>

የግብፅ አዲሱ ህልም ! (ሱሌማን አብደላ)

የግብፅ አዲሱ ህልም !

ሱሌማን አብደላ

 

በ“ ፕሬዚዳንት ሲሲ አደራዳሪነት ሃማስና እስራኤል” የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ወስነዋል።
በዚህ ጦርነት ላይ እጇን ሳታስገባ፣  በስውር እስራኤልን ስትደግፍ የነበረችው አሜሪካ፣ «ሲሲ ሙሉ አንገቱን አስገብቶ ከደረሰባት አለም አቀፍ ዉግዘት እንዲያድናት አድርገዋለች።
.
ቃል በቃል ሽማግሌው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት «ጆ» ባይደን ሲሲን ደዉለዉ አመስግኖታል። ሲሲም እንኳን በአሜሪካ ተመሰገንኩ ብሎ ወንድሜ አመሰገነኝ እያለ በፌስቡክ ገፁ ፅፏል። መቸም በአሜሪካ  ምስጋና ላይ የሲሲን መቆበድ ላጠናው ሰው ሲሲ እንቅልፍ መተኛቱንም እንጃ
ሲሲ፣ የተቆበደው አንድም በመካከለኛዉ ምስራቅ ፖለቲካ ላይ ራሱን ሱፐር ፖወር አድርጎ ከአሜሪካና ከአውሮፖዎች በላይ
ክስተት ሆኖ ታይቶት ሊሆን ይችላል።
በርግጥ ምክኒያት የለውም አልልም። ብሔራዊ ጥቅም በሚለው «.የአባይ ወንዝ ላይ.» አሜሪካ እዛው በአፍሪካ ህብረት ጉዳያችሁን ጨርሱ ስትለው፣ የሲሲን ድክመት ከጠበቀው በታች ትኩረት አሳጥቶት ነበር ።
አሁን ግን ለሲሲ የእስራኤልና የፍልስጤምን ግጭት እንደ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሊጠቀምበት የቋመጠ ይመስላል። አይጠቀምበትም አንልም ። ዌስትባንክ ወይም መስጀል አቅሷ የእስራኤል ነው ብሎ በድፍረት የተናገረ ሰው አሁን ለፍልስጤማውያን አዝኖ ለእስራኤል ታምኖ አይደለም ጦርነቱ እንዲቆም ተወዳ ተወዲህ ሲል የከረመው።
በሌላ በኩል ግብፅ ለእሰራኤል ልትሸጠዉ ያሰበችው «.የሲና በረሃ.»የአባይ ፕሮጀክት ከእስራኤል ጋር መያያዙንም ባንዘነጋው መልካም ነዉ። ምክኒያት የአባይ ውሀ ከመስሩ ተጠልፎ 176 ኪሎሜትር መሬት ለመሬት ተቆፍሮ የሲና በረሀን እንዲያለማ ተደርጓል።
ግብፅ ለፍልስጤሞች አረብ እንደ መሆናቸዉ መጠን «.ልክ እንደ  ሱዳን ከጎናቹህ ነኝ አላላቸዉም.» ለእስራኤል መልዕክት ልኮ በጀት « ያፈረሳሁትን ከተማ እኔ እገነባለሁ .» እናንተ ብቻ ተኩስ አቀሙ ብሎ እየተማፀነው ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ሲሲ መሆኑን አንዘንጋ !
እዚህ ምድር ላይ በሲኦ ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች አሉ ከተባለ ጋዛ ዉስጥ ሚኖሩ  ህፃናቶች ናቸው ። ጋዛ ስትወለድ በበሽታ ወይም በህመም ከምትሞተው ከምትሞተው ይልቅ በእስራኤል ቦንብ እንደምትሞት እራስህን አሳምነህ ነው።
በሌላ በኩል ለመጀመሪያ ግዜ
ተኩስ እንዲቆም የተማፀኑት
የተመድ ሊቀመበር አንቶኒዮ ጉቶሬዝ ሲሆኑ
እሱም ሁለት ጊዜ በአሜሪካ ወድቅ ተደርጓል ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅትና በፀጥታው ምክር ቤት ሲለመኑ ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉት አሜሪካና እስራኤል
የግብፅን አሸማጋይነት ተቀብለዋል።
በሁለም የዲፕሎማሲ መንገድ የማይጎዱት እና አዋጭ ሆኖ ያገኙት ሁለቱም  ሀገሮች (እስራኤልና አሜሪካ ) በአረቡ ሀገር ተቀባይነት ያላትንና የሲዊዝ ቦይ በር ቁል ያላትን የግብፅን መንግስት ሽምግልና
ያለምንም ማንገራገር ሀሳቡን ተቀብለዋል ።
