>

የልብ ወዳጁ በረከት ስምዖን፣ ስለዚህ ሰው የተሳሳተው፣ በአንድ ነገር ብቻ ይመስለኛል. . . ! (አሰፋ ሀይሉ)

የልብ ወዳጁ በረከት ስምዖን፣ ስለዚህ ሰው የተሳሳተው፣ በአንድ ነገር ብቻ ይመስለኛል. . . !
አሰፋ ሀይሉ

«በዚህ ዓለም ላይ ለሰዎች ከማጎብደድ ለመውጣት ከፈለግህ ልትከተላቸው የሚገቡ ሁለት ወርቃማ ህጎች አሉ፡- እውነትን ለመናገር አለመፍራት፣ እና ውሸትን ለመናገር አለመድፈር፡፡»   — ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን
«ተቀምጦ ከመተቸት፣
ዳር ቆሞ ከማየት፣
ተስፋ ቆርጦ ከመቆዘም ይልቅ… »
ይልና የውዳሴ መዓት ይደረድርለታል አንድ በፌስቡክ የተለቀቀ የኢዜማ የቅስቀሳ ማስታወቂያ፡፡ እኔ ደግሞ ‹‹ይልቅ›› እስከሚለው ድረስ ያለውን አስቀርቼ ተገቢ የምለውን የሚከተሉትን የሰውየውን መገለጫዎች በግል ማስታወሻዬ አሰፈርኩ፡-
«ተቀምጦ ከመተቸት፣
ዳር ቆሞ ከማየት፣
ተስፋ ቆርጦ ከመቆዘም ይልቅ… »
ከአጥፊዎች ጎራ መሰለፍን፣
ለተረኞች ማጫፈርን፣ እና  በአማራው ዘር ላይ ያነጣጠረ ኦነጋዊ ጥላቻን ማስተጋባትን የመረጠ፣
የከሸፈ ሴረኛ መሪ!
የማስታወሻዬ ቅጠል አልቆ እንጂ፣ ሌላም የምጨምረው ነበረኝ፣ እንዲህ የሚል፡-
«በተጨማሪም ይህ ሰው፡- 
© ኢዜማ 22 ሺህ የአዲሳባ ነዋሪ ኮንዶሚኒየሞችን ለዘሮቹ ያደለውን ታከለ ኡማን «ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት ያሻግረናል» ብሎ የመሰከረ፣ እና
© የአውሮፓ ህብረት 80% ድራማ መሆኑን ገልጾ አልታዘብም ያለውን ምርጫ፣ ወዳጁን አና ጎሜዝን እባክሽ ሀሳባቸውን አስቀይሪልን ብሎ የለመነና ህብረቱን ያስለመነ፣ የኦሮሙማው የጭንቅ ቀን አማላጅም ነው!»
የዚህን ሰውና የሸሪኮቹን ሸፍጥና ሴረኝነት ስረዳ ብዙ ሀሳቦቼን መላልሼ ከለስኩ፡፡ ‹‹ነጻነት ጎህ ሲቀድ›› በሚል ርዕስ ከእስር ቤት በጻፈው (እና ከሲአይኤ የመረጃ ፋይል በተገኙ የግርጌ ማጣቀሻ ምንጮች በተገጠገጡበት) መጽሐፉ፣ የ1997ቱን ምርጫ ውጤት አስመልክቶ ከመለስ ዜናዊ ጋር ሊወያይ ቤተመንግሥት ሲገባ፣ የልብ ወዳጄ ነው የሚለው በረከት ስምዖን ወደ ጆሮው ጠጋ ብሎ፡-
‹‹እሺ፣ የእዣ ነጻ አውጪ!››
ብሎ አሽሟጠጠኝ – በማለት የከሰሰበትን ጽሑፉን ሳነብ፣ የሰዎቹ ትንሽነት ገርሞኝ አላባራ ብሎ ነበር፡፡ አሁን ላይ ሳስበው፣ «ለካ እባብ ለእባብ ይተዋወቃል!» አልኩ ለራሴ፡፡ አቶ በረከት ስምዖን እንደዚያ ማለቱ ብዙም ነውረኛ እንደማያሰኘው የገባኝ አሁን ነው፡፡ ከአንድ ነገር በስተቀር፡፡ በረከት የተሳሳተው አንድ ነገር ብቻ ነበር፡፡ በዶክተሩ ጆሮ ሹክ ማለት የነበረበት እንዲህ አስተካክሎ ነበር፡-
‹‹እሺ፣ የኦሮሙማ ነጻ አውጪ!››
ጊዜ የሰዎችን ማንነት ይገልጣል! ማንንም በመዝለፍ አላምንም፡፡ ሕዝብን ለዘለፈ አጫፋሪ ግን፣ የሚገባውን በልኩ መናገር፣ ዘለፋ ሳይሆን ሽልማቱ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ችግሩ ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ ምሣሌው ላይ፡- «በዘለፋ ብዛት አንገቱን ያደነደነ አንድ ቀን ይሰበራል፣ ፈውስም የለውም» ብሎ ይነግረናል፡፡ በዘለፋ ብዛት አንገቱን ያደነደነን ዘለፋ አያድነውም፡፡ ምክር ሴራውን አያስጥለውም፡፡ የሚቻለው ከእንዲህ ዓይነቶቹ የአደባባይ ሴረኞች ሴራ ራስን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡
ይህን ሰው (እና ነጻ አውጪ ሸሪኮቹን) መቼውኑም የአማራን ምድር ረግጠው «ምረጡኝ!» ለማለት እንዳይደፍሩ ሁለመናቸውን አደባባይ እያስጣጡ ለሕዝብ ማጋለጥ፣ ከሁሉም ሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ የተቀደሰ የዜግነት ተግባር እንደሆነ አምናለሁ!
ኢዜማ የኦሮሙማው የፕሮፓጋንዳ ፈረስ ነው!
እናት ኢትዮጵያ – በልጆቿ ቆራጥ ተጋድሎ – ከሴረኛ ጥፍሮች ተላቅቃ – ለዘለዓለም በክብር ትኑር!
Filed in: Amharic