እነሆ ታላቅ ገጸ-በረከት ከእስክንድር ነጋ!!
በላይ ማናዬ
ጋዜጠኛ፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች፣ አሰላሳይ፣ አርቆ ተመልካች፣ የነጻነት ታጋይ እስክንድር ነጋ “ድል ለዴሞክራሲ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው መጽሐፍ ከነገ (ቅዳሜ) ጀምሮ ለንባብ ይበቃል።
እስኬ አካሉ እንጂ ህሊናው አልታሰረም!
ድል ለዲሞክራሲ ከእስክንድር ነጋ!!
* * *
በኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ መጽሐፍ ተዘጋጀ…!!!
ደመቀ ከበደ
መጽሐፉ የፊታችን ቅዳሜ ገበያ ላይ ይውላል።
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮን) ጨምሮ በርካታ ሙያተኞች፣ ጓደኞቹ፣ እንዲሁም በቅርቡ ከነበሩ ሰዎች ለመጽሐፉ ዝግጅት ያልተነገሩና አስደናቂ መረጃዎችን የሰጡበት ሲሆን 409 ገጾችና አስራ አራት ምዕራፎች እንዳሉት ታውቋል።
“የከተማው መናኝ ፡ ኤልያስ መልካ” የሚል ርዕስ የተሰጠው “የትንታኔ ድርሳኑ” የተወዳጁን ሙዚቀኛ ኪናዊና ግላዊ ሕይወት ከተለያዩ ንድፈ ሀሳቦች አንፃር በስፋት መርምሯል፡፡
ከአራት መቶ በላይ ሙዚቃዎችን በማቀናበር አያሌ ዜማ በመስራትና ግጥም በመፃፍ ጭምር በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከቀዳሚዎቹ ተረታ የሚመደበው ኤልያስ መልካ ባለፉት ሩብ ክፍለ ዘመናት የሀገሪቱ ሙዚቃ እንቅስቃሴ ውስጥ የጎላ አሻራን አኑሯል ።
የጥናታዊ መጽሐፉ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው እንዳለው የከተማው መናኝ በሚል ርዕሥ ለገበያ ለመብቃት የተዘጋጀው መጽሐፍ የአንድ ብዙ የሆነውን አቀናባሪውን፣ ጊታር ተጫዋቹን፣ ግጥምና ዜማ ደራሲውን እንዲሁም ፕሮዲውሰሩን ኤልያስ መልካን ከፍልስፍና፣ ከነገረ-መለኮት፣ ከሳይንስ፣ ከታሪክና ኪነ-ጥበብ ሃልዮት አንፃር በስፋት ለመፈተሸ የሞከረ ስራ ነው፡፡
ኤልያስ መልካ የቅርብ ሩቅ የሆነ ባለሙያ ነበረ ያለው ጸሐፊው አድናቂዎቹ የሚያነሷቸውና ለማወቅ የሚጓጉላቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ መመሞከሩን አብራርቷል፡፡
ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እና ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ጋር በተያያዙ መሰናዶዎቹ የሚታወቅ ሲሆን በተለያዩ የሕትመት ውጤቶች ላይም ሰፋ ያሉ ፖለቲካዊና ኢኮሚያዊ ትንታኔዎች በማቅረብ ይታወቃል፡፡
መጽሐፉ ቅዳሜ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለኤልያስ ክብር በሚዘጋጀው ታላቅ ዝግጅት ወቅት እንደሚመረቅም ለማወቅ ተችሏል።