ኦሮሙማው እንደ ሙት ልጅ . . . !!
አሰፋ ሀይሉ
በፍርድ ቤቶች አካባቢ ሲነገር የኖረ አንድ የቆየ አስቂኝ ታሪክ አለ። ወልደው ያሳደጉትን እናትና አባቱን የገደለ አንድ አረመኔ ሰው በፍርድ ችሎት ይቀርብና ጥፋተኛነቱ ይረጋገጥበታል።
ዳኞቹም የሰውየውን ቅጣት ከመወሰናቸው በፊት “ፍርድቤቱ ቅጣቴን ሊያቀልልኝ ይገባል” የምትላቸው ማስተዛዘኛ ምክንያቶች ካሉህ “ንገረን እንስማህ” ሲሉ ይጠይቁታል። ሰውየውም በዳኞቹ ፊት በእንባ እየታጠበ እንዲህ አላቸው፦
“እኔ በአሁኑ ሰዓት አባትም እናትም የሌለኝ
የሙት-ልጅ ነኝ፣ ስለዚህ ምስኪን የሙትልጅ
መሆኔን ከግምት ውስጥ አስገብቶ፣ የተከበረው
ፍ/ቤት ቅጣቴን ያቅልልኝ!”
ዳኞቹም ተመካክረው እንዲህ ሲሉ የመጨረሻ ፍርዳቸውን ሰጡት፦
“እናትህንና አባትህን ስለገደልክ ሁለት የሞት
ቅጣት ይገባህ ነበር፣ ነገር ግን ያለ እናት-አባት
የቀረህ ምስኪን የሙት-ልጅ መሆንህን ስለተ
ረዳን ቅጣትህን አቅልለን አንድ የሞት ቅጣት
ብቻ እንዲፈፀምብህ ወስነናል።”
ቀልደኛው ገዳይ (የሙት-ልጅ) “ወይኔ እናቴ”፣ “ወይኔ አባቴ” እያለ፣ ከነለቅሶው በገበያ መሐል ተወስዶ ተሰቀለ።
አሁንም የኦሮሙማውን ነገረ-ሥራ ስመለከት ያንን አባትና እናቱን ገድሎ “የሙት-ልጅ ነኝ ማሩኝ?” ያለውን ቀልደኛ ነፍሰበላ ያስታውሰኛል።
ኦሮሙማው በወያኔ እግር ተተክቼ ኢትዮጵያን ረግጬ እገዛለሁ፣ አሊያ ግን ሀገሪቱን አፈራርሼ በፍርስራሿ ላይ የታላቋን ኦሮሚያ ሀገረመንግሥት እውን አደርጋለሁ ብሎ – ሁለት ባንዲራ እያውለበለበ፣ በሁለት ስለት፣ በሁለት ፅንፍ እየተውተረተረ ነው።
በከንድ በኩል በፀረ-ኢትዮጵያዊ ፖለቲካና ትርክት ትውልዱን እያጠመቀ፣ ከውስጥም ከውጪም ኢትዮጵያን እየገዘገዘ፣ ባንዲራችንን እየረገጠ፣ ታሪካችንን እያፈራረሰ፣ በኢትዮጵያ ጥላቻ የተመረዘ ነፃ አውጪ ሠራዊትና ቄሮ ወጣት እየገነባና እያስታጠቀ፣ እንደ ሀገር በጋራ ያያያዙንን የአንድነት ክሮች ሁሉ አንድ በአንድ ለመበጣጠስ ተግቶ እየሠራ፣ ኢትዮጵያዊነትን እያዳከመና እያስጠቃ እናገኘዋለን።
በሌላ በኩል ደግሞ ዞር ብሎ ያው የምናውቀው ፀረ-ኢትዮጵያ ሀይል መልሶ “ኢትዮጵያ ተዳከመች ብለው ዙሪያዬን ጠላቶች ወረሩኝ” ብሎ ሌት ተቀን በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎችና መሪዎቹ አፍ ማላዘንን ሥራዬ ብሎ ተያይዞ እናገኘዋለን።
በከንድ በኩል ለሥልጣንና ለተረኛ ፋሺስትነት በቋመጡ አረመኔ ጥርሶቹ ህዝባችንን እያመሰ፣ ዜጋችንን እያረደ እያፈናቀለ፣ ከጫፍ ጫፍ ሀገሪቱን እያተራመሰ፣ ምድራችንን በዜጎቿ ደም እያጠበ እናገኘዋለን።
በጎን ደግሞ ኦሮሚያን የሚገነጥል ሠራዊትና መገንጠሉን የሚደግፍ ህዝብ ለመፍጠር ቀን ከሌት ሠማይ ምድሩን እየቧጠጠ – ሀገርንና ሕዝብን የመጠበቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን ትቶ ሀገር በመበተንና ተቀናቃኞቹን በመውጋት ላይ ተጠምዶ እናገኘዋለን።
