>

እስክንድር ነጋ ለልጁ የፃፈው ደብዳቤ...

” ልጄ ናፍቆት ካንተ ጎን ያልተገኘሁት በግፈኞች የሀሰት ክስ እና የፍትህ አልባ ፍርድ ነው ! “
እስክንድር ነጋ ለልጁ የፃፈው ደብዳቤ…

     ገና በእናትህ ማህፀን ሳለህ ፣ ለሰብአዊነት  ፣ ለዲሞክራሲ እና ፍትህ የሚደረግን ትግል ተቀላቅለሃልና ደስ ይበልህ እንጅ አይክፋህ ። እናትህ በቃሊቲ ወህኒ እስር ቤት ሳለች ወለደችህ ፣ ነገር ግን አንዳች ወንጀል አልነበረባትም  ። ዛሬም አባትህ በዚያው አለሁ ።
    ነገር ግን አንዳች ወንጀል ያልሰራሁ ፣ ከጨረቃ የነጣ ንፁህ አባትህ ነኝ ። ልጄ ናፍቆት ካንተ ጎን ያልተገኘሁት በግፈኞች የሀሰት ክስ እና የፍትህ አልባ ፍርድ ምክንያት አባት አልባ ስለሆኑ ህፃናት ፣ ለስደት እና ሞት ስለሚዳረጉት የአንባገነን ገዥዎች ቀንበር ስለተጫናቸው  ፣ ህዝቤና ሀገሬ ጉዳይ ትግል ላይ በመሆኔ ነው ። የምዳኜውም በእነርሱ ህሊና ነው ።
       ሀገሬና ህዝቤ ከግፈኞች ቀንበር በተላቀቁ ጊዜ ፣ ያኔ …የእኔና የአንተ ቀን ብሩህ ይሆናል ። ተስፋም አደርጋለሁ  ፤ ይሄም ቀን ተቃርቧል ። ስለተረዳኸኝ አመሰግናለሁ ።”
 እስክንድር ነጋ 
ድል ለዲሞክራሲ  !!!
Filed in: Amharic