>

ህዝበ ሙስሊሙ 1442ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን በመከባበር፣ በመተሳሰብና በአንድነት ማክበር ይገባዋል...!!! (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ)

ህዝበ ሙስሊሙ 1442ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን በመከባበር፣ በመተሳሰብና በአንድነት ማክበር ይገባዋል…!!!
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ
(ኢ ፕ ድ) 

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስ የኢድ አል ፈጥር በዓልን  አስመልክተው ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት  መግለጫ  እንዳሉት፤ በዓሉን ስናከብር ያላቸው ለሌላቸው በማካፈል በመረደዳትና በአንድነት መንፈስ በጋራ መሆን ይገባል፡፡
በሀገር ውስጥም በውጪም የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም ይሄን እንዲያጠፋለን ዱአ ማድረግ ተገቢ ነው ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ፤  በአንድነትና በሰላም ሀገርን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡
ሀገር መብቷ እንዲከበር አንድነትና ህብረት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ጠብና ክርክርን ወደ ጎን በመተው በጋራ ሀገርን ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በአሉ ዛሬ ማታ ጨረቃ ከታየች ነገ፤  ካልታየች ደግሞ  ሀሙስ የሚከበር መሆኑንም ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
Filed in: Amharic