መንግሥት ነኝ እያለ፣ በተግባር ራሱን ወደ መንግሥታዊ አሸባሪ ቡድንነት የቀየረው – የጊዜያችን ኦሮሙማ – ከነለቅሶው – በአካል በአምሳል አባት እናቱን ገድሎ “ማሩኝ የሙት-ልጅ ነኝ” ያለውን አራጅም-አልቃሽም አረመኔ ገፀ-ባህርይ ደግሞ ደጋግሞ እየተጫወተልን ነው።
ኦሮሙማው አጥብቆ የሚጠላትን ሀገር በመንግሥትነት ተቆናጥጦ፣ ሀገርን እያተራመሰና ለውድቀቷ እየሠራ፣ የሀገሪቱን ህዝብ ከመዲናዋ እስከ ድንበሯ ያለ ጥበቃና ያለ ደህንነት ዋስትና አስቀርቶ፣ የጠላት መጫወቻና የአራጅ መፈንጫ አድርጓት ሲያበቃ – ሀገሪቱ በጠላት ተከባለች ይለናል።
የክልሉን ባንዲራ በግብፅና በሱዳን ባንዲራ ቀለምና አምሳል ሠርቶ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ለግብፃዊነትና ለሱዳናዊነት የቀረበ ትውልድ ሊፈጥር ሲሟሟት የኖረ ሀይል፣ ከግብፅና ሱዳን ጋር ቂጥ ገልቦ ሲያጫፍር የቆየ አስጠቂ ከሀዲ ሀይል ሆኖ ሳለ፣ አሁን ምንም ሳያፍር ግብፅና ሱዳን ሊወሩን ነው እያለ እዬዬውን በቅልብተኛ ጅቦቹ አፍ ጧት ማታ ማስደለቁን ተያይዞታል! ያንንም እዬዬ ሲያዘራ፣ ያን ለመቀልበስ የሚያደርገው ነገር የለም።
ይህን የጊዜያችንን የሙት ልጅ፣ ከነተቆረጠ የጡት ሀውልቱ፣ ከነኦነግ ባንዲራው፣ ከነግብፅና ሱዳን ባንዲራው፣ ከነእርዱና ጥላቻው፣ በተባበረ ክንድ ወደ መቃብሩ ካላወረድነው – ሀገራችንን ገፍቶ ገፍቶ ወደማትወጣበት መቀመቅ ሊከታት ጫፉ ላይ ደርሷል።
ይህ ሀገር አጨንጋፊ የአባ-ቶርቤ ሀይል፣ ከነጭንጋፍ አሸብሻቢዎቹ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትብብር የመንግሥት ካባው ተገፍፎ፣ አንዳችም ጉዳት ሊያደርስ ወደማይችልበት ጥግ ተገፍቶ በኳራንታይን ውስጥ እስካልተቀመጠ ድረስ፣ ይህች ሀገር በሠላም ተረጋግታና አንድነቷን ጠብቃ መኖር አትችልም።
እናት አባቱን ገድሎ “የሙት ልጅ ነኝ” ብሎ እንዳለቀሰው አረመኔ ነፍሰበላ በመሠሉ፣ ራሳቸው ገድለው ደሰታቸውን አብረውን በሚደቁ ፀረ-ሀገር ሀይሎች እጅ መንግሥት ተላልፎ ተሰጥቶ፣ ህዝባችን መቼም ሠላም አይኖረውም።
አያ ጅቦ ሥጋ የጫነችን አህያ ከፊቱ እያመለከቱት “ሸኚ አጥታ ተቸግራለችና ያቺን ዳገት አብረህ አሳልፋት” ተብሎ ቢጠየቅ፦ “ሣቄን እንዴት እችለዋለሁ?!” አለ ይባላል።
እናት ሀገርን ለወጋና ለሚወጋ የእናት ጡት ነካሽ፣ ሀገርን በአደራ አይሰጡትም። ኢትዮጵያን ለጠላና ሀገርን አፍርሶ የራሴን ሀገር እገነባለሁ ለሚል “እስኪያመቸው በግ፣ ሲያመቸው ተኩላ” ለሆነ ፀረ-ኢትዮጵያ ሀይል፣ ያሻህን አድርግበት ተብሎ መንግሥት ከነጦሩ አይሰጥም።
ሃምሳ ዓመት ሙሉ ይህቺን እናት ሀገራችንን እየረገሙ ሲያደሟት ከኖሩ ፅንፈኞቹ ጋር የሥልጣን ጋብቻና የጦር ቃልኪዳን ፈፅሞ፣ ጊዜ አግኝቶ፣ ጥፋቱን አሰናድቶ፣ ራሱን አደርጅቶ፣ ሀገርን ጨርሶ ከማጥፋቱ በፊት የሙት ልጁን በተባበረ ክንድ በቃህ እንበለው!
ኢትዮጵያ ትቅደም!