በርግጥ፦ እነ አሜሪካና እስራኤል የግብፅ አሸማጋይነት፦ በአንድ ድንጋይ ሁለት  ወፍ ሆኖላቸዋል። አይከስሩም አይጠየቁም።
ጋዛ ላይ 211 ህፃናትን እንደፈለጉ በእስራኤል ቦንብ ገለዋል። አሉ የተባሉ የሀማስ ማዕከላዊ ቦታዎችን ደብድበዋል
ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ወደ አፈርነት ቀይረዋል። በዚህ ሁሉ ጥፋት እስራኤል ተጠያቂ እንዳትሆን ድምፅን በድምፅ የምትሸረፍ USA ከጎኗ ቆማለች። ጋዛ ላይ በጀቶቿ አመድ ያደረገቻቸውን ከተሞች ግብፅ እገነባለሁ አለቻት። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ የሚለው የአማርኛ ትርጉም መልስ ያገኘ ይመስላል !
እስከዛሬ በመካከለኛው ምስራቅ ትኩረት የተነፈገው የግብፅ ፖለቲካ አሁን ከወደቀበት ሊነሳ፣ በመጣር ላይ ያለ ይመስላል።
በርግጥ የግብፅ ዲፕሎማሲ ትኩረት ማጣት” ለኛ ”ለኢትዩጵያውያን ትልቅ እድል ህኖ አገልግሎናል። በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ የነ አሜሪካ እስራኤል አቋም
ግራ ገብቶት እንዲቆም ተገዶ ነበር።
የሁሉምን በር አንኳኩታ መፍተሔ ያጣችው ግብፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ሙሌት በግብፅ ላይ ምንም ጉዳት አያስከትልም ብሎ እውነቱን እንዲመሰክር አስገድደነው ነበር።
ውሎ ሳያድር ትናትና ሁለተኛው የግድቡ  ሙሌት እኛ ላይ ተፅኖ አያደርስም ያለው ሰውየ ዛሬ ምላሱን ቀይሮ፣ የዝናብ እጥረት ካጋጠመን ሙሌቱ ለግብጽ ከፍተኛ ስጋት ነው አለ።
«.በነ አሜሪካ ሙገሳ ካገኙ፣ ወደ ቀድሞው ግትር አቋማቸው መግባታቸው አይቀሬ ነው.»
.
በርግጥ የሳሚ ሽኩሪ የዛሬው ንግግር
ትናት ቀኑን ሙሉ የተሰበሰበው የአሜሪካ ሴኔት፣ በኢትዮጵያ ላይ ሊወስን የፈለገው፣ አስገዳጅ የፖለቲካ ጥምዘዛ ውስጥም እንጥፍጣፌ ወከባ መፍጠር እንችላለን
ከሚል የመነጨ አይሆንም አንልም።
እኛም ነገሩን በፖለቲካ መነፀር ውስጥ አስገብተን ከለካነው፣ የነሱ ቃል ማጠፍ አሜሪካውያን” በኢትዮጵያ ላይ ሊያሳድሩት ከሚፈልጉት ተፅእኖ ጋር መገጣጠሙ የአጋጣሚ ነው ብለን እንድናልፍው አያደርገንም !
እዚህ ላይ ሲሲን የቆበደው የጆ ”ባይደን፦ አስተዳደር ንግግርን ነጥለን ካየው፣  ሌሎች የአረብ ሀገሮች ግጭት ከሚያቀጣጥሉ ይልቅ የግብፅን መንግስት ፈለግ ቢከተሉ
እኛም የነሱን ፈለግ እንከተላቸዋለን  የሚለው የፕሬዝዳንት ጆባይደን ንግግር ነው።
ይህ የጆ ”ባይደን ንግግር፣ ለግብፅ ከመሬት
አፈር ልሶ እንደመነሳት ብቻም፣  ሳይሆን አጋጣሚዉን ተጠቅማ የተወችውን፣ የአባይ ጉዳይ «በ ድጋሚ እንድታሰላስለው.» እንዲሁም፦ ለዘብተኛውን የአሜሪካን ሀሳብ ለማስቀየር ይረዳኝ ይሆናል ብላ እንድታስ ያደርጋታል !
ሲሲ እንማጀቱ የሚያየውን የአረብ ሊግንና በአምባገነንነቱ ያጣውን የግብፅ ህዝብን
ድጋፍ ለማግኘት ሲል፣ የፍልስጤም ተጎጂዎችን በጋዛ ሰርጥ በኩል አስር  አምቡላንሶችን  ልኮ ሲያመላልስ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ሲሲ ይሄንን ሁሉ የሚደክመው በኢትዮጵያ ላይ ያሰበውን አንድ ነገር ለማሳካት ነው። እሱም ግድቡ ሞላም አልሞላም፣ ከዚህ ቡሀላ በግድቡ ዙሪያና፣  አጠቃላይ በናይል ወንዝ ላይ ልላ ልማቶችን እንዳናለማ
አስገዳጅ ስምምነት ላይ ማድረስ ነው።
Filed in: Amharic