>

"ወይ ድርድር እንዲካሄድ እናስገድዳለን ካልሆነ ዶክተር አብይን እናስወግደዋለን....!!!" ምዕራባውያኑ - ክፍል ሁለት

“ወይ ድርድር እንዲካሄድ እናስገድዳለን
ካልሆነ ዶክተር አብይን እናስወግደዋለን….!!!”
ምዕራባውያኑ – ክፍል ሁለት! 
ደጀኔ አሰፋ

ኢትዮጵያ በምዕራባውያኑ ለምን ጥርስ ተነከሰባት?!?
#4ኛ) ኢትዮጵያ ከጥንት ወዳጇ ሩሲያ እና ከቻይና ጋር ግንኙነቷን ማጥበቋ ጥርስ አስነክሶባታል::
በዚህ ወቅት ምዕራባዊያኑ ጁንታውን ለመታደግ የሄዱበት ርቀት በኢትዮጵያ ታሪክ በክህደት የሚመዘገብ ነው:: በኢፍትሀዊ ጫና እና በሰብአዊ መብት ሽፋን subtle የሆነውን እቅዳቸውን ለማሳካት ያላደረጉብን የለም:: ታዲያ ሩሲያና ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ቆመዋል:: ከኢትዮጵያ ጋርም ግንኙነታቸው ጠብቋል:: ይህ ለምዕራቡ እንቅልፍ ነስቷል:: ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ጭምር የማጣት ከባድ ስጋት አላቸው:: ስለዚህ ከወዲሁ ኢትዮጵያን በማተራመስ እና በማፍረስ ቻይና እና ሩሲያ አፍሪካን እንዳይቆጣጠሩ ሩጫቸውን እንገታለን የሚል እቅድ ይዘው ነው እየሰሩ ያሉት:: ቀጠናው እንዲረበሽ ይፈልጋሉ:: የቀጠናው ምሰሶ የሆነችውን ኢትዮጵያን በማተራመስ ቀጠናውን መረበሽ እና እነሱ የሚፈልጉትን ደካማ እና ተላላኪ መንግስት መሰየም ይህ ካልሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን መበታተን የሚል እቅድ ይዘው ነው እየተጉ ያሉት!!!
.
#5ኛ) ኢትዮጵያ የቀጠናውን ሃገራት እያስተሳሰረች በመሆኑም ጥርስ ተነክሶባታል:: በተለይም ከኤርትራ እና ከሶማሊያ ጋር የመሰረተችውን የሶስትዮሽ ቅንጅት ፈፅሞ አልወደዱትም:: “ይች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም” በሚል ዓይነት ስሌት ምዕራባዊያኑ ለበቀል ተነስተዋል:: ምክንያቱም እነሱ የሚፈልጉት ቀጠናው በደካማ መንግስታት እንዲመራ: ባሻቸው ሰዓት ግጭት እየቀሰቀሱ አስታራቂ መሆን: የቀጠናውን የተፈጥሮ ሃብቶች ነዳጅን እና ሌሎች ማዕድናትን ጨምሮ መበዝበዝ: በቀጠናው (ቀይ ባህርን ጨምሮ) የሚኖራቸውን ተፅዕኖ አሳድገው ያሻቸውን እያዘዙ መኖር: ወዘተ ነው:: ለዚያም ነው በዚህ ወቅት በዋናነት በኢትዮጵያ ላይ ቀጥሎም በኤርትራ እና ከዚያም በሶማሊያ ላይ ጫና እየፈጠሩ የሚገኙት:: ኢትዮጵያን እና ኤርትራን አስጨንቀው ከረሙ:: ይሄው ጥቂትም ቢሆን ተረጋግታ የነበረችውን ሶማሊያንም ማመስ ጀምረዋል:: ከዚህ ትርምስ ጀርባ እንግሊዝ እንዳለች ተነግሯል:: ምዕራባውያኑ ተቅበዝብዘዋል:: አውሮፓ ህብረትም ለኤርትራ ሊሰጥ የነበረውን እገዛ ለሌሎች ሃገራትና ከትግራይ ተፈናቅለው ሱዳን ለተሰደዱ እሰጣለሁ ብሏል:: ሃቬስቶ ሱዳን ሄዶ የአሉላ ሰለሞንን እናት እና እህቶቹን ኢንተርቪው አድርጎ ተጨዋውቶ እንደተመለሰ የሚታወስ ነው:: ትግራይን እንደ ሃገር የመቁጠር ዝንባሌያቸው ቀጠናውን ለማስረበሽ እንዲሁም ታማኝ ሎሌ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የመነጨ ነው:: ትህነግ የምዕራባውያኑ ጉዳይ አስፈፃሚና ታማኝ ተላላኪ እንደነበር ይታወቃል:: ለዚያ ነው ጁንታው እንዲነሳ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የሌለው:: በአንፃሩ ዶክተር አብይም ሆነ ኢሳያስ አለያም ፈርማጆ ስማቸው በዚህ የሚነሳ አልሆኑም:: ስለዚህ የሶስቱን መሪዎች ስም በአደባባይ ያብጠለጥላሉ:: ሶስቱን መንግስታት ለማስወገድ ቀንተሌት ይሰራሉ:: Authoritarian governments ይሏቸዋል:: “ሌጅትሜት ያልሆኑ አምባገነኖች” እያሉም ይከሷቸዋል:: እሽ ሌጅትሜት ለመሆን ምርጫ ላካሂድ ሲባሉ ደግሞ ምርጫን ለማስተጏጎል ይሰራሉ:: ምክንያቱም ዓላማቸው ሌላ ነው!
.
#6ኛ) ሃገራዊ ምርጫን ለማካሄድ ማቀዳችን ምዕራባዊያኑን በትልቁ እረፍት ነስቷቸዋል:: ምርጫ ማለት ህዝቦች የሚፈልጉትን መንግስት የሚመርጡበት ሂደት ነው:: የተመረጠው መንግስትም ቢያንስ በፖፑላር ቮት የሚገኝ ሌጅትሜሲን ያገኛል:: ሌጅትሜት የሆነ (በካርድ) የተመረጠ መንግስት ደግሞ ነገሮችን ለማድረግ የሚያስችል የተሻለ የሞራልም የህግም አቅም ይኖረዋል:: ትልልቅ ሃገራዊ ውሳኔዎችን ማሳለፍ ይችላል:: በህዝቡ ፈቃድ ከባድ የሚባሉ ለውጦችን/ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ እድልን ያገኛል:: “ያልተመረጠ መንግስት” እየተባለ ሊብጠለጠልም አይችልም:: ስለዚህ ይህ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ያላቸውን አቅም ተጠቅመው ማደናቀፍ ይፈልጋሉ:: አኩራፊ ሃይሎችን ከመደገፍ ጀምሮ የንፁሃንን ግድያ በማካሄድ: ሃገርን በማወክ እና መንግስትን በተለያየ ጫና በመወጠር ምርጫውን ለማቋረጥ ተናበው እየሰሩ ነው:: ምርጫውን ማቋረጥ ግን አይቻልም!!!! ብዙ ዋጋ የተከፈለበት : በመቶ ሺህ ኢትዮጵያውያን የሞቱበት: ይህ ቀን እንዲመጣ አያሌ ዋጋ የተከፈለበትና የዘመናት ውጤት የሆነው ምርጫ የመጣው ቢመጣ የተከፈለው ተከፍሎ ሊካሄድ ይገባል:: መንግስትም ግልፅ አድርጏል:: ጥሩ ነው!!! ምርጫውን አድርገን ግድባችንን ሞልተን እስክንገላገል ድረስ ግን ፈተናችን መጨመሩ እንደማይቀር እናስብ እንዘጋጅ!!! በዚያ ላይ ከምርጫው በኃላ መንግስት ከስልጣን ያነሳኛል ብለው የሚያስቡ የብልፅግና ባለስልጣናትም የሴራው አጋር መሆናቸውን ልብ ማለት ያሻል!!! በተለይ በእንዲህ ያሉት ላይ ምርጫን ከመጠበቅ ዛሬውኑ እርምጃ መውሰድ የተሻለ ነው!!!!
.
ዛሬ በሃገራችን የምናያቸው ነገሮች ከጀርባቸው ብዙ ባለድርሻ አካላት ያሉበት ነው:: ተራ ግጭት አይደለም:: ድንገተኛ ኩነትም አይደለም:: ዛሬ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና መንግስት አልባ ለማድረግ በቀኝም ይሁን በግራ የተሰለፈው ሃይል ዘዋሪ አለው:: የሚሾፍረው አለ:: መጀመሪያ ይህን … ቀጥሎ ያንን … አድርጉ እያለ እቅድ አውጥቶ በገንዘብ እና በቁሳቁስ አግዞ የሚያሰማራው አካል አለ:: በተቀናጀ ሁኔታ ነው እየተሰራ ያለው:: ግራ እና ቀኙ ይናበባል:: ቋንቋውና ጥያቄው የሚለያይ ይምሰል እንጅ ግባቸው አንድ ነው:: የመንግስትን እጅ ጠምዝዘው “ብሄራዊ ድርድር” ይካሄድ የሚል ነው:: በዚህ ወቅት ግን #ድርድር ማለት ምርጫው ቀርቶ ጁንታውም ጭምር ሽፍታውም ወንጀለኛውም ጭምር የመንግስት ስልጣን ይካፈል ማለት ነው:: ደካማ መንግስት ይፈጠራል ማለት ነው:: ይህ ማለት በምዕራቡ እጅ ወደቅን ማለት ነው:: ከዚያ በኃላ ብዙ ብዙ እንሆናለን:: መጫወቻ ሆንን ማለት ነው:: ከግራ እና ከቀኝ ወከባው የበዛው ለዚህ ነው:: ይህን እድል አሁን መጠቀም አለብን እየተባለ ያለው ለዚሁ ነው:: እውነት ነው ችግር አለ:: ነገር ግን ችግሩን ተንተርሰው ችግሩ እንዲባባስ እንጅ ችግሩ እንዲቀረፍ ሲሰሩ የማናይቸው ለዚህ ነው:: ለዚያም ነው የህዝብ ለህዝብ ፍጅት እንዲከሰት እርስበርስ እንድንባላ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ እያራገቡ ያሉት:: ይህን የምለው ይህን ጉዳይ በእቅድ ለሚያስተባብሩ እና ለሚያራግቡ በግራ እና በቀኝ ተሰልፈው ኢትዮጵያን ወደ ትቢያነት እንቀይራለን ብለው እየሰሩ ላሉ አካላት እንጅ በቅንነት እና በንፁህ ህሊና ወገኔ ተጎዳብኝ ብሎ እውነተኛ የፍትህ ጥያቄን ለሚያቀርበው አይደለም:: እውነተኛ የህዝብ ጥያቄ ሳይውል ሳያድር ሊመለስ ይገባዋል!!!! የንፁሃን ሞት መቆም አለበት!!! መቆም አለበት!!! እያውራሁ ያለሁት ከጀርባ ስላለው ሴራ እና በንፁሃን ደም እየተሰራ ስላለው አስፀያፊ ሸፍጥ ነው!!!! ድርድር እንዲካሄድ የንፁሃንን ህይወት ማጥፋትም ሆነ እንዲጠፋ የሚያደርግ ስራን መስራት በምድርም በሰማይም እርም ነው!!! ነውር ነው!!! ደግሞም አይሳካላችሁም!!! ይህን ሸፍጥ በቀኝም በግራም ያለው ኃይል እንዴት እየተጠቀመበት እንዳለ በሚቀጥለው ፖስት አካፍላለሁ:: አገራችንን ለአደጋ እያጋለጡ ያሉ ትሮጃን ሆርሶችን ማጋለጥ ትንሹ የዜግነት ግዴታ ነው!!!! ይህ የሳይለንት ማጆሪቲው ድምፅ ነው!!! ለማይናገረው እናገራለሁ!!! ስለ አገራቸው ግድ ለሚላቸው አካፍላለሁ!!! ምክንያቱም ሀገር የምትጸናው ፈተና በመጣ ቁጥር በሚደነብሩት አለያም በሚያጋግሉት ሸፍጠኞች ሳይሆን ይሄንንም ጫና እንወጣዋለን በሚሉት እውነተኛ ዜጎቿ ብርታትና ቁርጠኝነት ነው!!!! አሁንም እንላለን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!! እውነት ያሸንፋል!!!! እንሻገረዋለን!!!!
Filed in: Amharic