>

በትንሳዔ በዓላችን ለመንግሥት ባለሥልጣናት  ትድረስልኝ...!!! (መምህር ፋንታሁን ዋቄ)

በትንሳዔ በዓላችን ለመንግሥት ባለሥልጣናት  ትድረስልኝ…!!!

መምህር ፋንታሁን ዋቄ

*…. እፈሩ!!! ነውር እወቁ! ሕሊናችሁን አድምጡት! ሕዝብ በጣፋጭ  ከረሜላ የሚያታልሉት የሕፃን ስብስብ አይደለም! እባካችሁ በእጃችሁ ላይ ያለችውን አንዲትና ውድ አገራችንን እቃ እቃ አትጫወቱባት!!!
የትንሣዔን በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት የምታስተላልፉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሚናችሁን ለዩ። አንኳን አደረሳችሁ እያላችሁ የምንገደለውን ኦርቶዶክሳዊያን አትቀልዱብን። ሥራችሁ ላይ አተኩሩ።
ይህ መልእክት ባለቤቱ  የቅዱሳን ፓትሪያርኮችና ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ነው። ሽንገላ ይሰለቻል።
ከእናንተ የምንጠብቀው የአፍ ሰላምታ አይደለም። በተግባር የሚታይ የሰላም ዋስትና መስጠት ነው። የእናንተ ሥራ
(1)  ጨፍጫፊውን ለፍርድ ማቅረብ
(2) ተፈናቃዮችን መልሳችሁ በነበሩበት አቋቋሙማችሁ በቤታቸው በዓለ ትንሳዔን እንዳያከብሩ ማድረግ
(3)  የኦሮሚያ መንግሥት ያልተጻፈ ዘር የማጽዳት ፖሊሲንና ለእርሱ በር የከፈተውን ሕገ አራዊት መሠረዝ
(4) በውጭ ጠላት እንዳንጠቃ እኛን አንድ ቤተሰብ ማድረግ
(5) ሁሉንም አክራሪነት፣ ከፋፋይነት የሚጠቀሙ እምነቶችና የፖለቲካ ርእዮቶች  በሕግ ማገድ ነው።
እፈሩ!!! ነውር እወቁ። ሕሊናችሁን አድምጡት። ሕዝብ በጣፋጭ  ከረሜላ የሚያታልሉት የሕፃን ስብስብ አይደለም። እባካችሁ በእጃችሁ ላይ ያለችውን አንዲትና ውድ አገራችንን እቃ እቃ አትጫወቱባት።
 ንስሐ ግቡና እናንተ ኮረፕት ያደረግኋቸዋቸውን ሳይሆን እውነተኞቹን የነባር ባህሎችና እምነቶች ሊቃውንትና ሽማግሌዎች ጠርታችሁ አገራዊ መንገድ ቀይሱ።  ይመክሯችኋል። በባዕድ ትምህርት ቃርሚያ ኮርስ ባገኛችሁት ድግሪ ብቻ ይልን ውስብስብና ድንቅ አገር ለመምራት አትሞክሩ።
በምናብ ስላችሁ እየቃዣችሁ ልትፈጥሯት የምትፈልጓትን አዲሷን የሞት አምራች ኢትዮጵያን ተዉአት። ቁማራችሂን ከውጭ ጠላት ጋር እንጂ በእኛ በዜጎች ላይ አትጫወቱ።
#ከብዙ ለትንሳዔ በዓላችን ከሚቀርቡልን  የመልካም ምኞት መልዕክቶች መካከል የማንን አሜን እንበል??
መጀመሪያ እኔ እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን  ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሳዔ ዋዜማ ቅዳም ስዑር አደረሳችሁ። እላለሁ። አሜን።
====
