>

ይህ ነጻ እርምጃ ህግ ካለ በህግ ሊባል ይገባል...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ይህ ነጻ እርምጃ ህግ ካለ በህግ ሊባል ይገባል…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

 

*…. የጸጥታ ጏይሎች እንዲህ ያለ የመንጋ ፍርድ ሲሰጡ ማየት እጅግ ያሳዝናል
በኦሮሚያ ክልል፤ በደንቢዶሎ ከተማ ይህን በምስሉ የምታዩትን ወጣት አማኑኤል ወንድሙን የአካባቢው የታጠቁ የጸጥታ ጏይሎች በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ እጁን የፊጥኝ ወደኋላ አስረው፣ ደረቱ ላይ ሽጉጥ አንጠልጥለው በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውታል።
ልጇ አንዴ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋለ፣ እና እጆቹ የፊጥኝ ታሥረው በማንም ላይ ጉዳት ሊያደርስ በማይችልበት ሁኔታ ላይ እያለ፣ ያለፍርድ መግደል – እጅግ አስነዋሪ ግፍ ነው፡፡ የወጣለት መንግሥታዊ አሸባሪነት ነው፡፡ እና የለየለት በህግ መዝገበቃላት ላይ በምሳሌነት ተጠቅሶ የምናገኘው የጦር ወንጀል ተግባርም ነው፡፡
 ይህ ድርጊት በውግዘት ብቻ የሚታለፈ አይደለም። መንግሥት ድርጊቱን የፈጸሙትን አካላት በቁጥጥር ስር አውሎ ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱን ለሕዝብ ማሳወቅ አለበት። የጸጥታ ጏይሎች እንዲህ ያለ የመንጋ ፍርድ ሲሰጡ ማየት እጅግ ያሳዝናል።
የመከራ ታሪካችንን የሚጽፍ ትውልድ ይነሳ እንደሁ፣
ይህ ለታሪክ ይቀመጥ!
መከራችን በዛ! ግፋችን እርቃን ወጣ! ፈጣሪ አምላካችን ሆይ፣ ልጆችህን በቃችሁ በለን! ‹‹እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ!›› እንበል፡፡ ነፍስ ይማር!
 
Filed in: Amharic