“ብአዴኖች ስልብ ናቸው!
ከጅምሩ ለስልጣን ሲታጩም ክብራቸውን፣ ወኔያቸውንና ማንነታቸውን በሙሉ ተሰልበው ነው”
መስከረም አበራ
ስናጠፋ ቆንጥጡኝን ያለው አብይ አህመድ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለምን ፎቶዬ ተዘቀዘቀ በማለት በአጎብዳጅ የአማራ መሪዎች በኩል ወጣቶችን እያሳሰረ ነው። በሰላማዊ ሰልፍ ሳይሆን በምርጫ ስልጣን እንደሚያዝም እየነገረን ነው። እንዴት ራሱ በህዝብ ተቃውሞ ወደ ስልጣን እንደመጣ ይረሳዋል? ሰውዬው ሾርት ሚሞሪ ነው ያለው።
ችግራችን በይስሙላ ምርጫ ቢፈታ ኖሮ፣ ወያኔም 5 ጊዜ ምርጫ አድርጎ ነበር እኮ! ታላቁን የአማራ ህዝብ አጎብዳጅ በሆኑት የአማራ ክልል መሪዎች ሚዛን ልክ ማየት ዋጋ ያስከፍላል። የአማራ ህዝብና የብአዴን አመራሮች ለየቅል ናቸው። ብአዴኖች ስልብ ናቸው፤ ወደ ስልጣን ሲወጡም ክብራቸውን፣ ወኔያቸውንና ማንነታቸውን ተሰልበው ነው።