>

በላኤ ሰብዕ ዐቢይ አሕመድ የአማራ ፖለቲከኞችን ለመብላት የሸረበው ሴራ እንደቀጠለ ነው...!!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

በላኤ ሰብዕ ዐቢይ አሕመድ የአማራ ፖለቲከኞችን ለመብላት የሸረበው ሴራ እንደቀጠለ ነው…!!! 

አቻምየለህ ታምሩ

በላኤ ዐቢይ አሕመድ ከአራት ቀናት በፊት በሚቆጠጠረው ሜዲያ በኩል በሰበር ዜና ባስነገረው እንጭጭ ድራማ “ስድስተኛውን ምርጫ ለማደናቀፍ ሲያሴሩ እንጅ ከፈንጅ ተያዙ” ያላቸው የቀሽም ድራማው ተዋንያን አብዛኛዎቹ በደኅንነት መስሪያ ቤቱ የተዘጋጁ የደህንነት አባላት መሆናቸውንና በሰበር ዜና የተነገረው መንግሥታዊ ውንብድና አላማ የአዲስ አበባ አማራዎችን ለመብላት የተሸረበ ሴራ መሆኑን ከውስጥ ምንጭ ያገኘነውን ማስረጃ ዋቢ በማድረግ ከቀናት በፊት ጽፈን ነበር።
ዛሬ ይፋ የምናደርገው ደግሞ ሰበር ዜና የተሰራበትን ድራማ ቀጣይ ክፍል ነው። “ስድስተኛውን ምርጫ ለማደናቀፍ ሲያሴሩ እንጅ ከፈንጅ ተያዙ” ተብለው በቴሌቭዥን ከልዩ ልዩ ቁሳቁስ ጋር ያየናቸው የድራማው ተዋናዮች እንዲቆዩበት ከተደረገው ሜክሲኮ ከሚገኘው ፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ባሳለፍነው አርብ ዘጠኝ ላይ በነጻ ተለቀዋል። ልብ በሉ! በነጻ የተለቀቁት ምርጫ ተብዮውን ለማደናቀፍ፣ ባለስንጣናትን ለመግደል ሲያሴሩና  በፌስታል ሙሉ “ምርጫ ይቁም” የሚል በራሪ ወረቀት ይዘው ሲበትኑ በደኅንነት መስሪያ ቤቱ እልህ አስጨራሽ ክትትል እጅ ከፈንጅ ተያዙ ተብለው ያየናቸው ናቸው።
እጅ ከፈንጅ ተያዙ ተብለው በቴሌቭዥን ካየናቸውና በነጻ ከተለቀቁት ተዋንያን መካከል፤
1.  ቴዎድሮስ ታደሰ (አማራ)፤
2. ሔኖክ ማትያስ (ጋሞ)፤
3. ነብዩ ሙክታር (ጉራጌ)፤
4. ሳሙኤል ልደቴ (አማራ)፤
5. ያለው ባዘዘው (የመከላከያ አባል የነበረ ስሙን የማይጽፍ)፤
6. እና ሌላ አንድ የደኅንነት አባል ናቸው።
ይህን ቀሽም ድራማ የጻፈውን በላኤ ሰብዕ ዐቢይ አሕመድን እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቁት፤
1.  “ስድስተኛውን ምርጫ ለማደናቀፍ ሲያሴሩ እንጅ ከፈንጅ ተያዙ” ተብለው በሰበር ዜና በቴሌቭዥን የተለያዩ ቁሳቁስ ይዘው ያየናቸው ሰዎች ነጻ ለመባል የበቁት  የትኛው ፍርድ ቀርበው ነው? ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እንዴት በነጻ ሊለቀቁ ቻሉ?¡
2. ነጻ ያስባላቸው “የሽብርተኞች” ጠበቃ መቼ መረጃ ሰብስቦና እነማንን ምስክር ቆጥሮ አስመስክሮ ነው የአገዛዙን አቃቤ ሕግ  ረትቶ ልጆችን በነጻ ያወጣቸው?¡
3. እጅ ተፈንጅ ተያዘ  የተባለን “አሸባሪ” ፍርድ ቤት ሳያስቀርብ የሚያስፈታ ወጭ ቆጣቢ ጠበቃ የት እንዳለ ልትጠቁሙን ትችላላችሁ¡? ይህን መጠየቄ እንዲህ አይነቱን ጠበቃ ለእነ እስክድር ነጋ እኔ በግሌ የሚፈልገውን ክፍያ ፈጽሜ ልቀጥረው እፈልጋለሁ!
ይታያችሁ! ሰው ሲለፋ ውሎ በስራ የደከመ አካሉን እና አዕምሮውን በሚያሳርፍበት ሰዓት ሰበር ዜና ብሎ ያስነገረው አሸባሪ ድራማ የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ በደኅንነት መስሪያ ቤቱ እልህ አስጨራሽ ክትትል ሽብር ሲሰሩ እጅ ተያዙ ያላቸውንና በኩርቱ ፔስታል አሸክሞ በቪዲዮ ቀርጾ ለሕዝብ ያሳያቸውን የድራማው ተዋንያን በተያዙ በበነጋታው  ለይስሙላ እንኳን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡብ  በነጻ ሲለቅቃቸው የእነ እስክድር ነጋ እውነትና ፍትህ ወዴት አለሽ?፣ ማደሪያና መዋያሽ የት ነው? ያስብላል።
እጅ ከፈንጅ ተያዙ ተብለው በቴሌቭዥን ያየናቸው ሰዎች  የተለቀቁት በላኤ  ሰብዕ ሰዎቹን ተጠቅሞ የሚፈልገውን አላማ ስላሳካ ነው። የድራማው አላማ የአማራ ባለሀብቶችን እና ስለ አዲስ አበባ ዝም አልልም የሚሉትን ለኅሌናቸው ያደሩትን የፍትሕና የእኩልነት ፈላጊዎችን ለመፍጀት ነው።
ከተለቀቁት የቀሽም ድራማው የደህንነት አባል የሆኑ ተዋንያን ጋር አብረው ከታሰሩት መካከል፤  1. አቶ ናደው ዘውዱ [የየረር ኮንስትራክሽን ባለቤት]
2.  የመሰረት ተራድኦ ድርጅት ባለቤት ወሮ መሰረትና ባለቤቷ
3.  ጋዜጠኛና የታሪክ አዋቂው አቶ ታዲዎስ ታንቱ እና ሌሎችም በዚሁ ድሪቶ ቡትቶ ወሬ እስካሁን ታስረው ይገኛሉ።
እጅ ከፈንጅ ተያዙ ተብለው ከተለያቱ ቁሳቁሶች ጋር በቴሌቭዥን ያየናቸው የደኅንነት መስሪያ ቤቱ አባላት እና አርብ እለት የተለቀቁት እነዚህ ከታች በፎቶ የሚታዩት የድራማው ተዋንያንን በመጠቀው የተሰራው ሰበር ዜና አላማ እነዚህን የአማራ ልጆችና በአማራ ላይ አገዛዙ የሚፈጽመውን ግፍ የሚያወግዙ የኅሊና ሰዎች ለማጥፋት ነው።
Filed in: Amharic