>

የሌተና ኬሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም ትዝታዎች ሲጨለፍ ........

ትዝታ ሲጨለፍ ……..

“የሄድኩት ካገር ወጥቼ ለመቅረት ሳይሆን የመጨረሻ የቀረኝን እድል ለመሞከር ነበረ”
ግንቦት 13 1983  ጓድ መንግሥቱ አ/አ ለቀው የሄዱበት እለት ነበር ።
(የሌተና ኬሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም ትዝታዎች:— በ  Guenet Ayele Gruenberg ።)
ገነት:—   ህዝቡ ” ሁሉም ነገር ካልተሳካ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ይሆናል ፣ ራሱን ያጠፋል ሲባል ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ቤተሰቡን ፣ልጆቹን ካሸሸ በኋላ ሀረሪ (ዝንባብዌ ) ገባ ።” ይሎዎታል ። ለዚህ የሚሰጡት መልስ አለ??
መንግሥቱ ሐይለማሪያም:—
መጀመሪያ ነገር ቴዎድሮስን ለመሆንም ላለመሆንም አካሄዴ ምን ለማድረግ ነበር ነው? የወጣሁት በዚያው ለመቅረት አልነበረም ።
…..ወደ ጥያቄሽ ልመለስና ….. እሳቸው የሞቱበት ጊዜና ሁኔታ የተለየ ነው ። ለአፄ ቴዎድሮስ ትልቅ አድናቆት አለኝ ።
….. ወደኔ ስንመጣ  እኔ አ/አ ብቆይም በዚያ በተበላሸ ሁኔታ በተዳከመ አሰራር ከማን ጋር  እንደምሰራ ለመገመት ያስቸግረኛል ። ተስፋ ላለመቁረጥ ፣እጅ ላለመስጠት በደቡብ በኩል ይሄ መሳሪያ ቢገባልን ኖሮ የጎሬላ ውጊያ ለማድረግ በዚህ ብቻ የመጨረሻ ተስፋዬን ጥዬ ነበር ።
ከዚህ በተረፈ የኛ ባለስልጣኖች እንዳደረጉት ተሰልፌ ሄጄ ተራ ጠብቄ (ከት ብለው እየሳቁ )እጄን አልሰጠሁም ። …..ዘለዓለማዊ አደለንም ሁላችንም እንሞታለን ለምን አልሞቱም? ተንጋግተው ሄደው እጃቸውን ከመስጠት?!  “
”  …..የጦር አዛዦችን ብትይ  አ …..ንድ (ረገጥ እያደረጉ )ሀያና ሰላሳ ወታደር አስከትሎ ትንሽ የተንቆራጠጠ ነበር? ማነው ለመሆኑ ከሴት ከወንድ  የኔን ድፍረትና ወኔ ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ የሚችለው? ይሄን ህሌና ያለው ይመርምር ።
የት ነበሩ በፈንጂ ላይ ስረማመድ? ጦሩ መሀል አልነበርኩም እንዴ? ትግራይ አልነበርኩም እንዴ? ኤርትራ አልነበርኩም እንዴ? ጅጅጋ በተከበበ ጊዜ ማን ገፍቶኝ ነበር የሄድኩት? ይከተሉኝ ነበር እንጂ ተከትያቸው አውቃለሁ እንዴ?!
በአብዮቱስ ጊዜ እንደ መለስ ዜናዊ የጥይት መከላከያ እያደረኩ ፣ ጥይት በማይበሳው መስታወት ውስጥ ቆሜ ነበር እንዴ አደባባይ የምወጣው? ብረት ለበስ መኪና እያንጋጋሁና ወታደር ግራና ቀኝ እየማገርኩ ፣ ትራፊክ እያስቆምኩ ነበር እንዴ አዲስ አበባ ውስጥ የምዞረው?? ደረቴን ገልብጬ አልነበር እንዴ በከተማ ፣በገጠር ፣በየገበሬው ጎጆ ስገባ የነበረው?? ይሄ ሁሉ በህዝቡ ላይ እምነት ስለነበረኝ ነው ።
ይሄን ሁሉ ያነሳሁት ራሴን አንቱ ለማለትና ለመመፃደቅ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠላቶች 17 አመት የፈተኑኝ ሰው ነኝ ። ማውራት ቀላል ነው  ማድረግ ግን ሌላ!
የሄድኩት ካገር ወጥቼ ለመቅረት ሳይሆን የመጨረሻ የቀረኝን እድል ለመሞከር ነበረ።
Filed in: Amharic