>

ነውር ጌጡ የሆነው ‹‹ተቋም››!  የ70 ዓመት    ሽማግሌ ከአርበኞች ድል በዓል ላይ አፍኖ በመውሰድ - ለህዝብ ያለው ንቀት አስመሰከረ!!! (አሰፋ ሀይሉ)

ነውር ጌጡ የሆነው ‹‹ተቋም››!  የ70 ዓመት    ሽማግሌ ከአርበኞች ድል በዓል ላይ አፍኖ በመውሰድ – ለህዝብ ያለው ንቀት አስመሰከረ!!!
አሰፋ ሀይሉ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከአርበኞች ድል በዓል አከባበር በኋላ በፌድራል ፖሊሶች ታፍነው መወሰዳቸው መረጃ ደርሶኛል።
ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌድራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ተቋም ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
ከተማን በጠራራ ፀሐይ የሚያነዱትን፣ የምስኪን ገበሬ ቤተሰብን ጎጆ ዘግተው በእሳት የሚያንጨረጭሩትን፣ ንፁሃንን በገፍ የሚያርዱትን፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን የሚያፈናቅሉትን፣ ሀገር የሚያሸብሩትን፣ ሕዝብን ዘርን ለይተው የሚጨፈጭፉትን – እና ፎቷቸውን እዩልን-ስሙልን ብለው ለህዝብ የሚለቁትን የታጠቁ የቀን ወንበዴ ጅቦች አሳዶ ለመያዝ የተንጃፈፈ ጀፋፋ የተረኞች መጫወቻ ‹‹ተቋም›› – ትልቅ የጠፋ አሸባሪን እንደያዘ ቢጤ – የ70 ዓመት ሽማግሌ ምሁርን ከአርበኞች ድል በዓል ማክበሪያ አደባባይ ላይ አፍኖ ወስዶ – ታላቅ አቅሙን ሊያሳየን እየተጋጋጠ ነው!
ማፈሪያዎች! 
አንድ ቀን የናቃችሁት ሕዝብ እሳት ሆኖ ይበላችኋል! አንድ ቀን የናቃችሁት የአርበኞች ሀውልት – መዋረጃ ሰገነታችሁ ይሆናል!  አንድ ቀን የናቃችሁት ሕዝብ ሽንቱን ይሸናባችኋል! አንድ ቀን ሜዳ ላይ ተሰጥታችሁ የናቃችሁትን ሕዝብ ትለምናላችሁ!
ለዚህ የጥጋብ ግፋችሁ የኢትዮጵያ አምላክ – አንድ ቀን – ሕዝብ የሚሰጣችሁን የመጨረሻ ፍርድ ያሳየን!
Filed in: Amharic