ዘመድኩን በቀለ
… ቪዛ ተከለከለ ትዪኛለሽ እንዴ? ይሄ መልአከ ሞት ገና እንጦሮጦስ ይዞሽ ይወርዳል… ቪዛው ቢቀርበት ደሮስ ከኤርትራና ከጅቡቲ… ከሶማሊያና ከደቡብ ሱዳን ከታችኛው ዲቪዝዮን… ከቀበሌ ቡድን ጋር የሚርመጠመጥ… ያቺን ከኃያላን ሃገራት ተርታ የሚሰለፍ ዲፕሎማሲ የምትሠራ… ዲፕሎማቶችም የነበሯትን ሃገር የካድሬ ወሬ… የአርቲስቶችና የሞዴላ ሞዴሎች መጫወቻ ያደረጋት አውርቶ አደር አፈ ቅቤ… ሆደ ጮቤ ሶዬ… ገና ምን አይተሽ ነው ስለቪዛ መከልከል የምትጨቀጭቂኝ። ቪዛ እንጂ ፒዛው እንደሆነ በእጁ ነው። እግዚአብሔር እስኪፈርድበትማ መጠበቅ ነው።
… ይሄን መልአከ ሞት… ገና ምን ታይቶ… ጋዳፊ… የሳዳም ሁሴን አምላክ ሆይ ከወዴት አለህ? የሞት ነጋዴዎች ቪዛ ተከለከሉ ብዬ ላሽቃብጥ እንዴ ማሚትዬ? በይ ንኪው…
ነገርኩሽ… አትጨቅጭቂኝ
… አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከአንዱ ክፍለ ሃገር ወደ አንዱ ክልል ለመሄድ በማይችልበት ሁኔታ… አንዱ ኢትዮጵያዊ በገዛ ሃገሩ ከቦታ ቦታ መዘዋወር በታገደበት ሁኔታ… ከአዲስ አበባ በመቶ ኬሎ ሜትሮች ርቀት ከኦሮሚያ ክልል ወደ ዐማራ ክልል መንቀሳቀስ የሚያሳርድ በሆነበት ሁኔታ… በወለጋ… በመተከል… ዐማራ በመሆናቸው ብቻ ዜጎች እየታረዱ በጅምላ የሚቀበሩበት ነገር ባልቀረበት ሁኔታ… በደቡብ በጉማይድሌ… በሰገን… በኮሬ… በጉጂ ዜጎች ያለከልካይ በኦነግ በሚታረዱበት ሁኔታ… ዜጎችን በአደባባይ መረሸን መንግሥታዊና ሕጋዊ በሆነበት ሁኔታ… በትግራይ… በቻግኒና በመተከል… በጉማይድሌ… በኮሬ… ተፈናቃይ ዜጎች የወገን ያለህ ብለው በሞትና በህይወት መካከል በሚቃትቱበት ወቅት ጥጋበኛ ነፍሰ ገዳይ ሞዴላሞዴሊስቶቹ ሜካፓም የህወሓትና የብልጽግና ባለሥልጣናት የአማሪካ ቪዛ ተከለከሉ ብዬማ ክፍት አፌን አልከፍትም። አላሽቋልጥም። አላሽቃብጥም። ለደንታቸው ነው።
… የዐማራን ልዩ ኃይል በፓርላማ ለይቶ የከሰሰው ማነው? ቀድሞ ያሳጣው ማነው? አሁን አማሪካ ነጥላ የዐማራው ልዩ ኃይል ላይ የጉዞ እቀባ የጣለችው ለምንድነው? ኦሮሙማ በዐማሩማ ላይ… ትግርሙማ እና ኦሮሙማ በዐማሩማ ላይ የሚሸርቡት ሴራስ ተስውሮአችሁ ነው? ፋኖ ድሮስ አማሪካ ምን ሊያደርግ ይሄዳልና ነው? ቪዛ ተከለከለ ቀረስ? ዐባይን መሻገር የማይችል… ሽባ ተደርጎ የተጠረነፈ አትላንቲክን አቋርጦ ምን እንዳይቀርበት ነው። ይልቅ ዐማራ እነ ኢዜማ በሚያሰራጩት ዜና ተደናብረህ ለብልጽግና አታሽቋልጥ። ያው በገሌ ነው የሆንክ ሁላ በጥጋበኞች ውስወሳ እንዳትነዳ… ዐማራን ሊያስመታ ፈንጅ የቀበረው ራሱ ኦሮሙማ ነው። ማይካድራን የደበቀ… ህወሓትን ሦስት ዓመት ሙሉ እንድትወበራ ያደረገው ራሱ ዐቢይ አሕመድ ነው። 20 ሰው ለፍርድ ማቅረብ አቅቶት… 2 ሚልዮን ትግሬዎችን በረሃብ እየፈጀ ያለው እኮ ራሱ ዳተኛው ዐቢይ አሕመድ ነው።
… እነዚህን ደም አፍሳሾች… እነዚህን ነውረኞች… እነዚህን ነፍሰ በላ ሰው መሳይ አውሬዎች… እነዚህን ነውር ጌጣቸው የሆነ… የሃገር ሉዐላዊነትን በኤርትራና በሱዳን ያስደፈሩ አውርቶ አደር ባንዳ ጭራቆች… ፈጣሪዬ የእጃቸውን ይሰጥልኝ ዘንድ… በአፍጢማቸውም ደፍቶ… በአናታቸው ይተክልልኝ ዘንድ… የድሆችን ደም በከንቱ ያፈሰሱ… ያስፈሰሱ ደም አፍሳሾችን በምድር ሳሉ ይቀጣቸው ዘንድ ፈጣሪዬን ስማጸን ቆይቼ አሁን ምን ተገኘ ብዬ ነው ምናቸውም ለማይጎዳው… ሽርሽሩ ብቻ ለሚቀርባቸው ሆዳሞች… አዕምሮ ለተነሡ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ለሆኑ ወንጀለኞች አማሪካ ቪዛ ከለከለቻቸው ብዬ የማሽካካው?
… ወዳጄ የቅጣቱ ዘመን እየቀረበ ስለሆነ የገባ አይወጣም። ሸሽቶ ማምለጥም የማይታሰብበት ዘመን ሩቅም አይደለም። ጋዳፊ… ሳዳም ሁሴንን የቀጣ ጌታ እነዚህን የማይቀጣበት ሁኔታ አይታየኝም። እነ ዘሎ ጥልቅ… መውጪያው ጭንቅ… ኦሆሆ … ነውረኛ ነፍሰ ገዳዮቹ ቪዛ ተከለከሉ… አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ ብዬማ አላሽቋልጥም። ለደንታቸው ነው። እንጦሮጦስ ይግቡ…
… እኔ ግን እላለሁ። አሁንም መድኃኔዓለም የእጃችሁን ይስጣችሁ። መቶ ሚልዮን ህዝብ… ለጭንቀት… ለስጋት እንደዳረጋችሁ… በቀቀን ያድርጋችሁ…