>
5:33 pm - Thursday December 5, 2543

ምኒሊክ ቢተቹ!... (መስፍን አረጋ )

ምኒሊክ ቢተቹ!…

 

መስፍን አረጋ 


ኢምንት ነን እንጅ ግዙፉን ለመክሰስ

ምኒሊክ እምየን የምንችል ለመውቀስ፣

ለገዳ ወረርሽኝ ሳይሰጡ ሙሉ ፈውስ

ሰላሌ፣ ጉለሌ፣ ቡልቡላ ቅብጥርስ

የተሰኙት ስሞች ከዘር ጭፍጨፋ መልስ፣

ሁነው ጠባሳወች የተስፋፊወች ቅርስ

በመቅረታቸው ነው እስከዛሬ ድረስ፡፡

 

አጼ ልብነ ድንግል ይዞ ብቻ ጋሻ

ከግራኝ ጦርና ከኦቶማን ባሻ 

የተፋለመበት እየመራ አበሻ፣

ታላቁ ጦርሜዳ ያ ሽንብራ ቁሬ

ስሙ ተለውጦ ዱከም ሁኗል ዛሬ፡፡

 

ከሚሴም ገነነ ተረስቶ ምድረገኝ

አሳምነው ጽጌ ከተከለው ችግኝ

አስታውሶ እሚያነሳው ጀግና እስከሚገኝ፡፡

 

ያማራን ማዕከል ሳይንትን ጠቅልሎ

ላኮመልዛ የሚል ወሎን ወዲያ ጥሎ

መፈጠሩ አይቀርም አድሮም ሆነ ውሎ፡፡

 

በጦቢያ ምድር ላይ ከጣና እስከ ጫሞ 

በኦሮምኛ ቃል ያለ ተሰይሞ

ከመስፋፋት በፊት ሁሉም አስቀድሞ

አይደለም ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ፡፡

 

የኦነግ ሠራዊት የቆጡን ለማውረድ አጣየ ሲመጣ

መገንዘብ አለበት የብብቱን ነቀምት ሊችል እንደሚያጣ፡፡ 

 

EMAIL; መስፍን አረጋ mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic