>

የወያኔና የኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት መፈረጅ አንድምታው...!!! (አስጨንቅ በጓንዴ)

የወያኔና የኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት መፈረጅ አንድምታው…!!!

አስጨንቅ በጓንዴ

ወያኔ የሚባል ድርጅት ያለ መሆኑ ግልጽ ነው። ምክንያት በአካልም በመንፈስም የሚታወቅ፣ ለሚወስደው እርምጃ ኃላፊነትን የሚወስድ አካል ያለ ስለሆነ። ወያኔ በአለም ዓቀፍ ተቋማትም ዕውቅና ያለውና ከመንግስት ጋርም ድርድር እንዲያደርግ ግፊት ሲደረግ የነበረ መሆኑ ወያኔ ለመኖሩ ተጨባጭ ማስረጃዎች ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ።
\\\
“ኦነግ ሸኔ” የሚባል ድርጅት በተጨባጭ ያለ ስለመሆኑ ምንም ማሳያ የለም። ምክንያት
፩/ “ኦነግ ሸኔ” እባላለሁ ብሎ በይፋ የቀረበ አካል አለመኖሩ፣
፪/ለቀረበበት ውንጀላ ኃላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩ፣
፫/”ኦነግ ሸኔ” ሰራው የተባለው ወንጀል አንድ በሽፍትነት የሚንቀሳቀስ የፈለገውን ያክል ሙሉ  ኃይል ቢያሰማራ ከተማ ሙሉ በሙሉ ለማውደም የሚያስችል አቅም እንደማይኖረው የሚታመን መሆኑ፣
፬/ የ”ኦነግ ሸኔ” አባላት ተብለው በማህበራዊ ትስስር የሚታዩ ምስሎች አንድ ሽፍታ ሊይዘው የማይችለውን መሳሪያ ታጥቀው መታየት፣
፭/የ”ኦነግ ሸኔ” አደረሰው ለተባለው ጥፋት ከተሞች ለ፫ እና ለ፬ ቀናት ሲነዱ መንግስት ችግሩን ለማብረድ ምንም ዓይነት እርምጃ አለመውሰዱ፣
፮/ “ኦነግ ሸኔ” አደረሰው ለተባለው ጥፋት መንግስት ምንም ዓይነት መጸጸት(መግለጫን ጨምሮ) አለማሳየቱ፣ እንዴውም ያላለቁ ፕሮጀክቶችን በመመረቅ “…ሪባን እንቆርጣለን” እያለ መሳለቁ፣
፯/መንግስት ዜጎች “መገደል በቃን” ብለው ያደረጉትን ሰልፍ ለማፈን የተሄደበት እርቀት፣
፰/ “ኦነግ ሸኔ” አባላት የተሰኙ ታጣቂወች በይፋ በከተሞች ጭምር የሚንቀሳቀሱና፣ የሚያደርጉትን ወንጀል እየቀረጹ በግልጽ ፎቷቸውን ጭምር የሚለጥፉ መሆኑ፣
፱/ወዘተ ናቸው።
ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች “ኦነግ ሸኔ” የሚባል በተጨባጭ አለመኖሩን ያሳያል።
\\\
የሆነው ሆኖ የእነዚህ አካላት መፈረጅ ጥቅሙ ባይገባኝም የአማራና የኢዜማ ልሂቃን ጮቤ እየረገጡ ይገኛሉ። ነፍጥ አንስቶ እየታገለ ያለን ወያኔን ፈረጅከው አልፈረጅከው ምን ለውጥ ያመጣል? ከቻለ ሊገድል፣ ካልቻለ ሊገደል የቆረጠን አካል ብትፈርጀው ምን ለውጥ ያመጣል?
\\\
“ኦነግ ሸኔ” የለም ካልን የሌለን አካል መፈረጅ ይህን ሁሉ ጥፋት ያደረሱ፣ ትዕዛዝ የሰጡ፣ የተከላከሉ፣ ያድበሰበሱ አካላትን “ሸኔ” በተባለ የዳቦ ስም ተከልሎ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ያለን አካል በተጨባጭ በሌለ አካል ስም ተዳፍኖ እንዲቀር ከማድረግ ያለፈ ምንም ጥቅም የለውም።
\\\
የእኔ እምነት
\\\
፩/የህወሃት ፍረጃ ለመናጆነት ሲሆን፣ ዋና ዓላማው ግን ባለፉት ፫ አመታት በዜጎችና በንብረት ላይ የደረሰውን ጥፋት በተጨባጭ የሌለ አካል(ሸኔ) ይዞት እንጦሮጦስ እንዲዎርድና፣ ዋነኛ ተጠያቂዎች እንዲያመልጡ ለማድረግና
፪/ ተቃዋሚን ሁሉ በሽብር እየፈረጁ ለማሰር እንዲያመች ለማድረግ ነው።
Filed in: Amharic