>

የአማራን ህዝብ  ገዳዩም ሆነ አፈናቃዩ መንግስት ነው ስንል በምክንያት ነው...!!!! (ተረፈ ጌታቸው)

የአማራን ህዝብ  ገዳዩም ሆነ አፈናቃዩ መንግስት ነው ስንል በምክንያት ነው…!!!!

ተረፈ ጌታቸው

በመጀመሪያዉም ሆነ በሁለተኛዉ ኢህአድግ የሚሞተዉ የሚፈናቀለዉ ፣ የሚታረደዉ ፣ የሚሳደደዉ ፣ …………. በመንግስት እና በእሱ እዉቅና በተሰጣቸዉ የዳቦ ስሞች ነዉ የምንለዉ ለዚህ ነዉ፡፡ አሁን እስቲ ይህን ዜናና ተግባር ምንትሉታላችሁ ?  መንግስት የአማራ ህዝብን ይቅርታ እንኳን ቢል ተቀባይነቱ ምንድረስ ነዉ ? ይታመናልስ ? …………. በጣም ያሳዝናል ፣ ያስገርማል .፣ ያስደንቃል ፣ ያስለቅሳል ፣ያሳርራል፣ ሲያሰኛቸው በቀስት በሉ ሲላቸው በክላሽ የአማራን ህዝብ ለይተው ሲገድሉ ከቀዬው ሲያፈናቅሉ በስውር ስንቅና ትጥቅ ሲቀርብላቸው የኖሩትን የጉምዝ ታጣቂዎች ለውለታቸው ከጫካ ወደ ከተማ በማምጣት ለሀብትም ለስልጣንም መታጨታቸውን እየነገሩን መሆኑ ነው….
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥትና ታጣቂ ቡድኑ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተደጋጋሚ ጥቃት በሚከሰትበት መተከል ዞን ያለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት መፍትሄ ለማምጣት የክልሉ መንግሥትና ታጣቂ ቡድኑ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ዞኑ አስታውቋል።
ስምምነቱ የተፈረመው በትናንትናው ዕለት ግንቦት 10፣ 2013 ዓ.ም በግልገል በለስ ከተማ መሆኑን የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል።
የአካባቢውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በታጣቂ ቡድኑ በኩል የሚነሱ እና የጋራ በሚያደርጉ ጉዳዮች የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ መፈረሙም ተገልጿል።
በዚህ ሰነድ ከተካተቱት ዋነኛ ጉዳዮች መካከል እነዚህ ኃይሎች የኃላፊነት ቦታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የከተማ የቤት መስሪያ ቦታ፣ የገጠር የእርሻ መሬት እንዲኖራቸው ማድረግ ይገኙባቸዋል።
በኃላፊነት ቦታ የሚመደቡት አቅምና የትምህርት ደረጃቸውን ባማከለ መልኩ እንደሆነ የጠቆመው መግለጫው በክልል ደረጃ ሁለት፣ በዞን ደረጃ ሶስት እና በወረዳ ደረጃ ደግሞ አራት ሰዎች ይቀመጣሉ ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ ልምድ ያላቸው የቡድኑ አባላት በክልሉ ውስጥ ባሉ የፀጥታ መዋቅሮች መመደብ፣፣ሴቶችን አካታች ያደረገና በተለያዩ ማህበራት እንዲደራጁ ማስቻል፣በተማሩበት የሙያ መስክ እንዲመደቡ ማድረግና የብድር አገልግሎት እንዲመቻች ማድረግ የሚሉ ሃሳቦች በሰነዱ ውስጥ ተካተዋል።
ታጣቂ ቡድኑ በስም ባይገለፅም የተሃድሶ ስልጠና እየወሰዱ ከሚገኙ አባላት ጋር እንደሆነ መግለጫው አስፍሯል።
Filed in: Amharic