቃል ኪዳን ባለመጠበቁ ማዘናቸውን እንደገለጡለት ታውቋል። ዛሬ ደግሞ ከኤርትራ ሠራዊት ጋር የአማራ ኃይል በፍጥነት ለቅቆ እንዲወጣ አሜሪካ አሳስባለች ተብሏል።
******
ያልገባኝ ነገር፣ ኤርትራስ እሺ በሰው አገር ጣልቃ የገባች እራሷን የቻለች አገር ስለሆነች ትውጣ ብትባል ያስኬዳል። የአማራ ኃይልን ግን ውጣ የሚሉት ከየት ነው? ከጎንደር እና ከወሎ ነው? የአማራ ኃይል ተከዜን መች ተሻግሮ ሄደና ነው ካሁኑ ጋር በተደጋጋሚ እንዲወጣ አሜሪካኖች የሚገፉት? አውቃለሁ አብይን ጨምሮ የኦሮሙማው ክንፍ በኤንባሲዎቻቸው እና በሚገናኟቸው የዲፕሎማቲክ ሰዎች በኩል የአማራ ኃይልን እንደሚያጠለሹና ስሙን በእነርሱ ፊት እንደማይከላከሉለት።
ነገር ግን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አናት የተቀመጠው ደመቀ መኮንን እንደመሆኑ ይሄ የአሜሪካኖች በአማራ ኃይል ላይ የሚነዙት ውዥንብርና ውንጀላ ስህተት እንደሆነ አስረግጦ ማስረዳትና ይህ አይነት ነገር ለግንኙነታቸው መሻሻል ሲባል መደገም እንደሌለበት መንገር ለምን አቃተው? (በአንድ በኩል ሲነግራቸው በሌላ በኩል አብይ እያፈረሰበት ይሆናል)።
ደመቀ መኮንን ባለፈው አንድ ጊዜ ያንን ለማድረግ የሞከረ ቢሆንም አሜሪካኖች በአማራ ኃይል ላይ የነከሱትን ጥርስ ባለመንቀላቸው፣ ኃይሉ አገራዊ ሀይል መሆኑንና “ይውጣ” የሚባልበት ምንም አይነት ምክኒያት ሊኖር እንደማይገባ በአንክሮ በመንገር ላይ ከከዚህ በፊቱም በበለጠ መልኩ ከፍ ያለ ሥራና እንቅስቃሴ ሊያደርግ ይገባል እላለሁ።
Filed in: Amharic