>
5:26 pm - Tuesday September 15, 9903

ጥቃት የተሰነዘረባቸው የሆሮ ጉድሩ፤ አዲስ አለም አካባቢ ነዋሪዎች “ሙሉ ለሙሉ ተፈናቅለዋል”  (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ጥቃት የተሰነዘረባቸው የሆሮ ጉድሩ፤ አዲስ አለም አካባቢ ነዋሪዎች “ሙሉ ለሙሉ ተፈናቅለዋል”

        ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ወለጌ ቀበሌ ላይ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች “ሙሉ ለሙሉ” ቀያቸውን ለቅቀው መሰደዳቸውን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ምሽት በተነሰዘረው በዚሁ ጥቃት ሶስት ሰዎች መገደላቸውን ቢያንስ አራት ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ የጥቃቱ መፈጸምን እና የሶስት ሰዎችን መገደል ቢያረጋግጡም፤ ነዋሪዎች ሙሉ ለሙሉ አልተፈናቀሉም ሲሉ አስተባብለዋል።
በወለጌ ቀበሌ “አዲስ አለም” በሚል መጠሪያ ከምትታወቀው አካባቢ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ ታጣቂዎቹ በአካባቢያቸው ላይ ተኩስ የከፈቱት ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ ነው። በጥቃቱም ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች ሲገደሉ ስድስቱ ደግሞ መቁሰላቸውን አስረድተዋል። በአቤ ዶንጎሮ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የነበሩ የዓይን እማኝ፤ በጥቃቱ የተጎዱ አምስት ሰዎችን በህክምና ቦታው ተመልክቼያለሁ ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2021/3260/
Filed in: Amharic