አሜን የምንለው የፓትሪያርኮቻችንን፣ የብፁዐን ላሊቃነ ጳጳሳትን፣ የካህናቶቻችንን፣ የክርስቲያን ምእመናንን፣ የአገር መሪዎችን (ያለ አድልዎ ለሁሉ እንደ እግዚአብሔር እረኛና መጋቢ ከሆኑ)፣ የሚያከብሩን የሌላ እምነት ተከታዮቻን ይሆናል።
ነገር ግን የምንጠነቀቃቸውና ዲያብሎስ ሔዋንን ለማታለልና የሞት መዕድ ሊጋብዛት፣  ይሁዳ ጌታን በመሳም ለገዳዮች አሳልፎ ለመስጠት እንደተጨቀመበት ሰላምታ መራቅና እክኸደከ ሠይጣን ልንለው የሚገባ አለ።
=+++++++++++
# ለኦርቶዶክሳዊያን ስንት አይነት እንኳን አደረሳችሁ የየሚልኩ ተዋንያን ያሉ ይመስላችኋል?
======
ዘፋኞች ከንስሐ ሊያርቁንና ለሞት ሊያልጡን ይህንኑ ይላሉ፤ ነጋዴው ሸቀጡን ሊሸጥልን ይጠቀምበታል፣ ፖለታከኞች ለማደኝዘዣነት ይፈልጉታል።
ከሁሉ የከፋው አዲሱ ገዳይ ፖሊሲ ፈጻሚ ሲለው ግን ???ግብረ ይሁዳ እየሳሙ ማስገደል ሥራቸው የሆነውም ያለኃፍረት “ሰላም” ይላሉ።  እኛ ግን የሽንገሌውን  ከሃይማኖታዊ  እና ወዳጆቻችን ሰላምታ ለይተን አሜን እንላለን።
===========
አሁን የባሰው —-
የፕሮቴስታንትና የዉሀቢ ጥምረት የፈጠረው የፖለቲካ ፍጡሩ “ኦሮሙማ” መሪዎችም  ከግድያቸው የተረፍነውንና ወረፋ የምንጠብቀው ክርስቲያኖች ብቅ ብለው “እንኳን አደረሳችሁ” baga nagaan geessan  (በገ’ ነገኣን ጌሰ’ን)  ይሉናል። እንኳን ለሚቀጥለው እርድ ቆያችሁን እንደማለት ይመስላል።
ባይሆን ኖሮ የሻሸመኔን፣ የዶዶላን፣ የኮፈሌን፣ የሐረርን ወዘተ ተፈናቃዮች መልሰው አቋቋቁመው ክሰው በዓመቱ እእኳን አደረሳችሁ ይሉ ነበር።
ግብረ ይሁዳ እየሳሙ ማስገደል ይሉሃል ይኽ ነው።
እነርሱ መልካም ምኞትን የሚጠቀሙበት ፀረ ኦርቶዶክ፣ ፀረ ሸዋ፣ ፀረ ቦረና፣ ፀረ ሱኒ ኢስላም፣ ፀረ-አማራ  መሆናቸውን አውቀን አንድ ሆነን እንዳንቆም ማዘናጊያ ነው።
ሌሎቹ አርቲስቶች፣ ነጋዴዎች፣ መናፍቃንና አምላክ የለሽ ፖለቲከኞች ናቸው። እነዚህም እንዱሁ ለአጀንዳቸው መሰካት ሰላምታን  ይጠቀሙበታል።
በሞት መካከል እያስደነሰ እንደ ኖኅ  ዘመን ሰዎች   ወደ መርከቢቷ ወደ ንስሐ አንዳጠቡ አርቆ ለሞት የሚያስጠብቀን አርቲስትም እንኳን አደረሳችሁ ይለናል። እኛ ደንዝዘን ለሁሉም ገበያ ሆነናል። ባንኮች እንድንበደራቸው፣ ነጋዴዎች ቀኖና-የለሽ ፈጂዎች (unbridled nsumers) እንድንሆንላቸው ነው፤ መናፍቃን በሐትና በእውነት መካከል ያለውን ድንበር እንዳንለይ ሰላም ይሉናል። ዘረኞች የክርስቶስ ዘር መሆናችንን ዘንግተን እንድንጠጋቸው ሰላም ይሉናል።
ከድንዛዜ የመንነቃበት የትንሳዔ በዓል ያድርግልን!!!!
እግዚአብሔር በዕለተ ትንሳዔው ከሞት መንገዳችሁ ይመልሳችሁ። ከቅዠታችሁ ያንቃችሁ።
Filed in: Amharic