>

የእስራቱ ምክንያት  ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው ከሆነ ግን ጉዳዩ አሳሳቢ የሚሆነው ከአቶ ታዲዮስ ይልቅ ለአሳሪዎቹ ነው!!! (ስዩም ተሾመ)

የእስራቱ ምክንያት  ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው ከሆነ ግን ጉዳዩ አሳሳቢ የሚሆነው ከአቶ ታዲዮስ ይልቅ ለአሳሪዎቹ ነው!!!
ስዩም ተሾመ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ Yeneta tube የኔታ  ቲዩብ ላይ ይሰሩ እንደነበር አውቃለሁ። ከዕለታት አንድ ቀን የእሳቸውን ቪዲዮ ከፈት አድርጌ ስመለከት ሰውዬው የሚናገሩት ነገር እንደ ጩቤ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሆኖ አገኘሁት። በአንድ አረፍተነገር፤ ያልገባውን ያሳውቃሉ፣ የገባውን የሸነቁጣሉ። ለመጨረሻ ግዜ ስለ አቶ ታዲዮስ ታንቱ የሰማሁት Abebe Tolla Feyisa ከመቼው ከለንደን ተነስቶ አዲስ አበባ እንደገባ ሳላውቅ ከእሳቸው ጋር ቃለምልልስ ሊያደርግ እንደሆነ በፌስቡክ ገፁ ላይ ለጥፎ ነው። አሁን ላይ አቶ ታዲዮስ ታንቱ መታሰራቸውን ሰምቼ ግራ ገባኝ። ጉዳዩ በሂደት ተጣርቶ የሚታይ ይሆናል። ነገር ግን አቶ ታዲዮስ የታሰሩት ከአቤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ወይም በተለያዩ ሚዲያዎች በሚሰጡት አስተያየት ከሆነ እስራቱ በሁላችንም ላይ የተቃጣ የመብት ጥሰት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።
እዚህ ሀገር ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት (Freedom of Speech) ብዙዎቻችንን ዋጋ ያስከፈለ መብት ነው። በስንት መከራና መስዕዋት የተከበረ መብታችንን እንዲሁ እንደዋዛ አሳልፈን እንደማንሰ ሊታወቅ ይገባል። ጉዳዩ በሂደት የሚታይ መሆኑንና የፖሊስን መግለጫ በትዕግስት የምንጠብቅ መሆኑን እየገለፅን፣ የእስራቱ ምክንያት አቶ ታዲዮስ ሃሳባቸውን በነፃነት መግለፃቸው እንዳይሆን ከወዲሁ ስጋታችንን እንፀገልጻለን። ስጋታችን እውን ከሆነ ግን ጉዳዩ አሳሳቢ የሚሆነው ከአቶ ታዲዮስ ይልቅ ለአሳሪዎቹ ነው።
Filed in: Amharic