>

ኦሮሙማው ዓብይ አህመድ ኢትዮጵያን ከሰሜን እና መሀል ማፈራረሱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል...!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

ኦሮሙማው ዓብይ አህመድ ኢትዮጵያን ከሰሜን እና መሀል ማፈራረሱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል…!!!

ኤርሚያስ ለገሰ

አዲስ አበባ አንገትሽ ላይ የጠለቀው ገመድ ሸምቀቆ እየጠበቀ ነው!! ግን ዓብይ አህመድ አዲስአበቤን ምን ያህል ቢጠላና ቢፈራ ነው ይህን የአፓርታይድ ሕግ ለመተግበር የተሯሯጠው?
 
 
በነገራችን ላይ የኦሮሚያው ፍ/ቤት ጉዳይ ማብራሪያ የሚፈልግ ይመስለኛል!
••• ይህ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ተቋማት የሚኖራቸውን የወንጀል እና የፍታብሄር ጉዳይ የማየት ስልጣን አለው ተብሏል።
√√ ተቋማቱ ከማን ጋር ፣ በምን ጉዳይ የሚኖራቸውን ጉዳይ ነው የሚመለከተው??? ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ጋርስ እንዴት ታይቷል?
••• በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በቋንቋቸው የመዳኘት መብት በዚሁ ፍርድ ቤት ይተገበራል ተብሏል።
√√ በምን ጉዳይ? ወንጀል?  ፍታብሄር?  ከማን ጋር በሚኖራቸው ክርክር?  ከፌደራል ህጎችስ ጋር እንዴት ታይቷል?
 ••• ፍርድ ቤት ከመንግስት የስልጣን ክፍፍሎች አንዱ ነው። ይህ ፍርድ ቤት የተቋቋመው በኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 216/ 2011 ይመስለኛል።  እናም የዚህ ፍርድ ቤት ስልጣን ከህገ መንግስቱ ፣  ከአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር እና ከፌደራል አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር  በምን መልኩ ታይቷል!!!
Filed in: Amharic