የብርሀን ልጅ
*.. ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ናት ፥
*..ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማሳደድ ይቁም
በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ ቅድስተማሪያም ጠቅላይ ቤተክህነት በር ላይ ቤተከርስቲያናችን ለሁለት አትክፈሏት መንግሥት ከኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ እጁን ያንሳ በሚል የተቀውሞ ሰልፍ እየተደረገ ነው::
መስቀል አደባባይ ለተካሄደው የአፍጥር ስርአት ሙሉ ወጪ በመሸፈን እና በቂ ጥበቃ በማድረግ ሽርጉድ ሲል የዋለው መንግስት እውነትን ብቻ ይዘው የወጡ የቤተክርስቲያን ልጆችን ያለምንም ምክንያት ማሳደድ ጀምሯል።
ከረፋዱ ጀምሮ እስከ ደቂቃዎች በፊት ድረስ ለቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለቅድስት ቤተክርስቲያን በፍጹም ሰላማዊ መንገድ ” አለሁ” ሲሉ የነበሩ ፍጹም ሰላማዊ የቤተክርስቲያን ልጆችን ከቤተክርስቲያኑ እና ከአካባቢው በማራቅ ብዛት ያላቸውን አድማ በታኝ የፌደራል ፖሊስ አባላት በማሰማራት ከየአቅጣጫው ወደ ቦታው የሚወስዱ መንገዶችን ዘግቷል።
ለአንዱ በሳፋ ለሌላው በአካፋ አይነት መንገድ የት ያደርስ ይሆን? እኛ ግን አሁንም ከቅዱስ አባታችን እና ከቅድስት ቤተክርስቲያን ጎን መቆማችንን አንተውም!
ፖሊስ ሰልፈቹን ለመበተን ጥረት እያደረገ ነው:: መላው ኦርቶዶክሰውያን ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ እየቀረበ ነው::