>

ታሪካዊ ስሕተት እንዳይደገም፤ የአባቶች ውይይት በቤት ውስጥ ይለቅ...!!! (ፋንታሁን ሙጬ)

ታሪካዊ ስሕተት እንዳይደገም፤ የአባቶች ውይይት በቤት ውስጥ ይለቅ…!!!

ፋንታሁን ሙጬ

*…. የዚህ አገር አብዮት የተጀመረው ቤተክርስቲያን የቀባችውን ንጉሥ በመግደል፣ ቀቢውን ጳጳስ በስቀል የቀጠለውን ፓትሪያርክ ከአገር ማስወጣትና በፈለጉት በመተካት፣ ባለ ጊዜውም በራችንን ገርበብ ካደረግን እንዲሁ ሊያደርግ ይችላል? 
ባለቤት እንደሌለው ጠፍ ከብት ያገኘን ሁሉ ሲያርደንና በቡለደዘር ስነቀበር   ያልተንጫጫ  ተዋኒያን ሁሉ ዘሬ ብቅ ብሎ ብዙ ሊያወዛግበን አይገባም።
ሁላችንንም አንድ የሚያደርገን እንጂ  ሙት ቅርሥ ሊያደርጉን ለመሚሞክሩ ኦርቶዶክስ-ጠል ጠላቶቻችን ዱላ ማቀበል አይጠቅመንም።
አንድም አባት ሌላኛውን አሳልፎ በሚሰጥ መንገድ የተለመደው የፖለቲካ እጅ እንዲገባ  የሚያመቻች ጥረት ከገዳዮቻችን ጋር እንደመተባበር ይቆጠራል።
የዚህ አገር አብዮት የተጀመረው ቤተክርስቲያን የቀባችውን ንጉሥ በመግደል፣ ቀቢውን ጳጳስ በስቀል ነበር። የቀጠለው ፓትሪያርክ ከአገር ማስወጣትና በመተካት፣ ቀጥሎ ያለውም እንዲሁ ሊመኝ ይችላል።
ጠላት ሁሉም ግን የሚሳካላቸው ከውስጥ አንድነት ሲጠፋና በአድርባይነት፣ ፈሪ  ወይንም ባለመዋቅ፣ ወይንም በዘርኝንተ የተለከፉ ከመካከል ሲገኝ ነውና ታሪካዊ ስሕተት እነዳይሠራ የልጅንተ ሥጋቴን መግለጽ ፈልጋለሁ።
Filed in: Amharic